2012-02-18 09:21:25

መነሻው ምኅረተ አብ የሚያደርግ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ማነቃቃት


የካፑቺን ንኡሳን ወንድሞች ማኅበር ጠቅላይ መሥተዳድር ያነቃቃው “የንስሐ ምሥጢር ‘የእርቅ ቅዱስ ምሥጢር’ እና አዲስ አስፍሆተ ወንጌል፣ ለውሉደ ክህነት የአስተንትኖ እና የሕንጸት ጊዜ” በሚል ርእስ ተመርቶ በኢጣሊያ ሳን ጆቫኒ ሮቶንዶ ከተማ በመካሄድ ላይ ያለው ዓለም አቀፍ የእርቅና ምኅረት ሁለተኛው ሳምንት በማስመልከት በዓለም አቀፉ ጉባኤ አስተምህሮ የሚያቀርቡት የአለቲ ማእከል፦ እርሱም የዚህ RealAudioMP3 የኢየሱሳውያን ማህበር ለጳጳሳዊ የምሥራቅ አቢያተ ክርስያን ተቋም አገልግሎት የሚሰጥ ማእከል ሲሆን፣ የዚህ ማእከል አስተዳዳሪ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል ኣባ ማርኮ ኢቫን ሩፕኒክ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ምሥጢረ ንስሓ ለገዛ እራሱ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ማለት ነው። ኤውሮጳና ኤውሮጳውያን ከክርስቶስ ካልተወለዱ በስተቀረ የኤውሮጳም ሆነ የኤውሮጳውያን ኅዳሴ ይኖራል ማለት አይቻልም። ምሥጢረ ንስሐ ወደ አብ እንድንመለስ የሚያበቃን ጸጋ የምንታደልበት ቅዱስ ምሥጢር ነው፣ በመታደስ ብቻ ነው ለሌሎች በመታደስ ላይ ያለው ውበት ልንመሰክር የምንችለው።
ዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ወይንም አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ክርስትያን ወደ ክርስቶስ በበለጠ ቅርብ እንዲሆን የሚያደረግ ከክርስቶስ ጋር ያለው መቀራረብ ከፍ የሚያደርግ በልምድ ከሚኖር ክርስትና ሕይወት ነጻ የሚያወጣ ነው። ስለዚህ ምሥጢረ ንስሐ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደም መታጠብ ማለት ሲሆን። በመኃሪው አብ ምኅረት አግኝነት እኛም የዚህ ምኅረት ተካፋዮች ሆነን መኃሪዎች እንድንሆን ተጠርተናል። የአብ ምኅረት ያላጣጣመ በእውነት ምኅረት ምን ማለት መሆኑ ሊገነዘብ አይችልም።
የአስፍሆተ ወንጌል ጎዳናዎች እልፍ አእላፍ ናቸው። መሠረቱ ግን በክርስቶስ የተገለጠው የእግዚአብሔር ፍቅር ነው። ይኽ ፍቅር የሕይወታችን የዕለታዊ ኑሮአችን ግኑኝነታችን በጠቅላላ የመላ ሕይወታችን ሚዛን መሆን አለበት፣ በዚህ ፍቅር ገዛ እራሳችንን እየመዘንን ዕለታዊ ኑሮአችን የምንመራ ከሆን በርግጥ በአስፍሆተ ወንጌል እየኖርን ዳግመ አስፍሆተ ወንጌል እንፈጽማለን ማለት ነው ሲሉ የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.