2012-02-18 09:17:06

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በሮማ አቢይ የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት ሓዋርያዊ ጉብኝት ፈጸሙ
“ምንም’ኳ የቁጠባ እና የመገናኛ ብዙኃን ሥልጣን አስፈላጊ ቢሆንም ቅሉ አደገኛ የሰውን ልጅ የሚጨቁን ሥልጣን ሊሆን ስለሚችል፣ ከዚህ ሥልጣን ጋር ተመሳስሎ ከመኖር ምርጫ ተቆጠቡ”።


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ከትላትና በስትያ ዓመታዊ የሮማ ዓቢይ የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት ጠባቂ ታማኚቷ እመቤት በዓል ምክንያት ሮማ በቫቲካን ራስ ገዛዊ ክልል በሚገኘው አቢይ ሮማዊ የዘረአ ክህነት ትምህርት ቤት ሐዋርያዊ ጉብኝት ማከናወናቸው ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን RealAudioMP3 በዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት እንደደረሱ በትምህርት ቤቱ ጠቅላይ አለቃ፣ በአበ ነፍስ በዘረአ ክህነት ተማሪዎች የሞቀ ውሉዳዊ አቀባበል ተደርጎላቸው የእንኳን ደህና መጡ መልእክቶችና መንፈሳዊ መዝሙሮች ከተደመጡ በኋላ ቅዱስነታቸው አስከትለው ሥልጣናዊ አስተምህሮ መለገሳቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
በአሁኑ ወቅት የቁጠባው ዓለም የጋራ ጥቅም እና የሰብአዊ መብት ክብር እና ፈቃድ እንክብካቤ ለማረጋገጥ የሚደግፍ እና ለዚህ ዓላማ የሚውል መሣሪያ ከመሆን ይልቅ፣ ጨቋኝ ሥልጣን ሆኖ ልክ እንደ ጣዖት የሚመለክ በእውነት “የሐሰት መለኰት” ሆኖ ዓለምን በሞላ የሚወር እየሆነ ነው። የዚህ ሥልጣን ተገዥ እንድትሆን ከሚገፋፋው ልደር ባይነትና አስመሳይነት ከሚኖር ሕይወት ተቆጠቡ። ግድ የሚባለውና የሚፈለገውም ያለህ ሳይሆን መሆንህ ነው። ስለዚህ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችን በሚያሰጠን ነጻነተ መሠረት ቁጠባም ሆነ የመገናኛ ብዙኃን ልንጠቀምበት እንጂ የዚህ ሥልጣን ተገዥ መሆን አይግባም ብለዋል።
አስመሳይነት እና ልደር ባይነት የማይል ክርስትና ያድናል፣ እውነትን ያስጨብጣል፣ ለእውነትን ያስረክባል፣ እግዚአብሔር ልመሳሳል ተመሳስየ ልደር የማይሉትን፣ ይህ ማለት ደግሞ የምንኖርበት በእግዚአብሔር የተፈጠረው ዓለም መቃወም ማለት ሳይሆን፣ ዓለምን በእውነት ልናፈቅራት የሚያበቃን በዓለም እንጂ የዓለም አይደላችሁም ከሚለው ቃል የሚገኘው ኃይል እንዲጸገውን እንለምነው።
በአሁኑ ሰዓት ስለ ሮማዊት ቤተ ክርስትያን ብዙ ሲባል እና ሲነገር እንሰማለን፣ ስለ ሮማዊት ቤተ ክርስትያን እምነት እንዲናገሩ ተስፋ እናደርጋለን። አመለካከታችን፣ አስተሳሰባችን ብቻ ሳይሆን መላ ሕይወታችን ሊጡርጊያ እና አምልኮ እንዲሆን በእግዚአብሔር እውነት ሁለ መናችን ሊነካ ይገባዋል፣ በማለት ያቀረቡት ሥልጣናዊ አስተምህሮ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.