2012-02-04 10:17:35

በአቱ ለእግዚእነ
አመታዊ የምንኩስና ሕይወት በዓል


ትላትና በላቲን ሥርዓተ የአምልኮ ግፃዌ መሠረት በዓለ በአቱ ለእግዚእነ ተከብሮ መዋሉ ሲታወቅ፣ ከዚህ ዕለት ጋር በማያያዝም ር.ሊጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ኵላዊት ቤተ ክርስትያን የምንኩስና ሕይወት ቀን እንድታከብር በሰጡት ውሳኔ መሠረት ይኸው ትላትና 16ኛው የምኩስና ሕይወት RealAudioMP3 ቀን ታስቦ ውሎአል። ይኸንን ድርብ በዓል ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በኋላ ልክ 11 ሰዓት ተኩል በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ መሥዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታውቀ።
የመናንያን ሕይወት እና የሐዋርያዊ አገልግሎት ማኅበሮች የሚንከባከብ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ዦዋው ብራዝ ደ አቪዝ ቀኑን ምክንያት በማድረግ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ዕለቱ ለምንኩስና ሕይወት የተጠሩት ለየት ያለ መንፈሳዊ ቤተ ክርስትያናዊ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ እሴቶች የሚከተሉ የወቅቱ ጊዜ ክፍል ነገር ግን መጻኢ ሕይወት የሚያጎሉ መሆናቸው መዘንጋት እንደሌለበት የሚያሳስብ ዕለት መሆኑ ገልጠው፣ ስለዚህ ይኽንን ሕይወት የሚኖሩት ልዩ እሴት፣ መቼም ቢሆን መዘንጋት የለበትም። ድንግልና/ ንጽሕና ሰብአዊ ጎኑን ብቻ መሠረት በማድረግ ለመረዳት መመኰ ፈጽሞ የማይቻል ነው፣ ስለዚህ በእግዚአብሔር መንግሥት የሚሆነውን ሁኔታ ከወዲሁ እንዲያታይ የሚያደረግ በበለጠ ወደ ኢየሱስ ቅርብ የሚያደርግ፣ በገዛ እራስ ኃይል “ተኩኖ-የሚኖር ሕይወት” ሳይሆን ለእግዚአብሔር የሚደረገው የፍቅር ምርጫ የሚጠይቀው ተግባር በሚሰጠው ኃይል የሚረጋገጥ ሕይወት ነው፣ ካሉ በኋላ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ በሁለት ሺሕ መንፈሳዊ ማኅበሮች እና ገዳማት ሥር የሚታቀፉ አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሺሕ መነኮሳት እንዳሉ ጠቅሰው፣ የዚህ ጥሪ ሕይወት ከባድ ቢመስልም ቅሉ በሚጠራው ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል አማካኝነት የሚቻል ነው፣ በዚህ ኃይል መሠረትም በአሁኑ ወቅት የምንኩስና ሕይወት ያለው ውበት ግንዛቤ እጅግ ከፍ እያለ መምጣቱ ገልጠዋል።
ነገ በካምፓላ ዓለም አቀፍ የምክንኩስና ሕይወት ቀን ከአፍሪቃ መነኮሳት እና ለዚህ ሕይወት ከተጠሩት ጋር ለመኖር በዚህ አጋጣሚ ወደ አፍሪቃ እንደሚሄዱና ለክርስቶስ የጋለ ፍቅር ለአፍሪቃ የሚል ቃል መርህ የሚያደርግ ዕለት መሆኑ አብራርተውም፣ የአፍሪቃ ሁለተኛው ሲኖዶስ እንደሚያሳስበውም የእውነት ምስክሮች መሆን በሚል ነገረ መሠረት አፍሪቃ በጠቅላላ ዓለም የውህደትና በአገሮች መካከል ሰላም ለማረጋገጥ ለሰላም ግንባታ ለሚደረገው ጥረት የሚበጅ ልምድ እንዲኖር የሚያሳስብ ዕለት እንደሚሆን ገልጠው፣ ይኽንን መሠረታዊ ሃሳብ ከአፍሪቃ መነኮሳት ጋር ለመካፈል ወደ አፍሪቃ እንዲሄድ ኵላዊት ቤተ ክርስትያን በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ውሳኔ አማክኝነት ስላክ ለእኔ አቢይ ደስታና ኃላፊነትም ነው ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.