2012-03-22 09:56:17

ኤውሮጳዊ-እስያ አገሮች ኅብረት ምሥረታ በእቅድ


በቀድሞ የሶቪየት ኅብርት አገሮች መካከል ኤኮኖሚያው ውኅደት ለማረጋገጥ ያለመ የኤውሮጳ ኅብረት አገሮች ማኅበር ተምሳሌት ያለው ኤውሮጳዊ-እስያ አገሮች ኅብረት እ.ኤ.አ. እስከ 2015 ዓ.ም. ባለው የአመታት ገደብ ውስጥ እንዲቋቋም በክረምሊን የኤውሮጳዊ እስያ አገሮች የኤኮኖሚ ማኅበረሰብ ባካሄደው ጉባኤ ንግግር ያሰሙት የርእሰ ብሔር ሥልጣን ተልእኮአቸው እያበቃ ያለው የፈደራላዊት ሩሲያ ርእሰ ብሔር መድቨደቭ ሃሳብ ማቅረባቸው ሲገለጥ፣ እቅዱ እግብር ላይ ለማዋል በሚደረገው ሂደት ኡክራይን በታዛቢነት መብት ለመሳተፍ እቅድ እንዳላት ከወዲሁ በማሳወቅ፣ በታቀደው ኤውሮጳዊ-እስያ አገሮች ኅብረት ምሥረታ ላይ እምብዛም እማኔ የሌላት መሆኑ ገሃድ አድርጋለች።
ኤውሮጳዊ-እስያ አገሮች ማኅበር እ.ኤ.አ. ጥሪ 2015 ዓ.ም. እውን የሚሆንበት ቀን ይሆናል ተብሎ ሲነገር፣ በዚህ እ.ኤ.አ. በ 1996 ዓ.ም. በተመሠረተው ሩሲያ በይሎሩሲያ ካዛክህስታን ኪርጊዚስታን እና ታጊኪስታን በአባላነት አርመኒያ ማልዲቭ እና ኡክራይን በታዛቢነት የሚያቅፈው ኤውሮጳዊ-እስያ አገሮች የኤኮኖሚ ማኅበረሰብ አባል አገሮች በክረምሊን እያካሄዱት ባለው ጉባኤ የሩሲያው ርእሰ ብሔር መድቨደቭ የኤውሮጳ ኅብረት አገሮች ማኅበር ተምሳሌነት መሠረት እንዲቋቋም ያሳሰቡት ኤውሮጳዊ-እስያ አገሮች ማኅበር በሩሲያ በተካሄደው የርእሰ ብሔር ምርጫ ያሸነፉት የወቅቱ የሩሲያ መራሔ መንግሥት ፑቲን ተቀዳሚ ዓላማ በማድረግ በምርጫ ዘመቻ ወቅት ብዙ ማብራሪያ የሰጡበት ርእስ ሆኖ መቆየቱም የሚታወስ ሲሆን፣ የቅድሞ ሶቪየት ኅብረት አነስተኛ ተምሳል ሊሆን እንደሚችልም ይነገርለታል።
የሩሲያ ኤኮኖሚ እና የኃይል ምንጭ ሃብት ጉዳይ ሊቅ ኤቭገንይ ኡትኪን ስለ ጉዳዩ በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ እ.ኤ.አ. ከጥር 2012 ዓ.ም. ጀምሮ በሩሲያ በይሎሩሲያ ካዛክህስታን መካከል የጸናው ነጻ የኤኮኖሚው ማኅበረሰብ በአባል አገሮች ከፍ ለማድረግ ያቀደ ቢመስልም ቅሉ ፖለቲካዊ እቅድ ያለው ይመስላል፣ ብዙ የቀድሞ ሶቪየት ኅበርት አባል አገሮች ከዚያ ነበር ኅበረት መገንጠል ወዲህ ከኤውሮጳ ጋር ቅርበት ካላቸው የባልካን አገሮች በስተቀረ ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጠው ይገኛሉ ስለዚህ ከዚህ አኳያ ሲታይ ውህደቱ የሚደግፉት ይሆናል ለማለት ይቻላል። ይህ የሚባለው ኅብረት ከተረጋገጠ እና ወደ ሻንጋይ ቡድን አገሮች ቻይናንም ጭምር በአባልነት ለማቀፍ ያለው ፍላጎት ከተረጋገጠ፣ በአለም ዓቀፍ ደረጃ አቢይ ለውጥ የሚያስገባ ከመሆኑም ባሻገር፣ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት እና በኤውሮጳ ያለው ኤኮኖሚው ሃብት ማሽቆልቆል ኤውሮጳዊ-እስያ አገሮች ኅበረት በዓለም የሥነ መሬት አቀማመጥ ፖለቲካና ኤኮኖሚ አቢይ ተጽእኖ እንዲኖረው ያግዛል፣ ሆኖም የኤውሮጳ ኅብረት አገሮች ለመመሥረት የጠየቀው ረዥም ዓመታት በመመልከትት ኤውሮጳዊ-እስያ አገሮች ኅብረት እ.ኤ.አ. ጥሪ 2015 ዓ.ም. እውን ይሆናል ብሎ ለመናገር ያዳግታል በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.