2011-12-30 14:02:42

ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ አዋጅ ዝክረ 50ኛው ዓመት


እ.ኤ.አ. ታህሳስ 25 ቀን 1961 ዓ.ም. ርሊ.ጳ. ዮሓንስ 23ኛ Humanae salutis - ሰብአዊ ድኅነት በሚል ርእስ ሥር በደረሱት ሐዋርያዊ ደንብ መሠረት ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ አዋጅ 50ኛ ዝክረ ዓመት ልክ ከአንድ ዓመት በኋላ በትክክል እ.ኤ.አ. ጥቅምት 11 ቀን 1962 ዓ.ም. በይፋ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ RealAudioMP3 ጅማሬ ከወዲሁ እ.ኤ.አ. በ 2012 ዓ.ም. 50ኛው ዓመት የሚታሰብ መሆኑም ሲገለጥ፣ ይኽ ጉባኤ የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ገጽ በይፋ ገሃድ ያደረገ እና ያደሰ ጭምር መሆኑ የቲዮሎጊያ እና የሥነ ኵላዊት ቤተ ክርስትያን ጉባኤ ሊቅ ማርኮ ቨርጎቲኒ ከቫቲካ ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ መለስ ብለን ሰብአዊ ድኅነት ሓዋርያዊ ደንብ ስናነብ ኵላዊት ቤተ ክርስትያን በጉባኤው አማካኝነት በዚያኑ ወቅት ለነበረው ዓለም ሳይሆን በአሁኑ ወቅት ጭምር ላለው በነቢያዊ መንፈስ ያነጣጠረ መሆኑ እናረጋገጣለን። የ900ዎች ዓመታት ሰብአዊ ማኅበራዊ ፖለቲካዊ ገጠመኞች እርሱም የዓለም ጦርነቶች የተለያዩ የፖለቲካ ርእዮተ ዓለም ያስከተሉት ችግሮች እና ጥለዉት ያለፈው ጠባሳ የተካፈለች ቤተ ክርስትያን ተስፈኛነት የተካነው ነቢይነት በማንጸባረቅ ለገዛ እራስዋ ቤተ ክርስትያንን ያደሰ ነው። ስለዚህ ር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ 23ኛ ለዚህ ኅዳሴ ዓቢይ አስተዋጽዖ እንዳላቸውም የሚያረጋገጥ ነው።
ሰብአዊ ድኅነት በተሰየመው ሐዋርያዊው ደንብ መሠረት ለመጀመሪያ ጊዜ ቁርጥ ያለ ወንጌላዊ አነጋገር መሠረት ክስተቶች እና ምልክቶች በወንጌል ሥር እንዲነበቡ ያነቃቃ፣ በሌላ አነጋገርም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስትያኑን ለማነቃቃት የሰጠው ወንጌላዊ መመሪያ እና በዚህ መመሪያውም መሠረትም ገዛ እራስዋ ከዓለም ታሪክ ጋር እንድታወያይ ያነቃቃት ነው። ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ መልካም ፈቃድ ላላቸው ጭምር የሚመለከት ነው። ስለዚህ በመለኮታዊ መድኅን ላይ የሚጸናው የማይታበለው እምነት የመሰከረ ብቻ ሳይሆን ይኽ የመዳን እቅድ ለሁሉም የሚመለከት መሆኑ ቤተ ክርስትያን ዳግም በታደሰ ቃል እና ሂደት የመሰከረ ጉባኤ ነው።
ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ፣ ር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ 23ኛ እንዳሉት ከዚህ ጉባኤ ቀደመው እንደ ተካሄዱት መናፍቃን እና የተለያዩ የመናፍቃን ቲዮሎጊያዊ እና ፍልስፍናዊ አመለካከት በይፋ ውድቅ ለማድረግ እና መናፍቃኑ ወደ ቤተ ክርስትያን እንዲመለሱ ከመጥራት አልያም ለማውገዝ ሳይሆን የሐዋርያዊ ግብረ ኖሎው ጉባኤ ነው። ስለዚህ በአዲስ ቃል እና ሕይወት ኵላዊው እና ግዜ ያማይሽረው ወንጌል ለማበሰር ያነቃቃ እና ያሳሰበ ለዚሁ ዓላማ መመሪያ በተለያየ መልኩ ያኖረ ጉባኤ ጭምር መሆኑ አብራርተው፣ ር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ 23ኛ ሰብአዊ ድኅነት በተሰየመው ሐዋርያዊ ደንብ አማካኝነት ጉባኤው ትንሽ ዘር በማለት ሲያስተዋውቁ ያ ዘር ተዘርቶ ይኸው አድጎ ዛፍ ሆኖ ፍሬ እየሰጠ ነው፣ በፍሬው ዙሪያ አስተንትኖ የምናደርግበት ወቅት ደርሰናል ካሉ በኋላ፣ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ፣ ቤተ ክርስትያንን የቤተ ክርስትያን ተልእኮ ለዛሬው ዓለም ያደሰ ነው፣ ይኸንን በመገንዘብ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ የወጠኑት በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 ውሳኔ መሠረት እውን የሆነው የዳግመ/አዲስ አስፍሆተ ወንጌል የሚከታተል ጳጳሳዊ ምክር ቤት ይመሰክረዋል በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.