2012-02-20 15:06:30

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ “ባለንጀራህን እንደ ገዛ እራስህ ማፍቀር እንዳይቻል የሚያደርገው ምንድን ነው?”


እ.ኤ.አ 2012 ዓ.ም. ዓቢይ ጾም ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ያስተላለፉት ዓለም አቀፍ የዓቢይ ጾም መልእክት፣ ባለንጀራህን እንደ ገዛ እራስህ ለማፍቅር የሚያሰናክለው ምን ይሆን RealAudioMP3 ሲሉ ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት በዓለማችን እየተስፋፋ ያለው እኔነትን ለሚለው ስስታም ባህል የቀሰረ ሆኖ፣ ለዚህ ባህል እምቢ የሚሉ ሰዎች እና ቤተሰቦች ለሌሎች በማሰብ፣ ባላቸው ኤኮኖሚያዊ እና የጊዜ አቅም ሰለ ሌሎች የሚያስቡ ትብብር እና መደጋገፍን የሚያስቀድሙ እንዳሉ ማስታወሳቸውም የሚዘከር ሲሆን፣ ይኸ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መልእክት ምክንያት በማድረግ የኢጣሊያ የትብብር ማኅበር አባል ዳኔኤላ ፎርቲኒ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በቅርቡ በዓቢይ ጾም ምክንያት ወደ ደቡብ ሱዳን ለድጋፍ እና ትብብር እቅድ እንደሚነሱ ገልጠው፣ በአባ አንጀሎ በኖሊ በሮማ የተቋቋመው የድጋፍ እና ትብብር ማኅበር በተለያዩ 110 አገሮች አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ዘክረው፣ በዚያች የተወሳሰበ ችግር በተፈራረቀበት በሽግግር ወቅት በምትገኘው ደቡብ ሱዳን ለአገልግሎት እንደሚላኩ ገልጠው በዚህ እቅድ መሠረትም በችግር እና በሥቃይ ለሚገኘው ሰው አለ መተባበር ለሚያጋጥመው ችግር ተጠያቂ ያደርጋል።
ባለ እንጀራህን እንደ ገዛ እራስህ ማፍቀር የክርስትያን መሠረታዊ ጥሪ ነው። ከዚህ ጥሪ ውጭ የሚኖር ክርስትና የለም፣ ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር መመዘኛው እንደ ገዛ እራሳችን ለባለንጀራችን ያለን ፍቅር ነው። ይህ መመዘኛ ኢየሱስ የሰጠው እንጂ በሌላና በማንም የተሰጠ አይደለም። ስለዚህ በዚህ ቃል በመመራትንም በኢጣልያ እና ከኢጣልያ ውጭ በበጎ ፈቃደኛነት በመደራጀት በዚህ ማኅበርም በመታቀፍ ክርስቶስ ማእከል ያደረገ የትብብርና የድጋፍ አገልግሎት እንሰጣለን ለዚህ ዓለማም ወደ ደቡብ ሱዳን በመሄድ ለዚያ በሽግግር ለምትገኘው አገር ሕዝብ ሰብአዊ ደጋፍ ለማቅረብ እንደሚሄዱ ገልጠው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.