Home Archivio
2012-05-18 14:31:16
“ጽሞናና ቃል”፦ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ቀን
ከትላንትና በስትያ እዚህ በቫቲካን ረዲዮ ሕንፃ በሚገኘው ማርኮኒ የጉባኤ አዳራሽ 46ኛው ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ቀን ላይ ትኩረት በማድረግ ጽሞናና ቃል በሚል ርእስ ሥር የተመራ
ዓውደ ጥናት መካሄዱ ሲገለጥ፣ በተካሄደው ዓወደ ጥናት ንግግር ያሰሙት የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የመግናኛ ብዙሃን ጉዳይ የሚከታተለው ድርገት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ዶመኒኮ ፖምፒሊ፣ እፊታችን እሁድ የሚከበረው ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ቀን ምክንያት በማድረግ ጽሞናና ቃል በሚል ርእስ ሥር ውይይት ማካሄዱ በርግጥ የመገናኛ ብዙሃን ዓላማ የሚገልጥ ነው። ጽሞናና ቃል ሁለት ተቃራኒ ተመስለው ቢገለጡም፣ የሚደጋገፉ ናቸው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የመገናኛ ብዙሃን ተጨባጭነቱን በተመለከተ ቅጽበታዊ ግንዛቤ ሊኖረን እንደሚገባን ብቻ ሳይሆን ግንዛቤውም እንዴት ሊኖረን እንደሚችል መንገዱንም ጭምር ያሳዩናል፣ በመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ ብዙዎን ጊዜ ቃላት ላይ ይተኮራል ይኽ ደግሞ የንግግር ውርጅብኝ ሆኖ ይታያል፣ ማራኪው ከጽሞና የሚመነጨው ቃል ብቻ ነው። ከመናገር በፊት በጽሞና ማስተንተን አስፈላጊ መሆኑ አብራርተዋል።
ሮማ በሚገኘው ሮማ ትረ ተብሎ በሚጠራው መንበረ ጥበብ የሥነ ኅብረተሰብ መምህር ፕሮፈሰር ጃንፒየሮ ጋማለሪ በበኩላቸውም ባሰሙት ንግግር፣ ጽሞና የአለ መኖር ወይንም የአስተንትኖ በጥልቀት ግንዛቤ የሚከናወንበት የኅላዌ ሥፍራ ነውን የሚለው ጥልቅ ጥያቄ ላይ ያተኮረ ሃሳብ ሲተነትኑ፣ ፖፖሊ ኤ ሚሲዮነ የተሰየመው መጽሔት ዋና አዘጋጅ አባ ጁሊዮ አልባነዘ፣ መገናኛ ብዙሃን በቤተ ርክስትያን ለቤተ ክርስትያን ከአስፍሆተ ወንጌል ተልእኮ ጋር የተቆራኘ ነው በሚል ርእስ ሥር ባሰሙት ንግግር፣ የመገናኛ ብዙኃን በተለይ ደግሞ የማስታወቂያ አቅርቦት የተልእኮ ሥፍራ ናቸው፣ ተልእኮ ግኑኝነት ነው። ማለትም ኃይለኛውን የእግዚአብሔር ቃል የሚስራጭበትና የሚገናኝበት ነው። እንዲህ በመሆኑም በጽሞና መቅድም የተሸኘ መሆን አለበት፣ መልካም ዜና ለሁሉም መዳረስ አለበት። የዓለም ዜና ለሁሉም ለማሰራጨት ከሚደረገው ጥረት በላይ የምሥራቹ ቃል ለሁሉም ለማሰማት የሚደረገው ጥረት አይሎ መገኘት አለበት። የምግብና የውሃ መጠጥ እጥረት መስፋፋት ሲነገር እንሰማለን፣ የእግዚአብሔር ጥማትና እርሃብ ግን ከፍ ብሎ በዓለማችን በስፋት እየታየ መሆኑ መገንዘብ ይኖርብናል ይኸንን ጥማት እና እርሃብ የሚያስወግደውም ከጽሞና የሚመነጨው የምስራጭ ቃል ነው ብለዋል።
All the contents on this site are copyrighted ©.