2012-04-25 14:10:41

ታላቋ ብሪጣንያ


ከትላትና በስትያ በሊድስ በታላቋ ብሪጣንያ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮ መኒኒ ባሰሙት የሰላምታ መልእክት የታላቋ ብሪጣንያና የወይልስ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት RealAudioMP3 ምሥጢረ ተክሊል፣ የኵላዊት ቤተ ክርስትያን የእምነት ዓመት አዋጅ፣ ጥሪና በአገሪቱ ሊካሄድ የተወሰነው ዓለም አቀፍ የኦሎምፒክ ስፖርት ውድድር ርእስ ያደረገ ጉባኤ መጀመሩ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
ሲር የዜና አገልግሎት እንዳመለከተውም የእንግልጣርና ወይልስ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 6 ቀን እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2012 ዓ.ም. በቢርሚንግሃም፣ ጥሪ በሚል ርእሰ ጉዳይ የተመራ ዓወደ ጥናት ለማካሄድ መርሃ ግብር መወጠኑ ሲታወቅ። ቤተ ክርስትያን በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል የሚጸናው ጋብቻ እርሱም በምሥጢረ ተክሊል ለሚጸናውን በመከላከል በአንድ ዓይነት ጾታ ባላቸው ሰዎች መካከል የሚፈጸመው ጋብቻ ሕጋዊነቱን ለማረጋገጥም የአገሪቱ መራሔ መንግሥት ዳቪድ ካመሮን ንድፈ ሕግ ለማቅረብ እቅድ እንዳላቸው ለገለጡት ሃሳብ ከወዲሁ መልስ እንደሚሆንም ሲር የዜና አገልግሎት ካሰራጨው የዜና ምንጭ ለመረዳት ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.