2012-01-13 15:19:25

ብፁዕ ካርዲናል ኦኮጊየ፦ “ናይጀሪያ እና የውይይት ግዴታዊ ኃላፊነት”


በፈደራላዊት ረፓብሊክ ናይጀሪያ የለጎስ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ኤንቶንይ ኦሎቡንሚ ኦኮጊየ በአገራችው ተከስቶ ስላለው ግጭት በማስመልከት ከሚስና የዜና አገልግሎት ጋር ባካሄዱት RealAudioMP3 ቃለ ምልልስ፣ የአገሪቱ አንድነት እንዳይናጋ መጸለይ ያስፈልጋል ካሉ በኋላ እኚህ የቅድስት መንበር ቅንብር እና የኤኮኖሚ ጉዳይ በተመለከተ በሚሰጡት የሥነ መሥተዳድር አገልግሎት ጥበብ የተካነው መርህነታቸውና በማሥተዳዳር ብቃታቸው የሚደነቁት ብፁዕ ካርዲናል ኦኮጊየ አክለውም፣ ባኮ ሓራም በማለት እራሱን የሰየመው የክራሪው የምስልምና እምነት ተከታይ ኃይል በናይጀሪያ ሰሜናዊ ክልል በሚሰነዝረው ጥቃት እና በሚያስከትለው አመጽ ምክንያት ክርስትያናኖችን ለማባረር የተያያዘው ምርጫ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ግጭት እያስፋፋ የነዳጅ ዋጋ እንዲንር፣ መንግሥት እግብር ላይ እያዋለው ያለው የድጎማ ውሳኔ እንዲሻር ለማድረግ የወሰደው ውሳኔ በሣሪያ በማድረግም ግጭቱ በሁሉም ዘርፍ እንዲዛመት ዓልሞ የተነሣ ነው የሚመስለው፣ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ክብር እና ፈቃድ አስከባሪው የባለይ ድረገት ‘ባኮ ሓራም’ በናይጀሪያ በሙስሊሞች እና በክርስትያኖች መካከል አለ መግባባት እንዲርኖር የሁከት ዘር እየዘራ ነው በማለት የሰጠው መግለጫ መሠረት በማድረግ በናይጀሪያ ባኮ ሓራም እየሰነዘረው ያለው ጥቃት፣ የኃይማኖት ጦርነት ነው በማለት ጋዜጠኞች ይዘግባሉ፣ በእውነቱ መሠረት የሌለው ትንተና ነው። የሃይማኖት ጦርነት ነው ብሎ መግለጡ ያለው የግጭቱ ተጨባጭ ሁኔታ ማዛባት እና አመጹን ማባባስ ይሆናል።
ችግሩ ቁርጥ ባለ መልኩ በፖሊቲካው የሥልጣን ሽኩቻ የሚባባስ ማኅበራዊ እና ኤኮኖሚያዊ ችግር ነው። እ.ኤ.አ. ባለፈው ህዳር ወር የባኮ ሓራም ደጋፊ በሚል ክስ አንድ የአገሪቱ የሕግ መወሰኛ የበላይ ምክር ቤት ለእስር ከተዳረጉ በኋላ በዋስ ተለቀዋል። በእሳቸው ላይ የተወሰደው እርምጃ ብዙዎች በክልላቸው የፖለቲካ ሥልጣን ለመጨበጥ የሚጠቀሙበት ክብር የሌለው ሥልት የሚያጎላ ይመስላል። በአንዳንድ ክልሎች አክራሪያኑን መደገፍ የክልሉ ሕዝብ ድምጽ በማካባት ሥልጣን ለመጨበጥ ሥልት እየተገለገሉበትም ነው።
ርእሰ ብሔር ጉድላክ ጆናታን፣ ባኮ ሃራም በመንግሥትና በጸጥታና የደህንነት ጥበቃ ኃይሎች መዋቅር ውስጥ ሰርጎ የገባ ነው በማለት የሰጡት መግለጫ፣ መፍትሄ አይደለም፣ ስለዚህ ጉዳዩ በጥልቅ መጣራት አለበት፣ ምክንያቱ የባኮ ሓራም ሰርጎ ገቦች የአገሪቱ አንድነት ቀስ በቀስ ሊያናጉ ይችላሉና። አንዱ ሌላው የመግደል መብት የለውም፣ መግደል አመጽን ነው የሚያባብሰው፣ ሃይማኖቶች በባህርያቸው የሰላም መሣሪያዎች ናቸው። ባኮ ሐራም በብዙኃን ምስልምና ሃይማኖት መሪዎች የተወገዘም ነው። በሌጎስ ክርስትያኖች እና ሙስሊሞች ተከባብረው ለጋራ ብልጽግና አብረው እየሠሩ ይኖራሉ፣ በናይጀሪያ ቀዳሚው ችግር ሙስና እና ምግባረ ብልሽት ነው። የፖለቲካ አባላት የአገር ልማት ለማፋጠን በሚል ሰበብ ለሕዝብ የሚሰጠው ድጎማ ለማንሳት እንደሚሹ ይናገራሉ፣ በርግጥ ናይጀሪያ በነዳጅ ሃብት የታደለች አገር ነች፣ የነዳጅ ምርት ለውጭ ንግድ አቅርቦት መሠረት አገሪቱ የምታስገባው የገዘብ ሃብት እስካሁን ድረስ የአገሪቱ ልማት ሲያፋጥምን ሆነ ያለው የሥራ አጥነት ችግር እና ድኽነት ሲቀርፍ አልታየም፣ አውራ ጎዳናዎች እና የከተማ መንገዶች የተጎዳጎደ፣ የመብራት ሃይል አገልግሎት ለደላው ብቻ እየሆነ፣ የትምህርት መርሃ ግብር ጥራት የለውም ነው ካሉ በኋላ የሕዝብ እና የአገር ጥቅም ማስቀደሙ ወሳኝ ብቻ ሳይሆን ሰላም የሚያደፈርሰውን ኃይል ጭምር ለመቆጣር እና ከወዲሁ ጸረ ሰላም ዓላማውንም ለማክሸፍ ይቻላል እንዳሉ ሚስና የዜና አገልግሎት አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.