2012-05-26 09:26:52

የቅዱሳን ቀርሎስና መተዲዮስ ዓመታዊ በዓል


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በዩሊዮስ ዘመን አቆጣጠር የሁለቱ ወንድማማቾች ቅዱሳን የኤውሮጳ ተባባሪ ጠባቂ ቅዱሳን ቀርሎስና መተዲዮስ ዓመታዊ ክብረ በዓል ምክንያት በቡልጋሪያ አዲስ ርእሰ ብሔር ሮሰን ፕለቭነላይቭና የቀድሞ የረፓብሊካዊት ዩጎዝላቪያ አገር ነበር በመቄዶኒያ መራሔ መንግሥት ኒኮላ ግሩአቭስኪ የተመሩት የሁለቱ አገሮች ልኡካን በተናጥል ተቀብለው ማነጋገራቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
እነዚህ ሁለት ቅዱሳን የአንድ አባትና እናት ልጆች ከመሆናቸውም ባሻገር የአንድ እምነት ተከታይ ወንድማማቾች ቀርሎስ ባህታዊ መተዲዮስ ጳጳስ እ.ኤ.አ. በዘጠነኛው ክፍለ ዘመን የቢዛንታይን ግዛት በነበረቸው በተሰሎንቄ ከተማ የተወለዱ ቀደምት በምስራቅ ኤውሮጳ አስፍሆተ ወንጌል ያነቃቁ በተለይ ደግሞ የስላቭ ሕዝቦች ይኖሩባቸው በነበሩት በጳኖኒያና ሞራቪያ ከተሞች አስፍሆተ ወንጌል ያፋጠኑ፣ ቀርሎስ ለስላቭ ሕዝብ የገዛ እራሱ ፊደሎች የፈለሰፈ በዚህ ቋንቋ ቄርሎስ ፊደል በመጠቀምም መጽሓፍ ቅዱስ የተረጎመ መሆኑም የበቤተ ክርስትያን የታሪክ ማኅደር ይገልጠዋል።
የሁለቱ አገሮች ልኡካን ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ግኑኝነት ሥንብት በመቀጠል የቅዱሳን ቀርሎስና መተደዮስ ቅዱሳት አጽም ባረፈበት ሮማ ከተማ በሚገኘው በቅዱስ ቀለመጦስ ባሲሊካ መንፈሳዊ ንግደት ፈጽመው እዛው ለክብረ በዓለ ቅዱሳን ቀርሎስና መቴዶስ ባረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ ተሳትፈው መንፈሳዊውን ንግደት እንዳጠናቀቁ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.