2012-06-06 14:41:19

እምነትና ሥነ ሙዚቃ


የሮማ ሰበካ የማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን ጉዳይ ቢሮ እምነትና ሥነ ሙዚቃ በሚል ርእስ ሥር ከትላትና በስትያ በቅድስት ማርያም ዘ አርኮኤሊ ባሲሊካ ባዘጋጀው የአንድ ቀን ዓውደ ጥናት የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚና የሥነ ሙዚቃ ሊቅ የውሁድ ጥዑም RealAudioMP3 ሙዚቃ ኦርኬስትራ (መሪ) መምህር ሪካርዶ ሙቲ ተሳትፈው አስተምህሮ ማቅረባቸው ዓወደ ጥናቱን የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ማሪና ታማሮ ካጣናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
መምህር ሪካርዶ ሙቲ ባቀረቡት አስተምህሮ ሙዚቃ (ውሁድ ጥዑም ሙዚቃ) ተስተውሎ ሳይሆን፣ ተመስጦና ሰቂለ ህሊና ነው። በእምነትና በሥነ ሙዚቃ መካከል ያለው ውይይትና ግኑኝነት በሙዚቃ የድምጽ (ልሳን) ጽሑፍ ወደ ዳር ማዶነት ወደ ሆነው ወሰን አልቦ ዘንድ የሚሸኝ ህቡእ ብርሃን አለ። ብዙ የውሁድ ጥዑም ሙዚቃ ትያትሮች ከሚተርኩት ታሪክ ማዶ እይታችን ወደ ሰማይ ቀና እንዲል የሚገፋፉ መሆናቸው በስፋት እንዳብራሩ ልእክት ጋዜጠኛ ታማሮ ገልጠዋል።
ከተካሄደው ዓወደ ጥናት ፍጻሜ ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ ከቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ታማሮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በሙዚቃና በእምነት መካከል ያለው ግኑኝነት ልክ በሁለት እህታማቾች መካከል ባለው ግንኝነት ልንመስለው እንችላለን፣ ሙዚቃ፣ ድምጸ ሙዚቃና የሙዚቃ ድምጸ ጽሑፍ በስሜት ኅዋሳት ግንዛቤ ብቻ የሚታጠር ሳይሆን ጥዑም ቅኝቱ አማካኝነት ወደ ዳር ማዶኖት የሚሸኝ ነው። ስለዚህ እምነትም ሆነ ሙዚቃ ወደ ላይ ቀና እንድንል ወደ አቢይ ምሥጢርና ወደ ተለየውና ሌላው የሚሸኙን ሁለት መንገዶች ናቸው ብለዋል።
የሚዚቃ ድርሰቶች፣ ከማኅበራዊ ሰብአዊ ገጥመኝ የሚመነጩ ናቸው፣ ብዙ የሙዚቃ ድርሰቶችም የመጽሓፍ ቅዱስ ቃላትና መልእክት ሲጠቀሙ ይታያል። ምንም’ኳ አንዳንድ ሙዚቃዎች ከክርስትና እምነት ውጭ ቢሆኑና ስለ ክርስትና ምንም ነገር የማይሉ፣ ዓለማዊነት የተካኑ ቢሆንም ቅሉ፣ በገዛ እራሳቸው ላይ የሚያስቀሩ ወይንም አግተው የሚይዙ ሲሆኑ ፈጽሞ ታይቶም ተሰምቶም እይታወቅ፣ ሊሆኑም አይችሉም፣ ምክንያቱም የሙዚቃ ጥሪ ወደ ላቀው ዳር አልቦ ወደ ሆነው መሸኘት ነው። ስለ እግዚአብሔር ለመናገር በማይፈልጉና እግዚአብሔር አለ ለማለት የማይሹ ኢአማንያን ጭምር በሰው ልጅ ዘንድ በኑባሬ ያለው የዳር አልቦነት ህላዌ ግንዛቤው ላይኖራቸው ማድረግ አይቻላቸውም ሙዚቃም እንዲህ ባለ መልኩ ለመረዳት ይቻላል በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.