2012-01-02 14:28:33

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፥ “አሳዛኝ የዓለም መካራዎች እና ተስፋዎች ለእግዚአብሔር አደራ መስጠት።”


በላቲን ሥርዓት የጎርጎሪዮስ ባሕረ ሐሳብ መሠረት የአዲስ ዓመት መባቻ ቅድስተ ቅዱሳን አመ አምላክ ቅድስ ድንግል ማርያም በዓል የሚከበርበት ዕለት ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለዚህ ዓቢይ በዓል ዋዜማ በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ አንደኛ ጸሎተ ሠርክ መርተው “Te Deum-እግዚአብሔር ሆይ እንወድስሃለን” ማህሌት ሥርዓተ ጸሎተ በማቅረብ እና በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ወንጌላውያን የሚያወሱት RealAudioMP3 የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ታሪክ በራእይ እና በምስል ተቀርጾ ወደ ተቀመጠበት ግርግም የሕፃን ኢየሱስ ማርያም እና ዮሴፍ ሓውልት ዘንድ በሚደረገው የመንፈሳዊ ንግደት መሠረት መጠናቀቁ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።
እ.ኤ.አ. ዓውደ ዓመት 2012 ዓ.ም. ከእግዚአብሔር እጅ ለመረከብ “Te Deum-እግዚአብሔር ሆይ እንወድስሃለን” የተሰየመው የምስጋና ጸሎት ተዘይሞ ቅዱስ አባታችን “አሳዛኝ የዓለም መከራዎች እና ተስፋዎችን ለእግዚአብሔር አደራ መስጠት” የተገባ መሆኑ የሚያስገነዝብ የምስጋና መዝሙር መሆኑ በማስረዳት፣ እያንዳንዱ ዓመት ምድራዊ ሕይወት አጭር እና በፍጥነት የሚያከትም መሆኑ ያስገነዝበናል፣ ስለዚህ ይኸንን ግምት በመስጠት የዕለታዊ ሕይወታች ትርጉም በተለይ ደግሞ ስቃይ እና መከራ የሚፈራረቅበት የሕይወት ትርጉም ምንድር ነው የሚለው የኅልውና ትርጉም ለመሻት ያቀና መሠረታዊ ጥያቄ እንድናቀርብ ያስገድደናል፣ የዚህ ጥያቄ መልስም የዛሬ ሁለት ሺሕ ዓመት በቤተልሔም የተወለደው ዛሬም ኅያው የሆነው ኢየሱስ ነው ብለዋል።
በኢፍትኃዊነት በአመጽ እና በተንኮል ቸነፈር የሚሰቃየው ኅብረተሰብ በሚያስደንቅ ሁኔታ አዲስ ኃሴትና ነጻ የሚያወጣ ኢየሱስ ክርስቶስ መድኅን ትስብእት በልደቱ አማካኝነት የእግዚአብሔር ደግነት እና ቸርነት እንዲያስተውል እና እንዲያስተነትን አድርጎታል።
በዚህ ልደት አማካኝነት በማይመለሰው ወደ ፊት በሚለው ቀን የሚከሰተው ስቃይ እና መከራ ሁሉ ተጠራርጎ ገደብ የሌለው ለእግዚአብሔር አደራ የሚሰጥበት መሆኑና ዕለቱ መፈቀራችንን ያረጋገጥልናል፣ ስለዚህ የሰው ልጅ አለ ምንም ምክንያት የሚያልፍ ለሚመሰለው ጊዜ ባርያ ከመሆን ገላግሎታል፣ ይህ ለሰው ዘር አዲስ ዘለዓለማዊ የሆነው መጪ ሕይወት የሚያረጋገጥ ፍቅር መግለጫ ነው። ቤተ ክርስትያን ይኸንን እውነት በይፋ በማቅረብ በአዲስ መንፈስ ይኸንን አስደናቂውን ታሪክ ታበሥራለች።
የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት በሕይወታቸው እንዲሁም በሌሎች ሕይወት ጭምር እግዚአብሔርን የሚመለከት መሆናዊ ናፍቆት በማነቃቃታ፣ ለምን አምናለሁኝ ለሚለው ግላዊ ጥያቄ መልስ የሚሰጠ ቃል በደስታ ለመኖር እና ለመመስከር ተጠርተዋል። ስለዚህ የቤተ ክርስትያን እና የመላ ማኅበረ ክርስትያን የማያወላውል የተልእኮ አንኳር የሆነው ያ ሥጋ ሆኖ በመካከላችን ያደረው ቃል መመስከር የሚለው በታደሰ መንፈስ በመኖር በተለይ ደግሞ በተለያየ ምክንያት አቅጣጫውን ለመለየት ለሚሳነው በወቅታዊው የኤኮኖሚ ቀውስና በእጅጉ በከፋው የእሴቶች ቀውስ በተጋረጠበት ዓለም ለየት ባለ መልኩ የተጠቃው ወጣት ትውልድ፣ የሰው ዘር ታሪክ ማእከል እና ፍጻሜውን የሚገልጠው የመፍቻው ቁልፍ የሆነውን ኢየሱስን እንዲያውቅ ያስፈልጋል።
ክርስቶስ በሁሉም ዘንድ እንዲታወቅ በማድረግ ኅያው ማኅበረሰብ ለመገንባት በሚድረገው የእግዚአብሔር ቃል በዕለታዊ ሕይወት እንዲስተጋባ እግዚአብሔርን ላላወቁት ለማሳወቅ ከእግዚአብሔር ለራቁት ወደ እግዚአብሔር ለማቅረብ በሚፈጸመው የተልእኮ ጥረት በሮማዊት ቤተክርስትያን ሥር ተደራጅተው ዓቢይ አገልግሎት የሚሰጡ የእግዚአብሔር ሕይወት ተሳታፊያን የሚያደረገውን ቅዱሳት ሚሥጢራት በመኖር ምስክርነት የሚሰጡ ዓለማውያን ምእመናን መኖራቸው የሚመሰክር ዕለት ነው በማለት፣ ቅድስት ድንግል ማርያም Totus Tuus- ሁሉም ያንቺው ነው የሚለው የር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሐዋርያዊ መርህ የሚያጎላ የመለኮታዊ እቅድ አገልጋይ መሆናችን የሚገልጥ እና የሚኖር ዓቢይ የጥሪ ኃላፊነት መሠረት ለምንኖርበት ኅብረተሰብ አገልግሎት ለመስጠት ተጠርተናል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.