2012-01-12 12:14:06

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሳምንታዊ የዕለተ ረቡዕ አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ (እ.ኤ.አ. ጥር 11 ቀን 2012)
“የክፋት መንፈስ ድል እንዳይነሳ በቅዱስ ቁርባን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸሎትን እንኖራለን”።


የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ
በወንጌል በቀረበው የእየሱስ ጸሎት ዙሪያ የጀመርነው የማስተንተን ሂደት በመቀጠል ዛሬ በመጨረሻ እራት ወቅት የደገመው ሞጎስ የተሞላው ክቡር ጸሎት ላይ እናተኩራለን።
ኢየሱስ ከጓደኞቹ ለመሰናበት በተዘጋጀው የማዕድ ግብዣ ‘የመጨረሻው እራት’ በስተጀርባ ያለው ሁኔታ እና ስሜት የሚቀበለው ሞት የማይቀር ግልጽ መሆኑ ያለው ግንዛቤ የሚገልጥ ነው። ኢየሱስ ቀደም በድማረግ ለደቀ መዛሙርቱ በዚህ ለወደፊት በሚሆነው የሚቀበለው ሥቃይ በተመለከተ የመከራው RealAudioMP3 ተካፋይነታቸውን ለመረጋገጥ ካለ ማቋረጥ በግልጽ ተናግረዋል። የቅዱስ ማርቆስ ወንጌል ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ጉዞውን በፊሊጶስ ቂሣርያ ካሉት ሩቅ መንደሮች ሲጀምር “ሽማግሌዎችና የካህናት አለቆች ጻፎችም የሰውን ልጅ ይነቅፉት ዘንድ ብዙ መከራም ያጸኑበት ዘንድ እንዳለው፣ እንደሚገድሉትና በሦስተኛው ቀንም እንደሚነሣ ያስተምራቸው ጀመር” (ማር. 8፣31)። በተጨማሪም ከደቀ መዛሙርት ለመሰናበት በሚዘጋጅባቸው ቀናቶችም፣ የሕዝቡ ሕይወት በፋሲካ ማለትም ከግብጽ ነጻ የወጣበት የተዘክሮ ቀን መቃረብ ሁናቴ የተስተዋለበትም ነበር። ይህ ባለፈው ታሪክ የተኖረው ነጻነት፣ በአሁኑ ጊዜ እና ለወደፊትም የሚኖር በመሆኑ፣ በቤተሰብ ውስጥ ፋሲካን በማክበር ህያውነት ካለ ማቋረጥ ይረጋገጣል። የኢየሱስ የመጨረሻው እራት አዲስትነት ተገቢነት ያለው፣ በዚሁ አገባብ የሚገለጥም ነው። ኢየሱስ መከራውን ሞቱንና ተንሣኤውን በተሟላ ግንዛቤ ይመለከታል። እርሱም ከዚህ ቀደም ከተከናወኑት ማእድች ለየት ባለ ሁኔታ እና ዓይነት ይኸንን እራት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ሙሉ በሙሉ አዲስ ሥጦታ እርሱም ገዛ እራሱን የሚሰጥበት የእርሱ እራት ለመኖር ይፈልጋል። እንዲህ ባለ መልኩ ኢየሱስ መስቀሉን እና ትንሥኤውን ቀደም በማድረግ የሚገልጥበት ፋሲካውን ያከብራል።
ዮውሐንስ ወንጌላዊ የመጨረሻ እራት በቅደም ተከተል ሲያቀርብ፣ ያለው አዲስ ገጽታውን ሲያበክር የፋሲካ እራት ተራ ሳይሆን፣ ኢየሱስ አንድ አዲስ ገጽታውን የሚያበሥር ከዘጸአት ሁኔታ ጋር የተጣመረ ሆኖ፣ ነገር የገዛ እራሱ ፋሲካ የሚያከብርበት መሆኑ በዚህ መልኩ የሚገለጠው የመጨርሻው እራት ያለውን አዲስ ገጽታውን ይገልጥልናል። ለወንጌላዊ ዮውሐንስ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሲሞት፣ በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ የፋሲካ በጎች የሚሰዉበት ወቅትም ነበር።
የዚህ የመጨረሻው እራት ነገረ አንኳሩ ምንድን ነው? እንጀራውን አንስቶ በመቁረስ፣ ደቀ መዛሙርቱ በማቋደስ የወይኑ ጽዋ በማንሳትም ከእነርሱ ጋር መካፈሉን የሚያበሥሩ የኢየሱስ እና የቤተክርስትያን መሠረታዊ ጸሎት የሆነው የቅዱስ ቁርባን ምሥጢር መሠራት የሚያረጋግጡ ሸኝ እና በጸሎት አገባብ የሚጠቃለሉ የኢየሱስ ቃላቶች እና የሚፈጽማቸው ምልክቶች ናቸው። ሰለዚህ ይኸንን ሁኔታ ቀርበን እንመልከት።
በቅድሚያ የቅዱስ ቁርባን ምሥጢር ቅዋሜው የሐዲስ ኪዳን ባህል (1ቆሮ. 11፣ 23-25፤ ሉቃ. 22፣ 14-20፤ ማር. 14፣ 22-25፤ ማቴ. 26፣ 26-29 ያለው ተመልከት) እንደሚያመለክተውም፣ ኢየሱስ ኅብስቱንና ጽዋውን በተመሳሳይ መልኩ በማንሣት በሚያስተዋውቃቸው ምልክቶች እና በሚደግማቸው ቃላቶች አማካኝነት፣ ሁለት ተመሳሳይና ተሟይ የሆኑት ግሶች ያጠቃለሉ ምልክቶች እና ቃላቶችን የሚከተል ጸሎት ያስተዋውቃል። ጳውሎስ እና ሉቃስ ስለ ቅዱስ ቁርባን - ምስጋና በሚለው አገላለጥ “ኅብስቱንም አነሣ አመሰገነ፣ ፈትፍቶም ሰጣቸው…(ሉቃ. 22፣19)፣ ማርቆስ እና ማቴዎስ ‘መባረክ’ በሚለው ቃል ላይ ያተኵራሉ፣ “…ኅብስቱን አንሥቶ ባርኮ ቈርሶም ‘ይህ ሥጋዮ ነው፣ እንኩ ብሉ’ ብሎ ሰጣቸው…”(ማር. 14፣22).፣ ስለዚህ ሁለቱ የግሪክ ቃላቶች እርሱም eucaristeìn-ምስጋና eulogeìn-በማረክ የሚሉት ቃላቶች ‘berakha’ በራክሃ ወደሚለው የእብራይስጥ ቃል ‘berakha’ በእስራኤል ባህል በታላላቅ ማዕድ የሚደግሙት የምስጋና እና የመባረክ ተግባር ወደ ሚያሰማው ጸሎት ዘንድ ይመሩናል።
ሁለቱ የተለያዩ የግሪክ ቃላቶች የዚያ ጸሎት በውስጠ ባህርይ መተሳሰርና እርስ በእርሳቸው የተሟይነት ባህር ያላቸው ሁለት ምልክቶች ይጠቁማሉ። ‘Berakha’ ስለተቀብልከው ጸጋ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ የምስጋና እና የአክብሮት ተግባርን ያሰማል። ኢየሱስ በመጨረሻ እራት፣ ኅብስት እግዚአብሔር የሚሰጠው ‘በተግባር-ሥራ’ በመሬት ተዘርቶ እራሱ (እግዚአብሔር) ያለማው እና ፍሬ እንዲሰጥ ያደረገው የስንዴ ዘር ነው። ወይኑም እግዚአብሔር የሚሰጠው በተግባር-ሥራ በመሬት ተዘርቶ እራሱ ያለማው እና ፍሬ እንዲሰጥ ያደረገው የወይን ተክል ነው። ይህ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርበው ውዳሴ እና ምስጋና፣ ቡራኬ ሆኖ ከእግዚአብሔር ተትረፍርፎ ጸጋ ሆኖ የሚወርድ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔርን መወደስ እና ማመስገን፣ ቡራኬ ይሆናል ማለት ነው። ለእግዚአብሔር እንደ መሥዋዕት የሚቀርበው ሥጦታ ከኃያሉ ተባርኮ ወደ ሰው ይወርዳል። የቅዱስ ቁርባን ቅዋሜ የሚያረጋግጡ ቃላቶች ከዚህ ዓይነቱ የጸሎት አገባብ ጋር የሚደላደል፣ የ Berakha ውዳሴ እና ቡራኬ፣ ያንን ኅብስትና ወይን ወደ ኢየሱስ ሥጋ እና ደም የሚለውጥ እና የሚቀድስ ይሆናል።
በቅዱስ ቁርባን ቅዋሜ የሚቀድሙት እርሱም ኅብስት መቁረስ ወይኑም ማቅረብ የሚያሰሙ ምልክቶች ናቸው። ኅብስቱን ቆርሶ ወይኑንም በማቅረብ ሁሉም እንዲካፈሉ የሚሰጠው በማእድ የቤተሰብ አባላትን እንዲሰባሰቡ ጥሪ የሚያቀርበው አበ ቤት ነው። እነዚህ ምልክቶችም የመስተንግዶ የሚያሰሙ፣ እንግዳ ተቀባይ፣ የተለየው የቤተሰብ አባል ያልሆነው ለውጭ አገር ሰው በማእድ ሱታፌ እንዲኖረው የሚያደርግ መስተንግዶን ያሰማል። እነዚህ ተመሳሳይ ምልክቶች በመጠቀም ኢየሱስ ከወዳጆቹ ሲሰናበት፣ ቃላቶቹ በተመሳሳይ ደረጃም ጥልቅ ኅዳሴ ይጎናጸፋሉ። እግዚአብሔር ገዛ እራሱ ጸጋ አድርጎ በሚስጥበት ማእድ ኢየሱስ ተጨባጭ የመስተንግዶ ምልክት ይሰጣል። ኢየሱስ በኅብስቱ እና በወይኑ ገዛ እራሱን መባ በማድረግ ገዛ እራሱን ያቀርባል ይሰጣልም።
ይህ ሁሉ እንዴት ሊፈጸም ይችላል? ኅብሱት እና ወይኑ በሰጠበት ወቅት ኢየሱስ እንዴት አድርጎ ነው ገዛ እራሱን የሚሰጠው? ኢየሱስ በመስቀል ተሰቅሎ፣ ነጻ ያልሆነው የሰው ዘር በሚገለገልበት የሞት ፍርድ ቅጣት፣ ቺቸሮነ እንደሚለውም አሰቃቂው የመስቀል ሞት አማካኝነት ሕይወቱ ለሞት ተላልፋ እንደምትሰጥ ያውቃል። ኢየሱስ በመጨረሻው እራት ኅብስት እና ወይን መባ አድርጎ ሲያቀርብ ስለ ቸር እረኛ ኢየሱስ በየውሐንስ ወንጌል ምዕ. 10፣ 17-18 እንደሚናገረ “ስለዚህ አብ ይወድደኛል፣ እንደገና አስነሣት ዘንድ እኔ ነፍሴን እሰጣለሁና። ከእኔ ማንም አይወስዳትም፣ ነገር ግን እኔ በፈቃዴ እሰጣታለሁ እኔ ላኖራት ሥልጣን አለኝ፣ መልሼ እወስዳት ዘንድ ሥልጣን አለኝና፣ ይህን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ።” በሚሉት ቃላቶች አማካኝነት የገዛ እራሱን ሞት እና ትንሣኤ ቀደም በማድረግ ይንገራል። ከገዛ እራሱ የምትነጠቀው ሕይወት እራሱን መባ አድርጎ የማቅረቡ ተግባር ቀድሞ ያበሥራል፣ በዚህ አኳኃን አሰቃቂው ሞቱ ነጻ በሆነው በገዛ ፈቃዱ ለሌሎች ገዛ እራሱን ለሚሰጥ ተግባር ይለውጠዋል። የሚደርስበት ስቃይ ነጻ እና ድኅነት የሚያረጋግጥ መሥዋዕት በማድረግ በሙሉ ተሳታፊነት ይለውጠዋል።
በመጽሐፍ ቅዱስ ባህል መሠረት በሚገለጡት ሥርዓቶች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገዛ እራሱን ማንነት እና የፍጹም ፍቅር ተልእኮው ካለ ማመንታት እስከ ፍጻሜ ድረስ እግብር ላይ እንደሚያውለው ያለው ቁርጠኝነት፣ እርሱም ገዛ እራሱን ለአብ ፈቃድ ታዛዥ ሆኖ በማቅረብ ያረጋግጠዋል። በቅዱስ ቁርባን መታሰቢያ አማካኝነት ገዛ እርሱን መሥዋዕት አድርጎ ለወዳጆቹ መስጠት፣ ከደቀ መዛሙርቱ የመሰናበቻ የመጨረሻ እራት ወቅት ያለው ተግባር የጸሎት የላቀው ትርጉም እና ፍጻሜው ይገልጣል። የዚያች ሌሊት የኢየሱስ ምልክቶች እና ቃላቶች ስናስተነትን፣ በእርሱ እና በአብ መካከል ያለው ጥልቅ እና ጽኑ ግኑኝነት የሚኖርበት ሥፍራ ለወዳጆቹ ለእያንዳንዳችን ጥሎት ያለፈው የፍቅር ምሥጢር “የሚሠዋ ፍቅር ምሥጢር” ነው። ለሁለት ጊዜ በቀራንዮ የተደመጡት “ …መታሰቢያዮንም እንዲሁ አድርጉ…” (1ቆር. 11፣ 24.25) የሚሉት ቃላቶች ያስተጋባል። ገዛ እራሱ አሳልፎ በመስጠት እውነተኛው የኦሪት አምልኮ የሚሰዋው በግ በመሆን እፍጻሜ በማድረስ ፋሲካን ያከብራል። ለዚህም ነው ጳውሎስ ለቆሮንጦስ ክርትስያኖች “ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና ስለዚህ በቅንነትና በእውነት ቂጣ በዓልን እናድርግ እንጂ በአሮጌ እርሾ በክፋት በግፍ እርሾም አይደለም” (1ቆር. 5፣ 7-8) በሚሉት ቃላቶቹ የሚያረጋግጠው።
ወንጌላዊው ሉቃስ የመጨረሻ እራት ሁኔታ በተመለከተ ድንቅ የሆኑ ሁኔታዎች ያቀርብልና፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚያች ሌሊት ለደቀ መዛሙርቱ የሚያቀርበው ለእያንዳንዱ ትኵረት የሚሰጥ ጸሎት፣ የሚያሳዝን፣ ለኃዘን ተካፋይነት የሚጋብዝ እንደሆነ ያረጋግጥልና። ከቡራኬ እና ከምስጋና ጸሎት በመጀመር ኢየሱስ ገዛ እራሱ ቅሩባን አድርጎ ማቅረብን ያመለክታል፣። ይኸንን ገዛ እራሱ የመስጠቱ እውነት የሚያርጋግጠው ምሥጢር ሲሰጥ፣ ባቀረበው ማዕድ ፍጻሜ “ስምዖን ስምዖን ሆይ እነሆ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፣ እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ፣ እንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና።(ሉቃ. 22፣ 31-32) ሲል ይናገራል። በደቀ መዛሙርት ፊት ፈተና ሲደቀን እርሱም የእግዚአብሔር መንገድ በፋሲካ ምሥጢረ በሞትና በትንሳኤ የሚያልፍ መሆኑ ለመገንዘብ ያለባቸው ድካምነት በሚጎላበት ወቅት ኢየሱስ ገዛ እራሱ በኅብስትና በወይን መባ አድርጎ እንደሚያቀርብ ቀድሞ የሚያበሥር ጸሎት ነው። ቅዱስ ቁርባን የመንገደኞች ለተጓዦች ማለት ለነጋድያን ኃይል የሚሰጥ ምግብ፣ በድካም እና ጉልበት በዛለበት ወቅት ኃይል የሚሰጥ ነው። በተለይ ደግሞ ለጴጥሮስ ምክንያቱም አንዴ ከተለወጠ በኋላ ወንድሞችን በእምነት እንዲያጸና የሚያበቃውም ቅዱስ ምሥጢር ነው። ወንጌላዊ ሉቃስ ጴጥሮስ ሦስቴ ኢየሱስን ከካደው በኋላ ዳግም ኃይል ተጎናጽፎ ከወደቀበት ተነሥቶ የእርሱን ዱካ እንዲከተል፣ ቀድመውና ፈጥነው የፈለጉት የኢየሱስ ዓይኖች ናቸው። (ሉቃ. 22፣ 60-61)
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ በቅዱስ ቁርባን ሱታፌ አማካኝነት፣ የክፋት መንፈስ በእያንዳንዳችን ድል እንዳይነሳና ሞትን የሚለውጥ እና የክርስቶስ ትንሳኤ ኃይል በእኛ ዘንድ እንዲሠራ የሚያደርግ ኢየፍሱስ የፈጸመው እና ካለ ማቋረጥ ለእያንዳንዳችን የሚያቀርበው ጸሎት በሚያስደንቅ ሁኔታ እንኖራለን። በቅዱስ ቁርባን ምሥጢር ቤተ ክርስትያን ለኢየሱስ ትእዛዝ መልስ ትሰጣለች፦ “ለእኔ መታሰቢያ አድርጉት” (ሉቃ. 22፣19፤ 1ቆር. 11፣ 24-26) በሚሉት ጸሎት አማካኝነም ምስጋናን እና ቡራኬ በማቅረብ ኅብስትን እና ወይን ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም የሚለውጠው ቃላት በትክክልኛና በፍጹም ተመሳሳይነት ትደግማለች። የእያንዳንዳችን ኅብስት እና ወይን ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስጋና ደም በሚለወጥበት ወቅት በቅዱስ ቁርባን የእየሱስ ጸሎት፣ ቅዱስ ቁርባኖች እንድሆን መሳባችን የሚያረጋገጥ ከእርሱ ጋር አንድ የሚያደርገን ጸሎት ነው።
ከጥንት ጀምሮ ቤተ ክርስትያን ኅብስትና ወይን ቀድሳ እና ባርካ በማቀረብ ተግባር የኢየሱስ ጸሎት መሆኑ ጠንቅቃ ታውቀዋለች። ከእርሱ ጋር በመሆን ለእግዚአብሔር ውለታ የሚቀርብ ክብር በመሬት ፍሬ የሰው ላብ ውጤት በሆነው እንደ አዲስ ከእግዚአብሔር ጸጋ ሆኖ እርሱም የኢየሱስ ሥጋና ደም የሆነው እግዚአብሔር በፍቅር ገዛ እራሱን በፍቃዱ የሚሰጥ ተቀባይ በሆነው ፍቅር አማካኝነት ትኖረዋለች(የናዝሬቱ ኢየሱስ ሁለተኛ ተከታታይ መጽሐፍ. ገጽ 146 ተመልከት)።
ከቅዱስ ቁርባን በመንደርደር በእግዚአብሔር ልጅ ሥጋው እና ደሙ ስንመገብ ጽሎታችንን በዚያች እንደ ሚሠዋው የፋሲ በግ ሆኖ በቀረበባት ሌሊት ጋር እናስተናብራለን፣ ምክንያቱን ምንም’ኳ ደካሞች ብንሆንም ሕይወታችን ጠፍታ እንዳትቀር እንድትለወጥም ነው።
ውዶቼ በምሥጢረ ንስኃ ለክርስትና ኅይወታችን መሠረታዊና የሁሉም ጸሎት የላቀው ፍጻሜ የሆነው የቅዱስ ቁርባን ሕይወት እንድንኖር እግዚአብሔር እንዲደግፈን እንለምነው። በዚያ የእግዚአብሔር መባ በጥልቅ አንድነትን ተጎናጽፈን ዕለታዊ መስቀሎቻችንን ነጻ ኃላፊነት በተሞላው ለእግዚአብሔር እና ለወንድሞች ፍቀር የሚለውጥ መሥዋዕት አድርገን ለማቀርብ እንድንችል እግዚአብሔር ደገፉን እንጠይቀው በማለት አስተምህሮውን ለማዳመጥ ቫቲካን በሚገኘው ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድተኛ የጉባኤ አደራሽ የተገኙት በብዙ ሺሕ የሚገመቱት ከተለያዩ አገሮች ለተወጣጡት ምእመናን በተልያዩ ቋንቋዎች ሰላምታን አቅርበው ሓዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ሸኝተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.