2012-05-11 15:03:50

ዓለም አቀፍ የካቶሊካዊት እና የአንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን የጋራ ድርገት


እ.ኤ.አ. በ 1969 ዓ.ም. በካቶሊካዊትና በአንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን መካከል ለውህደት ያቀና የጋራ ውይይት ለማነቃቃት ታልሞ የተቋቋመው የዚሁ የሁለቱ አቢያተ ክርስትያን የጋራው ድርገት ሦስተኛው ክፍለ ጉባኤው በሆንግ ኮንግ መካሄዱ የቅድስት መንበር RealAudioMP3 መግለጫ አመለከተ።
ይኽ የዓለም አቀፍ የካቶሊካዊት የአንግሊካዊት አቢያተ ክርስትያን የጋራው ድርገት እ.ኤ.አ. ከግንቦት 4 ቀን እስከ ግንቦት 10 ቀን 2012 ዓ.ም. ስላካሄደው የጋራው ውይይት በማስደገፍ በኒውዝላንድ የአንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሊቀ ጳጳሳት የዚህ ድርገት ረዳት ሊቀ መንበር ክቡር ዳቪድ ሞክሶን ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የዛሬ አንድ ዓመት በፊት በቦሰ ገዳም የተካሄደው የጋራው ጉባኤ የተንጸባረቀበት ይህ የሆንግ ኮንግ ስብሰባ፣ በካቶሊካዊትና በአንግሊካዊት ቤተ ርክስትያን እንዲሁም በምእመናን እና የአቢያተ ክርስትያን ውህደት የሚደረገው የጋራው ጥረት ለሚከታተሉ ተስፈኛ ጉባኤ ነው።
ካቶሊካዊትና አንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን ግብረ ገብ መሠረት በማድረግ መልስ ለመስጠት የሚከተሉት ዘዴ እንዲሁም በሥነ ግብረ ገብ ላይ የጸና ከሁለቱ አቢያተ ክርስትያን የሚሰጠው መልስ አገናኝ የሆነው የጋራ ሥፍራ ለመለየት ጥረት ያደረገ ስብሰባ እንደነበርም ገልጠው፣ የሁለቱ አቢያተ ክርስትያን ምእመናንና አባላት መሠረታውያን መመሪያዎችን በመከተል ግብር ገብ ጥያቄዎች በተመለከተ የሚሰጡት መልስና የሚከተሉት ምርጫ በቋንቋ በአገር በተለያዩ የአጋጣሚ ክስተቶች ምክንያት የሚለያዩ ሳይሆን፣ ሰው ባለው ሰብአዊ መሆን እንዲሁም ያለው ካቶሊካዊ ወይንም አንግሊካዊ አቢያተ ክርስትያን ተከትሎው የሚያስተጋባ መሆን እንዳለበት ያበከረ ጉባኤ ነበር፣ በቻይና በምትገኘው ካቶሊካዊት ሮማዊት ቤተ ክርስትያንና አንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን መካከል የጋራው ግኑኝነት እንዲነቃቃ ያበረታታ መሆኑ ጠቅሰው የሰጡትን ቃለ ምልልስ ሲያጠቃሉ፣ የበርሚንግሃም ሊቅ ጳጳሳት የጋራው ዓለም አቀፍ ድርገት ተባባሪ ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ በርናርድ ሎንግለይ በበኵላቸውም፣ የጋራው ስብሰባ ከመጀመሩ በፊት የእያንዳንዱ ቤተ ክርስትያን ልኡክ የጋራው ድርገት አባል የነበረው ተስፋ ሙሉ በሙሉ ባይባልም በከፊሉ የተረጋገጠበት ጉባኤ ነበር ለማለት ይቻላል፣ ባለፈው ዓመት ከተካሄደው የጋራው ውይይት የተጨበጠው ውጤት በሁለቱ አቢያተ ክርስትያን በተናጥል የተካሄዱት ውይይቶችና ውጤት ላይ በማተኮር እንዲሁም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ያወጁት የእምነት ዓመት፣ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ማእከል ያደረገ እንዲካሄድ የወሰኑት የመላ ካቶሊክዊት ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ በተመለከተ አንግሊካዊት ቤት ክርስትያን ያላት አስተያየት የተደመጠበት እንደነበርም ገልጠው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.