2012-05-02 14:52:33

ዝክረ ዓመት ብፅዕና ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ


እ.ኤ.አ. ግንቦት አንድ ቀን 2011 ዓ.ም. ኵላዊት ቤተ ክርስትያን በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አማካኝነት ር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ ጵውሎስ ዳግማዊ ብፁዕና ያወጀችበት ዕለት መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ትላትና በመላይቱ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን አንደኛው ዝክረ ዓመት ብፅዕና ር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ተከብሮ RealAudioMP3 መዋሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።
እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. “ትውልድ ዎይትይላ” በሚል መጠሪያ የሚታወቁት ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ባነቃቁት ሁሌ በየዓመት በሚከበረው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ይሳተፉ የነበሩት ከወጣትነት የዕድሜ ገደብ የተሸጋገሩት በኢጣሊያ ርእሰ ከተማ ሮማ በሚገኘው ቶር ቨርጋታ እ.ኤ.አ. በ 2000 ዓ.ም. “ቃልም ሥጋ ሆነ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛም አደራ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነውን ክብሩን አየን” (ዮሐ. 1፣ 14) በሚል ቃለ ወንጌል ተመርቶ ተካሂዶ በነበረው 15ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ተሳታፍያን ነበር ወጣቶች ዳግም በመሰባሰብ ለአንደኛው ዓመት ዝክረ ብፅዕና ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ጸሎት ዋዜማ ማቅረባቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።
የጸሎት ዋዜማውን የመሩት የሮማ ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አጎስቲኖ ቫሊኒ መሆናቸውም ሲገለጥ፣ ከወጣቶች ጎን የሚቆም ዘወትር ወጣት ይሆናል በማለት ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግምዊ እ.ኤ.አ. በ 2000 ዓ.ም. በተካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በሰጡት ሥልጣናዊ አስተምህሮ የገለጡት ሃሳብ ኵላዊት ቤተ ክርስትያን ዳግም ህያውነቱ የመሰከረችበት ቀን መሆኑ ብፁዕ ካርዲናል ቫሊኒ በተካሂደው የዋዜማ ጸሎት ባሰሙት ስብከት እንደገለጡ ለማወቅ ተችለዋል።
የሮማ ሰበካ የወጣቶች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ጽሕፈት ቤት ተጠሪ አባ ማውሪዚዮ ሚረሊ ቀኑን ምክንያት በማድረግ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ የጸሎት ዋዜማ እንዲካሄድ ያነቃቁት ትውልድ ዎይትይላ በመባል የሚታወቁት ነበር ወጣቶች ናቸው ካሉ በኋላ መለስ ብለን በቶር ቨርጋታ እ.ኤ.አ. በ 2000 ዓ.ም. በተካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የሰጡት ሥልጣናዊ አስተምህሮ ምዕዳን እና ያሰሙት ስብከት በዚህ በምንኖርበት ዓለም ለሚታየው ዘርፈ ብዙ ቀውስና ሰብአዊ ውጣ ውረድ መልስ ነው። ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ወጣቱ ትውልድ መልካም ከመፈጸም እንዳይታቀብ አደራ በማለት፣ ለማረጋገጥን ካለ መሰላቸት እንዲታገሉ አደራ ያሉት ቃል በወጣቱ ትውልድ ዘንድ ህያውነቱ እየተመሰከረ መሆኑ በዚህ በቶር ቨርጋታ በተሳተፉት ወጣቶች ተመስክሯል።
ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ወጣት ትውልድ ከጌታችን ኢየሱስ ክርቶስ ጋር እንዲገናኝ እንዲጸለይ የሚያነቃቃ፣ የምንኖርበት ዓለም ወደ በለጠው ለመለወጥ የሚያስችል እምቅ ኃይል፣ ንቁ ፍላጎት ያለው በመሆኑ ይኸ እምቅ ኃይል ባክኖ እንዳይቀር የሚያበቃው እውነት፣ መንገድ እና ሕይወትን እንዲከተል እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲከተል የሚደግፍ ኵላዊት ቤተ ክርስትያን በር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ አማካኝነት ያነቃቃቸው መርሃ ግብር ነው ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 23 ቀን እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2013 ዓ.ም. በብራዚል ዲዮ ደ ጃነይሮ ሊካሄድ ተወስኖ ባለው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለመሳተፍ የፓፑዋ አዲሲቷ ጊኒ ወጣቶች በአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የወጣቶች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በሚከታተለው ጽሕፈት ቤት አማካኝነት በመዘጋጀት ላይ መሆናቸው የጽሕፈት ቤቱ ተጠሪ አባ ሻንዚ ፑቱዘርይ የሰጡትን መግለጫ የጠቀሰው ፊደስ የዜና አገልግሎት አመለከተ።
ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን የእምነት ንግደት መሆኑ ያብራሩት አባ ፑቱዘርይ ገልጠው ወጣቱ ትውልድ እምነቱን ጠለቅ በማድረግ እንዲያውቅ በሚያግዝ መርሃ ግብር እንዲሳተፍ ቅዱስ መጽሐፍ እንዲያነብ በቤተ ክርስትያን ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን የሚያነቃቃ ነው እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.