Home Archivio
2012-03-22 09:50:52
ቪየትናም፦ ነፍሰ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ቫን ቷን
እ.ኤ.አ. በ 2002 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የፍትህና ሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር በመሆን ያገለገሉት የቨትናም ተወላጅ ብፁዕ ካርዲናል ፍራንሲስ ሳቪየር ንጉየን ቫን ቷን ብፅዕና እንዲታወጅላቸው ጥናቱን የሚያካሂደው የሮማ ሰበካ የመለመለው ድርገት የተለያዩ ምስክርነቶችን ለማሰባሰብ በፈረንሳይ ጀርመን የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት እና ኦስትሪያ ቆይታ ማድረጉ የሚዘከር ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. ነገ መጋቢት 23 ቀን 2012 ወደ ቨትናም እንደሚነሳ የገለጠው ከሮማ ሰበካ የተሰጠው መግለጫ አክሎ፣ በዚህ እ.ኤ.አ. እስከ ሚያዝያ 9 ቀን 2012 ዓ.ም. በሚጠቃለለው ቆይታ የተለያዩ ምስክርነቶች እና ሰነዶችን እንደሚያሰባስብ አስታውቀዋል።
ይህ የሮማ ሰበካ ስለ ብፅዕና ካርዲናል ቫን ቷን ጥናት በማካሄድ ስነዳቱን የቅድስና ጉዳይ ለሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር የሚያስረክበው ድርገት በዚህ በቨትናም ቆይታው እ.ኤ.አ. ከመጋቢት 24 ቀን እስከ መጋቢት 27 ቀን 2012 ዓ.ም. ነፍሰ ኄር የዛሬ 37 ዓመት በፊት ባገለገሉባት በጥንታዊት ሳይጎን በአገሪቱ መንግሥት አለ ምንም ክስ እ.ኤ.አ. በ1988 የቁም እሥረኛ እንዲሆኑ በበየነባት፣ በመንግሥት ከተባረሩባት በ1991 ዓ.ም. አገራቸው ትተው እስከ ተሰደዱበት ወቅት በቁም እስራኛነት ቆይታ ባደረጉባት በሆ ቺ ሚን ከተማ ቆይታ የሚያደርግ ሲሆን፣ የድርገቱ በዚያች ከተማ መገኘት በአገሪቱ ያለው ሥርዓት ደስ እንዳላሰኘው የገለጠው ኤግሊሰስ ዲ አስየ የዜና አግልግሎት አክሎ፣ ድርገቱ በመቀጠል እ.ኤ.አ. ከመጋቢት 28 ቀን እስከ መጋቢት 31 ቀን 2012 ዓ.ም. ነፍሰ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ቫን ቷንን በቅርብ የሚያውቅዋቸው በሚገኙበት እ.ኤ.አ. ከ 1967 ዓ.ም. እስከ 1975 ዓ.ም. ሐዋርያዊ አገልግሎት በሰጡበት በንሃ ትራንግ ሰበካ ቆይታ በማድረግ ቀጥሎ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 1 ቀን 2012 ዓ.ም. ነፍሰ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ቫን ቷን እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 17 ቀን 1928 ዓ.ም. በተወለዱባት ሁዌ ከተማ በመዛወር የሕይወታቸውና የቤተሰቦቻቸው በጠቅላላ የወላጆቻቸው ታሪክ ቀርቦ ለማጥናት ደግሞ የሳቸው መንፈሳዊ ልጆች ከሚባሉት ውስጥ በእድሜ በገፉት በክልሉ ከሚገኙት አንዳንድ ካህናት፣ ገዳማውያን እና እሳቸው በመሠረቱት ተስፋ የተሰየመው የሐዋርያዊ አገልግሎት ማኅበር አባላት ጋር ግኑኝነት በማካሄድ ቀጥሎ እ.ኤ.አ. ከሚያዝያ 5 ቀን እስከ ሚያዝያ 7 ቀን 2012 ዓ.ም. ቆይታ ወደ ሚያደርግባት ሃኖይ ከተማ በመዛወር ነፍሰ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ቫን ቷን እሥረኛ በነበሩበት ወቅት የተዋወቁዋቸው የቀድሞ እስረኞች የቨትናም ዜጎች ጋር በመገናኘት እና መረጃዎች እና ምስክርነት ካሰባሰበ በኋላ ወደ ሮማ እንደሚመለስ አስታውቀዋል፣
ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ነፍሰ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ቫን ቷን እ.ኤ.አ. በ 1998 ዓ.ም. የፍትሕ እና ሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር እንዲሆኑ ሹመዋቸው እ.ኤ.አ. በ 2001 ዓ.ም. ለካርዲናልነት ማእርግ ከፍ እንዳደረጉዋቸው የሚዘከር ሲሆን። የሮማ ሰበካ ነፍሰ ኄር ብፁዕ ክካዲናል ቫን ቷን ብፅዕና እንዲታወጅላቸው መረጃዎች እና ምስክርነት የሚያሰባስብ ድርገት እ.ኤ.አ. ጥቅምት 22 ቀን 2010 ዓ.ም. መመልመሉም ይታወሳል።
All the contents on this site are copyrighted ©.