2012-01-09 16:26:06

ር ሊ ጳ በነዲክቶስ ለ16 ሕጻናት ምሥጢረ ጥምቀት ሰጡ ፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ትናትና ሰንበት በሲስቲና ቤተ ጸሎት ለ16 ሕጻናት ምሥስጢረ ጥምቀት ሰጥተዋል።

ሕጻናት ማስተማር ከባድ ነው እና የእምነት ምስክርነት ያስፈልጋል ብለዋል ቅድስነታቸው ሥርዓቱ በፈጸሙበት።

ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን በሥርዓተ ላቲን ጥምቀት እግዚእነ ባከበረችበት እና ቅድስነታቸው በሲስቲና ቤተ ጸሎት ሥርዓተ ቅዳሴ በመሩበት ግዜ ባሰሙት ስብከት ፡ ወላጆች በጸሎት እና በቤተ ክርስትያን ምሥስጢራት ታግዘው ለልጆቻቸው የእግዚአብሔር እውነተኛ ምስክሮች ለመሆን ይችላሉ ብለዋል።

አያይዘው የእግዚአብሔር ልጆች እንዲንሆን ክብር እና ኀይል የሚሰጠን እሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ እንደሆነም አስምረውበታል ።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ልጆችቻው ላስጠመቁ ወላጆች እንዳሉት ለልጆቻቸው የእግዚአብሔር ሐቀኛ ድምጽ መስማት ይችሉ ዘንድ በትጋት እንዲሰሩ ጠይቀዋል።

ሕጻናት ማስተማር አንድ ራሱ የቻለ ተልእኮ መሆኑ ያወሱት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ እምነተ እግዚአብሔር ምርኩስ በማድረግ ከተካሄደ ማራኪ እና ደስታ ሰጭ ተልእኮ እንደሆነ አስገንዝበዋል ።

ጸሎት እና የቤተ ክርስትያን ምሥጢራት ለቤተ ሰብ ነፍስ መሆናቸው እና ቤተ ሰቦች በጸሎት እና በመንፈሳውነት ተሸኝተው ሰላማዊ ሕይወት እንዲመሩ እና ለልጆቻቸው መልካም አርአያ እንዲሆኑም ወላጆችን ተማጽነዋል።

እውነተኛ መምህር ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ መሆኑ እና ህዝበ እግዚአብሔር ክርስቶስን እንዲከተል ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አሳስበዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ትናትና ሰንበት እኩለ ቀን ላይ በጽሕፈት ቤታቸው ሰገነት ብቅ ብለው በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ከተሰበሰቡ ምእመናን ጋር መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ደግመዋል ።

በመጨረሻም በቅርቡ የገባው አዲስ ዓመት 2012 እኤአ ለመላ የዓለም ህዝቦች ዓመተ ሰላም ዓመተ ፍትሕ ዓመተ እድገት እንዲሆን ተመኝተው እና ቡራኬ ሰጥተው ተሰናብተዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.