2012-01-16 14:16:48

የአገረ ቫቲካን ፍርድ ቤት የሕግና ፍትህ የሥራ ዓመት


እ.ኤ.አ. ቀዳሜ ጥር 14 ቀን 2012 ዓ.ም. የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ በአገረ ቫቲካን አስተዳዳሪ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት የቫቲካን ፍርድ ቤት የዳኞች እና የሥነ ሕግ RealAudioMP3 ሊቃውንት የፍርድ ቤቱ አባላት እና ሠራተኞች በተገኙበት የቫቲካን ፍርድ ቤት ዓመታዊ የሕግና ፍትህ ሥራ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ መከፈቱ የቅድስት መንበር መግለጫ በመግለጥ፣ ብፅዕነታቸው የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ዋና ዓላማ እና ተልእኮ በማንኛው ጊዜ እና ሥፍራ የሰብአዊ መብት፣ ክብር እና ግዴታ ማወጅ እና መንከባከብ መሆኑ በመግለጥ፣ በዚህ ባላት ዓላማም በሕግና ፍትህ ጉዳይ አርእያ እንድትሆን ያላት ኃላፊነት የሚያበክር መሆኑ በማብራራት፣ ቤተ ክርስትያን ልዩ የሚያደርጋት ጥሪዋ እና ተልእኮዋ ዘወትር የእግዚአብሔር መሃሪው ፍቅር መግለጫ የሆነው የእግዚአብሔር ፍርድ መሣሪያ እና ምልክት ሆኖ መገኘት መሆኑ በጥልቀት መግለጣቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።
በቅዳሴው ሥነ ሥርዓት የኢጣሊያ የሕግና ፍትህ ጉዳይ ሚኒ. ፓውላ ሰቨሪኖ መሳተፋቸውም ሲገልጥ፣ የቫቲካን ፍርድ ቤት በማስመልከት የቫቲካን ሕግና ፍትህ አስከባሪ ጠበቃ ኒኮላ ፒካርዲ ባቀረቡት መግለጫ፣ የቫቲካን ፍርድ ቤት ብቃት ያላው ሚዛኑ የጠበቀ አጥጋቢነት ያለው መሆኑ ገልጠው፣ ጥንቁቅ እና የተወሃደ መሆኑ የእ.ኤ.አ. የ 2011 ዓ.ም. ክንዋኔዎች መሠረት በማድረግ ከገለጡ በኋላ፣ የቫቲካን ፍርድ ቤት ከዓለም አቀፍ ከተለያዩ አገሮች ጋር ያለው ግኑኝነት የተዋጣለት መሆኑ ጠቅሰው፣ ለዓለም አቀፍ ኤኮኖሚ ሰላም ጸጥታ እና ደህንነት አቢይ ሥጋት የሆነው በሕገ ወጥ መንገድ የሚደረገው የገንዘብ ሃብት ሕገ ወጥ አሸራውን ለመሰወር የሚደረገው ሕጋዊ መዋዕለ ንዋይ ፍሰት እንቅስቃሴ ለመቆጣጥር እንዲቻል ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባላቸው ጴጥሮሳዊ ልዩ ሥልጣን አማካኝነት እንዲቋቋም ያደረጉት የገንዘብ ሃብት ተቆጣጣሪ ባለ ሥልጣን እና ጉዳዩ በተመለከተ ያወጁት አዲሱ ሕግ እግብር ላይ የማዋል ሂደት ጭምር በማፋጠን ከቫቲካን የሚወጣ እና ወደ ቫቲካን የሚገባው የገንዘብ ሃብት ምንጩ የመቆጣጠር ሥልጣን መሆኑም አብራርተው፣ ቫቲካን ምንም’ኳ የኤውሮጳ ኅብረት አባል አገር ባይሆንም ፍርድ ቤቱ የኤውሮጳ ማእከላዊ ባንክ ቤት፣ ከተለያዩ አገሮች የጸጥታ ኃይል በሕግና ፍትህ ጉዳይ በተመለከተ ዘርፍ ያለው ግኑኝነት አመርቂ እና አብነት መሆኑም በስፋት እንደገለጡ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.