2012-04-02 15:14:42

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ “ሁሉ ጊዜ ደስ ይበላችሁ”።


“የጌታ በመሆናችሁ ሁሉ ጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜም የምላችሁ ‘ደስ ይበላችሁ’ ነው” (ፊሊ. 4፤4)። የላቲን ሥርዓት በምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን በየዓመቱ በሚከበረው በዓለ ሆሳዕና በሁሉም አገሮች በሚገኙት ሰበካዎች በብሔራዊ አቀፍ ደረጃ የወጣቶች ቀን ተያይዞ የሚከበር ሲሆን RealAudioMP3 ፣ በዚሁ ዕለት ምክንያት የሮማ ሰበካ በጳጳሳዊ ቅዱስ ዮሓንስ ዘ ላተራኖ ባዚሊካ በታይዘ የሁሉም ኃይማኖት የውህደት ማኅበረሰብ ወንድሞች ተነቃቅቶ በተመራው መንፈሳዊ መርሃ ግብር እንዲሁም የሮማ ሰበካ ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አጎስቲኖ ቫሊኒ ትምህርተ ክርስቶስ ባቀረቡበት የዋዜማ ጸሎት፣ ቅዱስ አባታችን ለዚህ ብሔራዊ የወጣቶች ቀን ቅዱስ ጳውሎስ ለፊሊጵስዩስ በጻፋት መልእክት ምዕ. 4 ቍ. 4 “የጌታ በመሆናችሁ ሁሉ ጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜም የምላችሁ ‘ደስ ይበላችሁ’ ነው” በሚለው ቃለ እንዲመራ የሰጡት ውሳኔ መሠረት በማድረግ፣ ምንም’ኳ ዕለታዊ ሕይወታችን በተለያዩ ችግሮች የተወጠረ የነገው ሕይወት ጨለማ ቢያስመስለውና በርግጥ ችግሩ ከባድ ቢሆንም እውነተኛው ደስታ የሚሰጠው እውነተኛው ደስታች ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው ሲሉ በመቀጠል በተካሄደው የዋዜማ ጸሎት፣ አስተንትኖ ያቀረቡት የታይዘ ማኅበረሰብ አባል ወንድም ዳቪደ፣ በመዝሙር መጸለይ ማስተንተን በቅዱስ ቁርባን ኅያው በሆነው በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ወጣቱ ትውልድ እንደ አንድ ቤተሰብ በመታቀፍ በማስተንተን በጌታ ደስ እደሚለን ደስታችንም እርሱ ብቻ ነው ሲሉ፣ በሚያጋጥም ችግር የማይወሰነውን የወንጌል ደስታ ለመመስከር የሚያነቃቃ መሆኑም በተካሄደው የዋዜማ ጸሎት ስብከት ያሰሙት ወንድም ማረክ ማብራራታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.