2012-05-31 10:04:21

ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ጉባኤ
ብፁዕ ካርዲናል ስኮላ፦ “የቅዱስ አባታችን በጉባኤው መገኘት ልዩ ጸጋ ነው”


እ.ኤ.አ. እስከ ፊታችን ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ.ም. የሚዘልቀው ግንቦት 30 ቀን 2012 ዓ.ም. በኢጣሊያ ሚላኖ ከተማ የተጀመረው ሰባተኛው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ጉባኤ ዋዜማ በከተማይቱ በሚገኘው በዓለም አቀፍ የትርኢት አደባባይ በሚላኖ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ስኮላና የቤተሰብ ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ኤኒዮ አንቶነሊ ተጋባእያን ልኡካንን በመቀበል የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት የታከበለበት የዋዜማ ጸሎት አማካኝነት በይፋ መጀመሩ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ይህ በሚላኖ ከተማ በሚገኘው በዓለም አቀፍ የትርኢት አደባባ የተካሄደው የሰባተኛው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ጉባኤ መቅድም ያደረገው በመክሲኮ የተካሄደው ስድስተኛው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ጉባኤ አስፍተላልፎት የነበረው የማጠቃለያ ሰነድ ዙሪያ በማስተንተን ሰባተኛው ጉባኤ ስለ ቤተሰብ ቲዮሎጊያዊ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ለመወጠት ታልሞ ለሦስት ቀን ቤተሰብ ሥራና በዓል ርእሰ ጉዳይ ማእከል በማድረግ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ በተመለከተ ጠቅላይ መግቢያ የተሰጠበት ሲሆን፣ የቤተሰብ ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል አንቶነሊ ባሰሙት መልእክት ቅዱስ አባታችን በዚህ ጉባኤ ለሚሳተፍ ሁሉ የምሉእ ሥርየተ ሐጢአት ውሳኔ ማስተላለፋቸው ጠቅሰው በሚላኖ ተገኝተው በሚመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴና በሚያቀርቡት ሥልጣናዊ ስብከት አማካኝነት ጉባኤ እንደሚጠቃለል ማሳወቃቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።
ሚላኖ ከተማ በዚህ በሰባተኛው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ጉባኤ በሚሳተፉት ከአምስቱ ክፍለ ዓለም በተወጣጡት የቤተሰብ አባላት ብዛት መጥለቅለቅዋ ሲገለጥ፣ ሚላኖ በሚገኘው ካቴድራል ፊት የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 ምስል የተኖረበት ሆኖ ይኸው ጉባኤና ተጋባእያኑ ቅዱስነታቸው በጉጉት እየተጠባበቁ መሆናቸው የሚያረጋግጥ ምልክት መሆኑም የሚላኖ ከተማ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ስኮላ ጉባኤ ከሚከታተለው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ ቅዱስ አባታችን በጉባኤ ማጠቃለያ ተገኝተው ለሚሰጡት ሥልጣናዊ ምዕዳን ቀድመው በማመስገን የቅዱስነታቸው መገኘትና የሚሰጡት ሥልጣናዊ ምዕዳን ልዩ ጸጋ ነው።
ይኽ በሚላኖ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ጉባኤና የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መገኘት በርግጥ የሚላኖ ከተማ ሰበካና የክልሉ ብሔር ኅብረተሰብ፣ ቤተሰብ እጹብ ድንቅ ጸጋና ማኅበራዊ ሰብአዊ መልካምነት መሆኑ ግንዛቤ እንዲኖረው ማነቃቃቱ ገልጠው፣ ቤተሰብ በቤተ ክርስትያንና በብሔረ ኅብረተሰብ በተጨባጭ ሁኔታ ሁሉ ማእከል መሆንና ይኽ ማእከላዊነት የቤተሰብ ባህርይ በሁሉም በማኅበራዊ በሰብአዊ በፖለቲካዊና በኤኮኖሚያዊ ዘርፍ መረጋገጥ እንዳለበት የሚያሳስብ ጉባኤ ነው። ስለዚህ ይህ የሚላኖ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ቀጣይነት ባለው ጽኑ ውህደት እርሱም በሚሥጢረ ተክሊል የጸና በማንም በማይሻረው የእግዚአብሔር ፈቃድ መሠረት የሚረጋገጠው ቤተሰብ በተመለከተ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ቀዳሜ ገጽ በመስጠት በተለያየ ዘርፍና ሥነ ጥናት አማካኝነት የተለያዩ የውይይት መርሃ ግብሮች እንዲያከናውኑ ማነቃቃቱንም ገልጠዋል።
ቤተሰብ የመዳን ጸጋ የተቀበሉት በአስፍሆተ ወንጌልና በማዳን እቅድ መሠረት መድኅናዊ ሱታፌ ያለው በማኅበረሰብ በቤተ ክርስትያንና ከቤተ ክርስትያን ጋር የእግዚአብሔር ቃል የሚመሰከርበት ቤተ እግዚአብሔር ማለት ነው። ከዚህ በመንደርደር በርግጥ የቤተሰብ ጥሪ የእግዚአብሔር ፍቅር መግለጫ በመሆኑም ፍቅር የሚኖርበት ሥራ እና እረፍት ወይንም በዓለ የሚኖርበት፣ ለወሊድነት ጸጋ ገዛ እራሱ ክፍት የሚያደርግ በመሆኑም፣ ይህ የሚላኖው ጉባኤ ሥራና በዓል በሚል ርእስ ሥር እንዲመራ መወሰኑ ምክንያታዊ ነው ብለዋል።
ይህ ጉባኤ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እምነት ላይ እንዲተኮር እየሰጡት ያለው ምዕዳን አስተምህሮ እና ውሳኔዎችን በመገንዘብ በጠቅላላ በኤውሮጳ የተጋረጠው ዘርፈ ብዙ ቀውስ መሠረት የእምነት ቀውስ መሆኑ ይኽም ኤውሮጳ ባህላዊ ማኅበራዊ እና ሰብአዊ መሠረተ ባህልዋ የሆነው እምነት ችላ በማለት የተያያዘቸው ሂደት እንደሚመሰክረው የሰጡት ሥልጣናዊ ትንተና በርግጥ እውነት ነው። እምነት የግኑኝነት መሠረት ነው ሲባል፣ በአንድ ወንድና በአንዲ ሴት መካከል ከባለንጀራ ጋር ለሚደረገው ግኑኝነት በጠቅላላ ለሰብአዊና ለማኅበራዊ ግኑኝነት መሠረት መሆኑ ነው የሚገልጠው። ሥራ በተመለከተም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ቁርባን በመሥራት የሰው ልጅ ሥራ ያለው ክብር ገልጦልናል፣ በዚህ መንፈስ ተመርቶ ዕለታዊ ሥራችንን በማንበብና በመኖር ሥራ ያለው ክብር ማክበር ዕረፍት መልካም መሆኑ ያረጋግጥልናል። በጠቅላላ ሰብአዊ ኑሮአችን በእምነት ሥር በቃልና በሕይወት ስንገልጠው ብቻ ነው ትርጉም የሚኖረው፣ ስለዚህ ይህ የሚላኖ ጉባኤ በተለያየ መልኩ ይኸንን እንደሚያረጋግጥ ገልጠው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.