2012-04-25 14:03:08

ሰባተኛው የጎብኚዎች መስህብ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ጉባኤ


የስደተኞች እና የተጓዦች ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ከመክሲኮ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሰባተኛው የጎብኚዎች መስህብ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ጉባኤ በመክሲኮ ካንኩን ከተማ እ.ኤ.አ. ከሚያዝያ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ እየተካሄደ መሆኑ ሲገለጥ፣ በዚህ RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 27 ቀን 2012 ዓ.ም. በሚጠቃለለው ዓለም አቀፍ ሰባተኛው የጎብኝዎች መስህብ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ጉባኤ ከአርባ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች የተወጣጡ የጎብኚዎችና የጎብኝዎች መስህብ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ድርገት ሊቀ መናብርት የተለያዩ የካቶሊክ የጎብኚዎች መስህብ አገልግሎት መስጫ ማኅበሮች የተወጣጡ ልኡካን በጠቅላላ 200 ተጋባእያን በመሳተፍ ላይ መሆናቸውም ለማወቅ ሲቻል፣ ጉባኤው በትላንትና ውሎው ሃይማኖታዊ መስህብነትና መንፈሳዊ ንግደት መካከል ያለው ጥልቅ ልዩነት የሚገልጥ ሰፊ ውይይት ማካሄዱ የጠቀሰው የቅድስት መንበር መግለጫ፣ የስደተኞችና ተጓዦች ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል አንቶኒዮ ማሪያ ቨሊዮ የጎብኝዎች መስህብነት ጥሪ ባላቸው አገሮች የሚገኙት ሰበካዎች፣ የጎብኝዎች መስህብ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ማረጋገጥ በዚሁ ሐዋርያዊ አገልግሎት ብቃታቸውንም ማሳየል ብቻ ሳይሆን፣ “የጎብኘዎች መስህብ መለያ” በሚል ርእስ ሥር በመካሄድ ላይ ባለው ጉባኤ ሃይማኖታዊ መስህብነት እና መንፈሳዊና መንፈሳዊ ንግደት መካከል ያለው ልዩነት በጥልቀት በማጤን ልዩነቱ መሠረት የኵላዊት ቤተ ክርስትያን የማኅበራዊ ጉዳይ የሚመለከተው አንቀጸ ሃይማኖት ትምህርት፣ የስደተኞች እና የተጓዦች ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት መመሪያዎች የቤተ ክርስትያን ሥልጣናዊ ትምህርት ሥር የሚመራ በማድረግ ተገቢ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መወጠን ይጠበቅባቸዋል እንዳሉ አመለከተ። ኵላዊት ቤተ ክርስትያን የዕረፍት ጊዜ የሰብአዊ መብት እና ክብር ጥያቄ መሆኑ በማመን ኵላዊነቱን በማስተማር የዚህ ሰብአዊ መብትና ክብር ጠበቃ መሆንዋ ትመሠክራለች። የዕረፍት ጊዜ ባህላዊ ጉዞና ወይንም ከውጣ ውረድ ገዛ እራስን አግሎ እፎይ ለማለት የሚያገለግል ነው፣ የጎብኚዎች መስህቦ ባህል ተገልጋይ የደላው በሃብት ለታደለ ዜጋ የተለየ ዕድል መሆኑ ቀርቶ ተለውጦ በተለያየ ዘዴ በመደራጀት ሁሉንም በማሳተፍ ሂደት እያደገ መጥተዋል።
መዘንጋት የሌለበት የጎብኘዎች መስህብ ካለው አወንታዊ ገጽታ ውጭ በአሁኑ ሰዓት ጾታዊ ስሜት ላይ ያተኮረ የጎብኚዎች መስህብነት እየተስፋፋ መሆኑና ይኽ ከሩካቤ ሥጋ ጋር የተያያዘ ጸያፍ ኢሰብአዊ ተግባር በተለያየ ክልል በተለይ ደግሞ በማደግ ላይ በሚገኙት አገሮች ላይ ተነጣጥሮ እግብር ላይ እየዋለ ሲሆን ይኽ ጸያፍ ኢግብረ ገባዊ ተባር የሚኮነን ብቻ ሳይሆን ተገቢ ቁጥጥር የሚያሻውና ፈጽሞ እንዳይኖር የማድረጉ ጥረት መሥፋፋት አለበት። ቤተ ክርስትያን ይኸንን ሁሉ እግምት ውስጥ በማስገባት በቤተ ክርስትያን ሥልጣናዊ ትምህርት መሠረት በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ሥር በማስቀመጥ ተገቢ አገልግሎት በመስጠት ለሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ እያገለገለች ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
የስደተኞችና የተጓዦች ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ አባ ጋብሬለ በንቶሊዮ፣ ከዚህ ሰባተኛው ዓለም አቀፍ የጎብኚዎች መስህብ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ጉባኤ በፊት የተካሄዱት ጉባኤዎች መለስ ብለው በመዳሰስ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለዚህ ሰባተኛው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ባስተላለፉት መልእክት እንዳመለከቱት የጎብኚዎች መስህብ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የጎብኚዎች መስህብ ባህል ጠቅላለል ባለ መልኩ፣ ሃይማኖታዊ የጎብኚዎች መስህብ፣ ክርስትያናዊ የጎብኚዎች መስህብ፣ በማለት በሦስት ደረጃ በመከፋፈል የሰጡት ንባብ ለጎብኚዎች መስህብ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መሠረት ነው። ቅዱስ አባታችን የገለጡት ሃሳብ በሃይማኖታዊ ጎብኚዎች መስህብና በመንፈሳዊ ንግደት መካከል ልዩነት እንዳለ የሚያመለክትም ነው። ምክንያቱም ለጉብኝትና ለንግደት የሚገፋፋው የውስጣዊ አመክንዮ ስሜት የሚመለከት በመሆኑ ያለው ልዩነት ረቂቅ ነው ካሉ በኋላ፣ ለጉብኝት የሚገፋፋ ምክንያት ከሰብአዊ መብትና ክብር ጋር የተስተካከለ መሆን አለበት እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.