2012-05-02 14:54:27

ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ፦ ለኤውሮጳ መናብርተ ጥበብ “በቅንነት ኢየሱስን ፈልጉ”


በኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት የወጣቶች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ድርገት አማካኝነት የሚያነቃቃው የኤውሮጳ መናብርተ ጥበብ ጉባኤ ዘንድሮ ሁለተኛው ጉባኤ ሮማ አቅራቢያ በሚገኘው በቶር ቨርጋታ መንበረ ጥበብ የጉባኤ አዳራሽ መካሄዱ ሲገለጥ፣ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ RealAudioMP3 ትላትና በጉባኤው መዝጊያው ዕለት ንግግር ማሰማታቸው ሲገለጥ፣ ብፁዕነታቸው ለጉባኤው ፍጻሜ ዕለት ተጋባእያኑ መሥዋዕተ ቅዳሴ አቅርበው ባሰሙት ስብከት፣ በጉባኤ ለተሳተፉት 400 ወጣቶች ምስጋናን አቅርበው፣ ተሳታፊዎች ለቤተ ክርስትያንና ለቤተ ክርስትያን ሥልጣናዊ መሪነት ያላቸውን ቅርበት መመስከራቸው ገልጠው፣ ደስ የሚያሰኝ ምስክርነት ነው እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
በዕለቱ ምንባበ ወንጌል ተንተርሰው ባሰሙት ስብከት እንተ የተባረክ የእግዚአብሔር አብ ልጅ ነህን የሚል ጥያቄ በማቅረብ፣ ሁሉም ይኸንን የአብ ልጅ ለይቶ ለማወቅ ከእርሱ ጋር ለመገናኘት የሚያደርገው ዘርፈ ብዙ ጥረት በግል የሚከናወን ሳይሆን በሚፈለገው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚደገፍም ነው ካሉ በኋላ፣ ወጣቶች በጸረ ባህል ሂደትና ስብከት ሳይታለሉ እውነተኛውን ባህል በመከተል መጠራጠር እና ጠንቅቆ አለ መረዳት ሲያጋጥማችሁም ለሕይወታችሁ መመሪያ የሚሆነው ትምህርት የሚሰጠው የቤተ ክርስትያን ሥልጣናዊ ትምህርት ዋቢ አድርጉ በማለት ካሳሰቡ በኋላ ኢየሱስን በቅንነት እና በትህትና ፈልጉት እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.