2012-01-23 14:17:37

የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ተልእኮ በላቲን አመሪካ የሚያጎለብት ሐዋርያዊ ጉብኝት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ከመጋቢት 23 ቀን እስከ መጋቢት 28 ቀን 2012 ዓ.ም. በላቲን አመሪካ ሜክሲኮን እና ኩባን ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያከናውኑ ቀደም ተብሎ መገለጡ የሚዘከር ሲሆን፣RealAudioMP3 ይህ በሁለቱ የላቲን አመሪካ አገሮች ብቻ ሳይሆን በመላ ላቲን አሜሪካ የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ተልእኮ የሚያጎለብት መሆኑ የላቲን አመሪካ ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ድርገት ዋና ጸሐፊ ፕሮፈሰር ጉዝማን ካሪኵይሪ ከቫቲካን የተሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ መክሲኮ እና ኵባ ቅዱስ አባታችንን ለማስተናገድ ቅድመ ዝግጅቱ በደስታን እና በጋለ ስሜት እያካሄዱ መሆናቸው አስታውቀዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 12 ቀን 2011 ዓ.ም. ዓመታዊ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዘ ጓዳሉፐ በዓል እንዲሁም የላቲን አመሪካ አገሮች ነጻነታቸውን ያረጋገጡበት 200ኛው ዓመት ምክንያት በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ያረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ መምራታቸው እጅግ ደስ የሚያሰኝ ብቻ ሳይሆን እ.ኤ.አ. መጋቢት 24 ቀን 2012 ዓ.ም. በመክሲኮ 200ኛው ዓመት በተሰየመው አደባባይ መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው ከመክሲኮ ብፁዓን ጳጳሳት ከመላ ላቲን ኣመሪካ ብፁዓን ጳጳሳት ጋር እንደሚገናኙና፣ ለመላ ላቲን አመሪካ ሕዝብ በክፍለ ዓለሙ ለምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የሚያስተላልፉት ሥልጣናዊ መልእክት እና አስተምህሮ በአቢይ ጉጉት እየተጠበቀ መሆኑ ፕሮፈሰር ካሪኵይሪ ገልጠው፣ ቅዱስነታቸው እ.ኤ.አ. ታህሳስ 12 ቀን 2011 ዓ.ም. ላቲን አመሪካ በዚህ ዓለማዊነት ትሥሥር በተረጋገጠበት ዓለም ዋና ተወናያን ከመሆንዋ ባሻገር የተሟላ ውህደት እና ልማት ለማረጋገጥ የሚደረገው ሂደት በሕይወት ባህል፣ ምሥጢረ ተክሊል ያለው ውበት እንዲሁም እውነትን ቤተሰብ በሥፋት የሚታየው የሕንጸት ግሽበት ለማግለል የሚደረገው ጥረት ማኅበራዊ እኩለት እና ጥራት ያለው ፖሊቲካ በማነቃቃት ምርጫ የተደገፈ መሆን እንደሚገባው ማሳሰባቸው ዘክረው፣ አመጽ እና ድህነት እንዲወገድ በሜክሲኮ ሰላም እርቅ ፍትህ ተስፋ ማእከል ያደረገ ሥልጣናዊ መልእክት እንደሚለግሱና በኩባ የፍቅር ንግደት የሚል መጠሪያ የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት የሰየሙት የቅዱስ አባታችን ሐዋርያዊ ጉብኝት ቅድስት ድንግል ማርያም ዘ ኮብረ ሐውልት በክልሉ አሳ አጥማጆች የተገኘበት 400ኛው ዓመት ምክንያት ጋር የተጣመረ በመሆኑም በእውነት ይኽ የኩባው ሐዋርያዊ ጉብኝት በደሴቲቱ ለእምነት ጸደይ ምልክት እንደሚሆን ነው ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.