2012-02-24 13:54:08

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የአቢይ ጾም መልእክቶች በትዊት የማኅበራዊ ድረ ገጽ


የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በዚህ ዓቢይ ጾም ምክንያት በየእሁዱ ጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ የሚያቀርቡት ሥልጣናዊ ስብከት በ40 ሥልጣናዊ ቃለ ስብከት ተከፋፍሎ ትዊተት በተሰየመው ማኅበራዊ ድረ ገጽ አማካኝነት እንደሚሰራጭ የመገናኛ ብዙኃን RealAudioMP3 ጉዳይ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ትላትና ከሰጠው መግለጫ ለመረዳት ሲቻል፣ ከትላትና ጀምሮ ይህ እቅድ በ “Pope2you” በተሰየመይ የማኅበራዊ ድረ ገጽ አድራሻ አማካኝነት እየቀረበ መሆኑም ጳጳሳዊው ምክር ቤት ትላትና በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በተግባር አቅርበዋል።
“Pope2you” የተሰየመው ለወጣት የኅብረተሰብ ክፍል ያቀናው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የማኅበራዊ ድረ ገጽ አድራሻ በብዙ ሺሕ በሚገመቱት ወጣቶች የሚጎበኝ መሆኑ የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ክላውዲዮ ማሪያ ቸሊ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ አሁን ደግሞ በትዊተር አማካኝነት የቅዱስ አብታችን መልእክቶች ለሁሉም ለማቅረብ በሚል ውሳኔ መሠረት በውሁድ ልብ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ትብብር አማካኝነት በሥፋት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ መልእክት ለወጣት ኅብረተሰብ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ለማኅበራዊ ድረ ገጽ ተጠቃሚዎች ለማቅረብ ታቅዶ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፈቃድ ይኸው እግብር ላይ ውሎአል ካሉ በኋላ ለወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍል አፍቃሪ የሆኑትን ቅዱስ አባታችን ከወጣት ኅብረተሰብ ጋር በጥልቀት ለማስተዋወቅና ኩላዊ አስተምህሮቻቸውን ለሁሉም ለማሳወቅ ነው ብለዋል።
በተራቀቀው የመገናኛ ብዙኃን ሥልት አማካኝነት ለሁሉም ሰው ዘር ቅርብ ለመሆን ለሚሹት ቅዱስ አባታችን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማንንም የማያገል ጥልቅ ፍቅሩና የሚያበራ እውነተኛ ብርኑን ግልጽ ለማድረግ እና ኢየሱስ በክርስትያኖች ብቻ ሳይሆን በሁሉም ዘንድ እንዲታወቅ የሚሰጡት ምዕዳን እና እስተምህሮ ለሁሉም እንዲዳረስ የቢያበቃ አዲስ እቅድ ነው ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.