2012-01-26 09:29:14

መልዕክተ ር ሊ ጳ በነዲክቶስ ለዓለም አቀፍ ማኅበራዊ መገናኛ ቀን ፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ፊታችን ወርሃ ግንቦት ተከብሮ ለሚውለው ዓለም አቀፍ የማሕበራዊ መገናኛ ቀን መልእክት ማስተላለፋቸው ቫቲካን ላይ የወጣ መግለጫ አስታውቀዋል።

ዝምታ እና ቃለ እግዚአብሔር ፡ የአዲስ ስብከተ ቅዱስ ወንጌል ጉዞ መገናኛ መሆናቸው ቅድስነታቸው በመልእክታቸው ላይ ማስፈራቸው የቫቲካኑ መግለጫ አክሎ ገልጠዋል።

ቃለ እግዚአብሔር እና ዝምታ ካልተጣጣሙ በህዝቦች መካከል የሚደረገውን ግንኙነት ይቀዘቃዛል ያለው መልእክቱ ፡ ዝምታ ራሱ መገናኛ እንደሚቀስቅስ አመልክተዋል።

በአሁኑ ወቅት መልእክቶች እና ዘገባዎች በብዛት በሚሰራጩበት ግዜ ዝምታ ራሱ የበለጠ የመገናኛ መሳርያ መሆኑ ውድስነታቸው ፊታችን ወርሃ ግንቦት ተከብሮ ለሚውለው ዓለም አቀፍ የማሕበራዊ መገናኛ ቀን ያስተላለፉት መልእክት ማመልከቱ ይህ ቫቲካን ውስጥ ላይ የወታ መግለጫ ዘግበዋል።

የሰው ልጅ የህላውናው ትርጉም እና ተስፋ ለማፈላለግ መገናኛ ብዙኀን ሲያገላብጥ እንደ ሚታይ እና አብዛኛው ግዜ በሚቀርቡለት የተለያዩ ዘገባዎች እርካታ እንደማየገን መልእክቱ አመልክተዋል።

እግዚአብሔር የሰው ልጅን በዝምታ እንደምያናግረው እና ሰውም በዝምታ እግዚአብሔርን ለማዳመጥ ከሱ ለመናገር ለመጸለይ እና ለማስተንተን ዕድል ያገኛል ያለው የቅድስነታቸው መልዕክት ስለሆነም ዝምታ ራሱ የመገናኛ መሳርያ መሆኑ ይገልጻል ።ሚዛኑ የተጠበቀ ሥነ ሕይወት መፍጠር አስፈላጊ መሆኑንም መልእክቱ አስምሮበታል።

ከመናገር ይልቅ ማዳመጥ የመዳመጥ ባህል ማሳደግ መማር ያሻል ያለው መልእክቱ ይህ ለማሳላሰል ህልና ለመመርመር ለመረዳት ይረዳል ብለዋል።

በቫቲካን ክፍለ ማኅተም ተገኝተው መልእክቱ ለቫቲካን እና ጣልያን ጋዜጠኞች ያስተዋወቁት በቅድስት መንበር የመሕበራዊ መገናኛ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ክላውድዮ ማሪያ ቸሊሊ ናቸው ።

ብጹዕ አቡነ ክላውድዮ ቸሊ ትናትና ተከብሮ የዋለውን የቅዱስ ፍራንቸስኮስ ዘ ሳለስ የጋዜጠኞች ጠባቂ ምክንያት በርካታ ጋዜጠኞች በተገኙበት ቫቲካን አቅራብያ በሚገኘው የቅድስት ድንግላ ማርያም ቤተ ክርስትያን ሥርዓተ ቅዳሴ አሳርገዋል።

ብጽዕነታቸው የቅዱስ አባታችን የመገናኛ ብዙኀን ቀን መሠረት በማድረግ ያስተላለፉት መልዕክት ለቤተ ለህዝበ ክርስትያን እና ያልሆኑ ያመላከተ እንደሆነ ጠቅሰው መልእክቱን አወድሰዋል ።

የጋዜጠኞች ዘገባዎች ለሰላም እና ህንጸተ ሰብእ ማእከል ያደረጉ ቢሆኑ እንደሚመረጥ እና ግብረ ገባዊ ሐላፊነታቸው በመገባ እንዲወጡ ብጹዕ አቡነ ክላውድዮ ማሪያ ቸሊሊ መማጸናቸው ተመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.