2012-05-24 17:41:47

የቤተ ሰቦች ጉባኤ በሚላኖ -ጣልያን ፡


በዚሁ በተያዝነው ወርሃ ግንቦት መጨረሻ በሰሜናዊ ጣልያን ሚላኖ ከተማ ላይ

የቤተሰቦች ሀገሮች አቀፍ ጉባኤ እንዲከናወን በእቅድ መያዙ የሚታወስ ነው ።

ጉባኤው ከ30 ግምቦት እስከ ሰነ ሶስት ቀን እንደሚዘልቅ እና ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት የዚሁ ጉባኤ ተሳታፊ እንደሚሆኑ አይዘነጋም ።የቫቲካን ክፍለ ማኀተም ትናትና የጉባኤው ይዘታ ትኩረት ሰጥቶ ባወጣው መግለጫ መሠረት ቤተ ሰብ የሕብረተሰብ ሃብት ሀብት ነው ።በቅድስት መንበር የቤተ ሰብ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብጹዕ ካርዲናል ኤንዮ አንቶነሊ የሚላኖ ከተማ ሊቀ ጳጳስ ብፅዕ ካርዲናል አንጀሎ ስኮላ በየቫቲካን ክፍል ማኅተም ተገኝተው የጉባኤው ይዘታ እና አካሄድ በተመለከተ መግለጫ መስጠታቸው ተገልጸዋል።በቅድስት መንበር የቤተ ሰብ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያካሄደው ጥናት የተመረኮሰ ቤተ ሰብ የሕብረተ ሰብ ሃብት ነው የተሰየመው እና ለሕትመት የበቃው መጽሐፍ በዚሁ ግንኙነት ይፋ እናደሆነ የቫቲካን ክፍለ ማኀተም አስታውቀዋል።ጤናማ ቤተ ሰቦች ከሌሉ ጤና ያለው ሕብረተ ሰብ አለ ማለት አስቸጋሪ መሆኑ እና ቤተ ሰቦች ተገቢውን እንክብካቤ ማግኘት እንደሚጠበቅ ብጹዓን ካርዲናላት ኤንዮ አንቶነሊ እና አንጀሎ ስኮላ ማመልከታቸው ከቦታው የደረሰ ዜና አስገንዝበዋል።የሥነ ማሕበረ ሰብ ጥናት ጠቢብ ፕሮፈሶስር ፒየር ፓውሎ ዶናቲ በበኩላቸው እንዳመልከቱት በመሰረቱ አንድ family ቤተ ሰብ ደስታ ነው ደስታው የሚቃወሰው ቤተ ሰቡየኤኮኖሚ ችግር ሰለባ ሲሆን ነው እና ፡ ጣልያን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ስለ ቤተሰብ የሚከተሉት ፖሊቲካ የተሳሳተ ሲሆን ያ ቤተ ሰብ የነበረውን ደስታ እየራቀ ይሄዳል ።የሕብረ ሰብ መሠረት ቤተ ስብ ነው ከተባለ ለቤተ ሰብ እንክብካቤ መስጠት እንደሚጠይቅ ፕሮፈሶር ፒየር ፓውሎ ዶናቲ በማያያዝ መግለጻቸው ተዘግበዋል።ሁለቱ ብፁዓን ካርዲናሎች በቃል ኪዳን ጸንቶ መኖር እንደሚያሻ እና ቃል ኪዳን ሲበተን በቤተ ስቦች ላይ ከፍተኛ ሥነ ልቦናዊ እና ማተርያላዊ ችግር እንደሚደቀን አስገንዝበዋል በማለት ከቦታው የደረሰ አስገንዝበዋል።ይሁን እና በዚሁ በተያዝነው ወርሃ ግንቦት 30 ቀን በሰሜናዊ ጣልያን ሚላኖ ከተማ ላይ ለሶስት ቀነት የሚዘልቅ ዓለም አቀፍ የቤተ ሰቦች ስብሰባ የፋሚሊ የቤተ ሰብ ወቃታዊ ሁኔታ ትኩረት ሰጥቶ እንደ ሚወያይ ይታወቃል።ዓለም አቅፉ የቤተ ሰቦች ጉባኤ ስራና ቤተ ሰብ የተሰየመ ርእስ በዋንነት የሚነጋግርበት ጉዳይ እንደሆነም ተያይዞ ተገልጠዋል።ከዚህ ባሽገር በበዓል ግዜ ቤተ ሰብ ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኝበት ግዜ መሆኑ እና በዓልየክርስያንእሴት መሆኑ የሚያንጸባርቅ በጥናት የተደገፈ ጽሑፍ ለጉባኤው እንደሚቀርብ ተመልክተዋል።የሚላኖ ዓለም አቀፍ የፋሚሊ የቤተ ሰቦች ጉባኤ በማስመልከት ከየቫቲካን ማኅተም ክፍል ይፋ የሆነ መግለጫ እንደዘገበው ፡ በዚሁ ጉባኤ አንድ ሚልዮን ቤተ ሰቦች ተሳታፊ እንዲሆኑ እንደሚጠበቁ ቅዱስ አባታችን በነዲክት ወርሃ ሰነ ሶስት ቀን በሚመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ 300 ሺ ቤተ ሰቦች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተመልክተዋል።ጉባኤውን ለመከታተል የጣልያን ጨምሮ አንድ ሺ ጋዜጠኞች መመዝገባቸው ከውጭ ለሚመጡ ቤት ሰቦች ለማስተናገድ 50 ሺ ዩሮ እንደተዋጣ ፡ 34 ሺ አልጋዎች ዝግጁ መሆናቸው አምስት ሺ በበጎ ፈቃዳቸው በአስተናጋድነት እንደሚሰመሩ ተገልጠዋል።11 ሺ የሚላኖ ከተማ ቤተ ሰቦች እያንዳዳቸው አንድ ቤተ ሰብ በግል ቤታቸው ለማስተናገድ ፈቃደኛ መሆናቸው ተመልክተዋል።ከአፍሪቃ ሀገራት የኮንጎ ረፓብሊክ የኬንያ ኡጋንዳ ደቡብ ሱዳን ቤተ ሰቦኦች በዚሁ ዓለም አቀፍ የቤት ሰቦች ግንኙነት ተሳታፊ እንድሚሆኑም ተጠቁመዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.