2012-01-18 15:12:10

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሳምንታዊ የዕለተ ረቡዕ አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ (እ.ኤ.አ. ጥር 18 ቀን 2012 ዓ.ም.)
የሁሉም አቢያተ ክርስትያን ውኅደት፣ የቤተ ክርስትያን ተቀዳሚው ዓላማ የክርስትያኖች ታማኝነት ባላቸው ኅብረት ላይ የሚጸና ነው የሚል እማኔ ነው።


ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ
ከአንድ ዘመን በላይ የሆነው ሁሌ በየዓመቱ በሁሉም በተለያዩ አቢያተ ክርስትያን እና ማኅበረ ክርስትያን ስለ ክርስትያኖች አንድነት መረጋገጥ ሃሳብ በማድረግ የሚከናወነው የጸሎት ሳምንት የሚጀመርበት ዕለት በመሆኑ ምክንያት፣ ዛሬ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሚቀበለው ሥቃይ ቀደም በማድረግ በመጨረሻው እራት ወቅት ባቀረበው ጸሎተ ልመና የጠየቀው ልዩ ጸጋ እንዲህ በማለት “አንተ እንደ ላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ RealAudioMP3 አንተ አባት ሆይ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ፥ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምንለሁ” (ዮሐ. 17፣21) ያቀርበዋል። ስለ ክርትያኖች አንድነት የጸሎት ሳምንት ተግባር እ.ኤ.አ. በ 1908 ዓ.ም. የአንግሊካን ገዳማውያም ማኅበር መሥራች ቀጥለው ወደ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የተመለሱት አባ ፓውል ዋትሶን መሆናቸው ቅዱስ አባታችን ጠቅሰው፣ ይኽ ያነቃቁት ጅማሬ በር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 15ኛ ተባርኮ እና ተቀባይነትም አግኝቶ፣ በሁሉም በካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የሚከናወን ሥርዓተ ጸሎት እንዲሆን እ.ኤ.አ. ጥር 25 ቀን 1961 ዓ.ም. የሮማ ር.ሊ.ጳ. በሚል አጭር ሰነድ አማካኝነት በማበረታታት ተቀባይነት አግኝቶ የጀመረ መሆኑ ገልጠዋል።
ይህ የክርስትያኖች አንድነት የጸሎት ሳምንት እ.ኤ.አ. በ1930 ዎች ዓመታት በአባ ፓውል ኩቱሪየር ዘ ሊዮነ አማካኝነት “እንደ ክርስቶስ ፍላጎት እና እርሱ ባቀረበው መሣሪያ የተረጋገጠ እንዲሆን” በሚያሳስብ ምዕዳን ተስፋፍቶ ተሻሽሎአል። አባ ፓውሎ ኩቱሪየር በመጨረሻዎቹ ጽሑፎቻቸው አማካኝነት ይህ የጸሎት ሳምንት የጌታችን ኢየሱ ክርስቶስ ኩላዊ ጸሎት ‘በሁሉም የክርስትና አካል በሆኑት’ ጸጋውን ከእግዚአብሔር የሚለምኑት ‘ዘንድ እንዲገባ እና እንዲሰርጽ የሚያደርግ መሣሪያ” መሆኑ በማብራራት ‘የሁሉም ክርስቶሳውያን ሕዝቦች አንዳዊ በጣም ከፍ ብሎ ማደግ እንዳለበት ይገልጣሉ። በትክክል ይህ ስለ ክርትያኖች አንድነት የጸሎት ሳምንት በየዓመቱ ፍርያማ የሚያደረገው ብቁ ምልክት እንዲሆን በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በሁሉም ሐዋርያተ ክርስቶስ ዘንድ የተሟላ ውህደት የሚፈለግበት መሣሪያ እንዲሆን የሚያነቃቃ ግፊት ተሰጥቶበታል። ይህ የተለያዩ የሁሉም ባህሎች ክርስትያኖችን የሚያስተባብር መንፍሳዊው ቀነ ቀጠሮ በእኛ ዘንድ ይኽ የምናዘነብልበት ግብረ ውህደት የእኛ ጥረት የሚያረጋገጠው ውጤት ሳይሆን ከላይ የሚሰጥ ጸጋ መሆኑ ያለን ግንዛቤ እንዲያጎለብትና ካለ ማቋረጥም ዘወትር የምንለምነውም ጸጋ ነው።
በየዓመቱ ከሁሉም የተለያዩ አቢያተ ክርስትያን የተወጣጣው የውህደት ቡድን አማካኝነት የሚቀርብ የዚህ የክርስትያኖች ስለ አንድነት የሚደረገው የጸሎተ ሳምነት ደጋፊ ጸሎት መኖሩንም አስታውሰው። በዚህ ጉዳይ ላይ ለማተኮር እሻለሁ፣ በዘንድሮው በዚህ በካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ተወካዮች እና የፖላንድ የተለያዩ አቢያተ ክርስትያን ውህደት የሚያነቃቃው በአገሪቱ ከሚገኙት ከሁሉም የተለያዩ አቢያተ ክርስትያን የተወጣጡ ተወካዮች የሚያቀፈው ምክር ቤት ያዘጋጀው የዚህ የጸሎት ሳምንት ደጋፊ የጋራው ጸሎት ሰነድ መሆኑ ገልጠው፣ ይህ ደጋፊው የጸሎት ሰነድ ከክርስትያኖች አንድነት ከሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት፣ ከእምነት ድርገትና የአቢያተ ክርስትያን የውህደት ምክር ቤት ቅዋሜ ዘንድ በተመለመለው ኮሚቴ አማካኝነት ተጠንቶ እና ተሻሽሎ የቀረበም ነው። ይህ የጋራው ተግባር የሁሉም አቢያተ ክርስትያን መንፈስ ለውህደት ያለው ፍላጎት እና ለዚህ ተግባር ብሎም ሙሉ ውህደት እንዲደረስ የሚያደርግ ጸሎት ቀዳሚ ጎዳና መሆኑ የሚያረጋግጥ ምልክት ነው። የዚህ የዘንድሮው የሁሉም የተለያዩ ክርስትያኖች ስለ አንድነት የሚደረገው የጸሎት ሳምንት መርሆ፣ “…ሁላችንም በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድል እንለወጣለን… “ (1ቆር. 15፣ 51-58 ተመልከት) የሚል መሆኑ ቅዱስ አባታችን ገልጠው፣ ይህ መርሆ ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንጦስ ከጻፋት አንደኛይቱ መልእኽት እንዲሆን የጸሎተ ሳምንት ደጋፊ የጸሎት ሰነድ ያዘጋጀው የፖላንድ የሁሉም አቢያተ ክርስትያን የውህደት ድርገት ያቀረበው ከዕለታዊ ግላዊ እና አገራዊ ገጠመኝ በመንደርደር፣ የፖላንድ ታሪክ ዓይነተኛ መግለጫው የሆነው እርሱም በፈተና እና ግራ በተገባበትም ወቅት የክርስትናው እምነት ምንኛ ጽኑ ድጋፍ መሆኑ ያለውን እምነት ለማበከር ታልሞ መሆኑ ካስረዱ በኋላ ብዙ ውይይት እና ጥናት ከተደረገበት በኋላ በክርስቶስ ማመን ያለው የሚለውጥ ኃይል ላይ ያነጣጠረ መርሆ መመረጡና በተለይ ደግሞ የክርስቶስ አካል የሆነችው የተጨባጭዋ ቤተ ክርስትያን አንድነት እንዲረጋገጥ የሚቀርበው የእኛ ጸሎት ያለው አስፍፈላጊነት ለየት ባለ መልኩ በሚገልጥ ብርሃን የታወደም ነው። ይኽንን የአስተንትኖ ሃሳብ ያስተነፈሰውም ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንጦስ ለነበረቸው ቤተ ክርስትያን እርሱም በአሁኑ ባለበት የሕይወት ዘመን፣ ክፍል የሆነው የፍጡርነት ጊዚያዊ ባህርይ የሚገልጥ በኃጥያት እና ሞት የመሸነፍ ገጠመኝ የክርስቶስ ድል ለእኛ የሚሰጠው በኃጢአት እና በሞት ላይ ድልን መንሣት የሚያረጋገጠው ምሥጢረ ፋሲካ ጋር በማመላከት ያቀረባቸው ቃላቶች ናቸው።
ታሪክ፣ ለየት ባለ መልኩም የአገረ ፖላንድ ታሪክ እንደ አብነት በመጥቀስ በ14ኛው ክፍለ ዘመን በአገሪቱ የተኖረው ዴሞክራሲያዊ እና የሃይማኖት ነጻነት የተካነው ማኅበራዊ ሕይወት ባለፉት የመጨረሻ ዘመናት ወረራ መፈራረስ ካለ ማቋረጥ ጭቆና ለማግለል የተካሄደው ትግልና የነጻነት ጥማት የተሰማበት መሆኑ የሚያበክር ገጠመኝ የተሞላ እንደነበርም አስታውሰው፣ ይህ ሁሉ ታሪካዊ ገጠመኝ የሁሉም አቢያተ ክርስትያን የጋራው ድርገት ‘ሽንፈት’ እና ‘ድል’ የተሰኙት ሁለት ቃላቶች እውነተኛው ትርጉም ላይ ጥልቀት በተሞላው አግባብ እንዲስተነተን መርቶታል። ድል፣ አሸናፊነት የተሰኘው የአገላለጡ ሁኔታ የማይከተል ድል ማለት ምን ማለት መሆኑ እርሱም በሥልጣን እና በኃይል መንገድ አማካኝነት የማይጨበጠውን ለየት ባለ መንገድ ክርስቶስ “ፊተኛ ሊሆን ቢወድ ከሁሉ በኋላ የሁሉም አገልጋይ ይሁን” (ማር. 9፣35) በሚለው ቃል ላይ የጸና ድልን ያመለክታል። ክርስቶስ በፍቅር በጋራው የእርስ በእርስ አገልግሎትና መተጋገዝ፣ በአዲስ ተስፋና የመጨረሻ ለሆኑት እና ለተኮነኑት ለተረሱት እና ለተናቁት በማገልገል መንገድ የሚገኘው ድል ያመለክታል። ለሁሉም ክርስትያኖች የዚህ የትሁት አገልጋይነት የላቀው መግለጫ እና ትርጉም ለገዛ እራሱ ኢየሱስ ክርቶስ መሆኑ፣ ገዛ እርሱን ሙሉ ስጦታ በማድረግ የሚያቀርበው፣ በሞት ላይ ድል የነሳው የፍቅሩ ድል በፋሲካው የሌሊት ብርሃን ቦግ ቦሎ የሚንጸባረቀው ድልን ያመለክታ። እኛ የዚህ ድል ተካፋዮች ለመሆን የምንችለውም በእግዚአብሔር እንድንለውጥ ገዛ እራሳችን ስናቀርብ ሕይወታችን እንዲለወጥ ስንተጋ ብቻ ነው። ለዚህም ነው የፖላንድ የሁሉም የተለያዩ አቢያተ ክርስትያን የውኅደት ቡድን የዚህ የጸሎት ሳምንት ተገቢ መርሆ “ሁላችን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድል እንለወጣለን” የሚለው የቅዱስ ጳውሎስ ቃላቶች ላይ የተደገፈ እንዲሆን ያደረገው። (1ቆሮ. 15፣ 51-58 ተመልከት)።
የተሟላ እና ተጨባጭ የክርስትያኖች አንድነት ላይ ያነጣጠረው አትኵሮአችን እና ጥባቄአችን ዘወትር በተዋጣለት አግባብ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምሳል እንድንለወጥ እና እንድንጸና ገዛ እራሳችንን ፈቅደን ማቅረብ የሚጠይቅ ተግባር ነው። የምንጸልየው አንድነት የግልም ይሁን የጋራው ውስጣዊ መለወጥን የሚጠይቅ ነው። የተለመደው ተራው መከባበር እና ትብብር የሚል ሳይሆን፣ በእግዚአብሔር፣ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው የተናገረው እና ሥጋችን የለበሰው እግዚአብሔር ላይ ያለን እምነት ማጎልበት፣ እውነተኛ እና የመጨረሻው ወሳኝ ድላችን በሆነው በክርስቶስ ወደ አዲስ ሕይወት መግባት፣ በእያንዳንዳችን መካከል ግልጽነትን እግዚአብሔር ለእኛ ቅሙጥ ያደረገው ሁሌ እንደ አዲስ የሚጸግወን የአንድነት መሠረታዊ ነገሮችን ማስተናገድን፣ በክርስቶስ አማካኝነት የተገለጠው ኅያው እግዚአብሔርን ለዘመናችን ሰው መመስከር አንገብጋቢ መሆኑ መገንዘብን ይጠይቃል ብለዋል።
ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ የክርስትያን የተሟላ ውህደት (የክርስትያን ህብረት) በተሰየመው ውሳኔ ቍ. 4 ኅብረተ አቢያተ ክርስትያን በተሰኘው ንኡስ ርእስ ሥር “ይህ ቅዱስ ጉባኤ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ምእመናን የጊዜ ምልክቶች የሆኑትን በመገንዘብ ስለ አንድነት በሚደረገው እንቅስቃሴ በንቃት እና በትጋት መንፈስ ተሳታፊዎች እንዲሆኑ ይማጠናል” በማለት ጉባኤው አንድነትን መሻት በቤተ ክርስትያን ሕይወት እና ተግባር ማእከላዊ ሥፍራ ሰጥቶታል። ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እ.ኤ.አ. 1995 ዓ.ም. “Ut unum sint በተሰኘው ለተለያዩ አቢያተ ክርስትያን ውህደት ጥሪ የሚያቀርብ ዓዋዲ መልእክት ቍ.9፣ የዚህ ተልእኮ መሠረታዊው ባህርዩን “ይህ ጌታችን ለቤተ ክርስትያኑ የሰጣት የአንድነት ጸጋ በዚሁ አንድነት ሥር ሁሉምን የማሰባሰብ እና በእቅፍዋ የማኖር ፍላጎትዋ ቅጽል ወይን ተጨማሪ ሳይሆን የተልእኮዋ ማእከል ነው። ለእርሱ ማኅበረ ሐዋርያት የሰጠው በሁለተኛ ደረጃ የሚቀመጥ መለዮ ማለት ሳይሆን፣ የዚያ ማኅበረ ሐዋርያት መሆን ዘንድ ያለ ነው” በማለት እንዳሰመሩበት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በማስታወውስ፣ ስለዚህ የውህደቱ ጥረት የመላ ቤተ ክርስትያንና የሁሉም የተጠመቁት ኃላፊነት መሆኑ በክርስትያኖች መካከል የእውነት እና የፍቅር ሙሉ አንድነት እውን እስከ ሚሆን ድረስ ይኽንን አድነት በውስጣቸው ያጎለብቱ ዘንድ ኃላፊነት አለባቸው። ስለዚህ የክርስትያኖች አንድነት የጸሎት ሳምንት በዚህ ሳምንት ብቻ የሚታጠር ሳይሆን በሁሉም ሥፍራ እና ጊዜ በተለይ ደግሞ የተለያዩ ባህል ያላቸው ሕዝቦች ሲገናኙና በመተባበር በኃጢአት በክፋት በኢፍትኃዊነት በሰብአዊ ክብር ዓመጽ ላይ ድል የነሳው ስለ ክርስቶስ ድል ሲተጉ የሚገለጥ የሚኖር ባጠቃላይ የሁሉም ክርስትያኖች የጸሎት ሕይወት ጋር የተጣመረ ነው ብለዋል።
ይህ ስለ ክርስትያኖች አንድነት ወቅታዊው እንቅስቃሴ የዛሬ አንድ ዘመን ቀደም ብሎ ከተወለደበት ዕለት ወዲህ የክርስትያኖች አንድነት መጓደል የአስፍሆተ ወንጌል ተደማጭነቱና ፍቱንነቱን እንደሚያሰናክል ያለው ግንዛቤ ግልጽ እየሆነ መጥተዋል። የተከፋፈልን ከሆን እንዴት አድርገን ነው አሳማኝ ምስክርነት ለማቅረብ የምንችለው? በርግጥ የእምነት መሠረታዊ እውነት መሠረት አንድ የሚያደርገን ከሚከፋፍለን እጅግ ይበዛል። ሆኖም ግን የሚለያየው እርሱም መደናገርን እና አለ መተማመንን የመሳሰሉት የክርስቶስ የማዳን ቃል ለማስተላለፍ ያለን ብቃት የሚያዳክም ጉዳይ፣ ተግባራዊ እና ሥነ ምግባራዊ ጥያቄዎችን የሚመለከት ነው። በዚህ መልኩም ነው የር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ኡት ኡኑም ሲንት በተሰየው ዓዋዲ መልእክት ቁጥር 98 እና 99 ሥር ለክርስትያናዊ ምስክርነት እና ወንጌልን ለማበሠሩ ተልእኮ የእንቅፋት ምክንያት የሆነውን በመለየት ያሰመሩበት ሃሳብ ለመረዳት የምችለው።
የቤተ ክርስትያን ጉዞ ልክ እንደ የአሕዛብ ጉዞ፣ ለሁሉም ያቀረበው ጉዞ በሚሰቃዩት ሁሉም ሥም የተሰቃየው በሞትና በኢፍትሃዊት ላይ ድል በነሳው በክርስቶስ እጅ ነው። የድሉ ተሳታፊዎች እንድንሆን አድርጎናል፣ እርሱ ብቻ ነው የሚለውጠን፣ ከደካማነታችን እና ከመወላወል መጠራጠር በመለየት ለመልካም ሥራ እንድንቆም ቆራጦች እና ኃይለኞች የሚያደርገን። እርሱ ብቻ ነው መከፋፈላችን ከሚያስከተሉት አሉታዊ ነገሮች ሁሉ የሚያድነን እርሱ ብቻ ነው። የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ በዚህ ለክርስትያን አንድነት በሚደረገው ጸሎት፣ የጋራው ምስክርነት መተባበር እና መደጋገፍ በክርስትያኖች መካከል በሐዋርያት የተላለፈውን እምነት በጋራ የምንደግምበት እና እማኔውም የምንገልጥባት በክርስቶስ የመለወጣችን ቅዱሳት ምሥጢራት በጋራ የምንቀድስባት እና የምናከብርባት ያች ሞጎስ የተሞላት ቀን በመጠባበቅ በተጋ ጸሎት ትተባበሩ ዘንድ ለሁላችሁም ጥሪ አቀርባለሁኝ ካሉ በኋላ ለሁሉ ከውጭ እና ከኢጣሊያ ውስጥ ለመጡትን በብዙ ሺሕ የሚግመቱት ቫቲካን በሚገኘው ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ ለተገኙት ምእመናን በተለያዩ ቋንቋዎች ሰላምታን አቅርበው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ተሰናብተዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.