2012-04-30 13:59:27

ጳጳሳዊ የማኅበራዊ ሥነ እውቀት ተቋም ምልአተ ጉባኤ


ር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ 23ኛ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ አንድ ቀን 1963 ዓ.ም. “Pacem in Terris - ሰላም በምድር” በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ዓዋዲ መልእክት ማእከል በማድረግ እ.ኤ.አ. ከሚያዝያ 27 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ጳጳሳዊ የማኅበራዊ ስነ እውቀት ተቋም 18ኛው ምልአተ ጉባኤ እያካሄደ መሆኑ ሲገለጥ፣ ይኽ RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ግንቦት 1 ቀን 2012 ዓ.ም. በሚጠቃለለው ምልአተ ጉባኤ፣ በመሳተፍ ላይ የሚግኙት የታላቅዋ ብሪጣንያ የሕዝብ ተመራጮች ምክር ቤት አባል ዳቪድ አልቶን ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ “Pacem in Terris - ሰላም በምድር” የተሰየመው የር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ 23ኛ አዋዲ መልእክት ቃለ ኑዛዜ በቀጥታ የእሳቸው የእምነትና የሕይወት ገጠመኝ ገና ር.ሊ.ጳ. ሆነው ከመሾማቸው በፊት በቡልጋርያ ቀጥለውም በቱርክ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ በመሆን የሰጡት አገልግሎት፣ በናዚው ሥርዓት ወቅት ብዙ የአይሁድ እምነት ተከታዮች ከሞት ለማዳን ወደ እስራኤል እንዲሄድ የሰጡት አስተዋጽኦ፣ ብዙ አርመናውያን ይደርስባቸው ከነበረው ጅምላዊ ጭፍጨፋ ለማዳንም የሰጡት “ሁሉም በእግዚአብሔር አርአያና አምሳያ ተፈጠረ” የሚለው ቲዮሎጊያዊና ክርስትያናዊ ስነ ሰብእ ጥናት መሠረት ያደረገ እምነትን በቃልና በሕይወት ከመኖር ገጠመኝ የመነጨ ነው። የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ መሠረት ያስያዘ፣ በማንም የማይታበለውና በሰው ልጅ ሰብአዊ መሆን ዘንድ የታተመው መብትና ክብር የሰላም መሠረት መሆኑ ያብራራ ዓዋዲ መልእክት፣ ወቅታዊነቱ የሚመሰክር ምልአተ ጉባኤ ነው ብለዋል።
በመካሄድ ላይ ባለው ጉባኤ “Pacem in Terris - ሰላም በምድር” ዓዋዲ መልእክት ትግባሬው በተመለከተ ዓዋዲ መልእክቱ በእለታዊ ዘርፈ ብዙ ኑሮ ማመላከት በሚል ርእስ ሥር ንግግር ማሰምታቸው ሲገለጥ፣ የምንኖርበት ዓለም የእኔ የአንተ እውነት የተሞላው በመሆኑ በሰዎች ዘንድ የጋራ አካፋይ የሆነው ፍጹም እውነት የተዘነጋ ነው። የሚመስለው፣ ለምሳሌ አትግደል የሚለው ስድስተኛው ትእዛዝ፣ ድርድር የሚደረግበት ወይንም ክለሳ የሚያስፈልገው አይደለም አትግደል እንደየ ሁኔታ የሚተረጎምና አዛብቶ የሚኖር ትእዛዝ አይደለም፣ ትላትና ዛሬም ነገም የማይቀየር ትእዛዝ ነው። ስለዚህ በዓለማችን የሚታየው የሞት ባህል የዚህ ትእዛዝ ጸር ነው። በድኽነት በምግብ እጥረት ጽንስ በማስወረደ በሞት ፍርድ ወዘተ በመሳሰሉት የጸረ ሕይወት ተግባሮች አማካኝነት በዓለማችን የሚፈጸመው የቅትለት ተግባር በሕይወት ባህል መቃወም ይገባል፣ ቤተ ክርስትያን የፖለቲካ ሥልጣን አይደለችም፣ ሆኖም ግን ለትውልድ መሠረታዊ ደንብ በማስተላለፈ በኅብረተሰብ የምትሰጠው አስተዋጽኦ ወሳኝ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.