2011-12-27 10:41:31

መልእኽተ ልደት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ትናትና ሰንበት በቅዱስ ጰጥሮስ ሰገነት ብቅ ብለው መልእኽተ ልደት አስተላልፈዋል።

ቅድስነታቸው ባስተላለፉት መልእክታቸው ላይ ፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር ከለዩን እኩይ ነገራት ሁሉ እንድያድነን መጣ ።



በነዲክቶስ 16ኛ ባስተላለፉት በዚሁ የልደት መልእክት በወቅቱ በዓለም ዙርያ በተለያዩ እክሎች በርሐብ በማሕበራዊ ግጭቶች በጦርነት ለሚሰቃዩ ሁሉ ክርስቶስ መለኮታዊ ምሕረቱ እንዲርላቸው ጠይቀዋል።

በስጋዌውን እና በልደቱ ሰማይንን ምድርን ያስታረቀ ሰውን እና እግዚአብሔርን ያገናኘ ክርስቶስ በዓለ ልደቱ ስናከብር ከፍተኛ ደስታ ይሰማናል ያሉት ቅዲኡስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በምድር ላይ ጥቅጥቅ ያለ ጨለማ ሰፍኖ ነበር በክርስቶስ ልደት ጨለማው ወደ ብርሃን መለወጡ በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ በብዙሺ የሚቆጠሩ ምእመናን አስታውሰዋል።

የንጽሕት ድንግል ማርያም ልጅ ለዘር ሰው ሁሉ መድኅን መሆኑ ጠቅሰው ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ዛሬ በዓለም ዙርያ የቤተልሔም የብርሃን ነጸብራቅ ታስተጋባለች ብለዋል።

የሰው ልጅ የእግዚአብሔር ችሮታ ካላገኘ ለብቻው የሚገጥሙትን አደጋዎች እና ችግሮች ለመወጣት እንደማይችል ክርስቶስ እጁ እንዲዘረጋለት መጠየቅ ተግድ ይለዋል ብለዋል።ለሰው ሁሉ እውነተኛ ብርሃን የሚያበራ ክርስቶስ ብቻ መሆኑ ቅድስነታቸው ባስተላለፉት መልእክተ ልደት አስገንዝበዋል።

አያይዘውም ልደት እንግዲህ ጨለማ ተወግዶ ብርሃን የታየበት ብርሃን የተገለጠበት ዕለተ ቀን መሆኑም አመልክተዋል።ብርሃን የገለጠ ክርስቶስ ራሱ ብርሃን የሆነ ክርስቶ ሕይወትም እንደሆነ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ትናትና ዕለት ባስተላለፉት የገና መልእክት አስታውቀዋል።

አያይዘው የሰው ሕይወት ምስጢር የሰው ዋጋ የሰው መጨረሻ ዕድል በክርስቶስ ብርሃን ሲተረጐም ብቻ እውነተኛ ፍቺ የሚያገኘው ብለዋል ።

በልደት ወቅት እንግዲህ መንገድ እውነት ሕይወት በበለ ደግሞ ብርሃን ሆኖ ሚመጣ ክርስቶስ ልባችንን እንከፍተለት በማለት በተጨማሪ አስገንዝበዋል።

ኢየሱስ ክርስቶስ ለኩሉ ሰብእ ሊያድን በእግዚአብሔር ፈጣሬ ኩሉ የተላከ መድኅን መሆንም በየልደት መልእክታቸው ገልጸዋል።

ከእግዚአብሔር መለየት ክፉን ደግ መለየት የሕይወት እና ሞት ባለቤት ለመሆን በሰው ልጅ ዘንድ የሚታየውን መፍጨርጨረ እኩይ መሆኑም አመልክተዋል።

ከእግዚአብሔር ቸርነት እና ፍላጎት የሚሆን ነገር እንደሌለ የሰው ልች ተክህሎ ውስን መሆኑንም ቅድስነታቸው አመልክተዋል።

ኢየሱስ ክርስቶስ ሐኪም መሆኑ እና እኛ ሰዎች ሕመምተኖች መሆናችንም ቅደነታቸው በተጨም አስገንዝበዋል።

ኦ ኀያል ክርስቶስ ና እና አድነን በለትም ክርስቶስን ተማጽነዋል ብ አነዲክቶስ 16ኛ በልደት መልእክታቸው ላይ ።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የአፍርቃ ቀንድ ሀገራት ህዝቦች የገጠማቸውን ርሐብ ማህበራዊ አለመረጋጋት ለስደት የተጋለጡ የዞኑ ስደተኞች አስታውሰው ዓለም አቀፍ ማሕበር ሰብ እንዲተባበር ጠይቀዋል።

በደቡባው ኤስያ ሀገራት ታይላንድ ፍሊፒን በውሃ ሙላት ለከፋ ሁኔታ የተጋለጡ ህዝቦችም እንዲሁ ዓለም አቀፍ ርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ቅድስነታቸው አሳስበዋል።

ቅድስነታቸው የልደት መልእክታቸው በማያያዝ በፍልስጤሞች እና እስራኤሎች የተጀመረው የውይይት ሂደት እንዲቀላጠፍ ሶርያ ላይ እየተካሄደ ያለውን ሁከት እና ግጭት እንዲገታ ጠይቀዋል።

በዒራቅ እና አፍቃኒስታን ዕርቀ ሰላም እና መረጋጋት እንዲኖር ቅድስነታቸው በሰሜናዊ አፍሪቃ እና መካከለኛው ምስራቅ ህንጽተ ሰላም እንዲጠናከር በምዕራባዊ ኣአፍሪቃ በዓበይት ሐይቆች መረጋጋት እንዲሰፍን በሚያንማር የፖሊቲካ መረጋጋት እንዲከሰት የሰሜን እና ደቡብ ሱዳን ህዝቦች መብት እንዲተበቅ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በልደት መልእክታቸው አመካይነት አሳስበዋል።



በመጨረሻም በግዕዝ ቋንቋ ጨምሮ በ65 የዓለም ቋንቋዎች Urbi et Orbi ለሮማ ከተማ እና ለመላ ዓለም ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተዋል ።

ዛሬ እኤአ ታሕሳስ 26 ቀን በላቲን ሥርዓተ አምልኮ በዓለ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቀዳሜ ሰማዕት ነው ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ከተሰበሰቡ 50 ሺ ምእመናን ጋር መልአከ እግዚአብሔር ጸለሎት ደግመዋል።

ከመልአክ እግዚአብሔር ጸሎት ፍጽሜ በኃላ ቅድስነታቸው ናይጀርያ ውስጥ የእስላም አክራሪዎች በሶስት አብያተ ክርስትያናት ላይ የወሰዱት የማጥቃት ርምጃ አስታውሰው በገና በዓል በክርስትይኖች ላይ የዓመጽ ተግባር መፈጸሙ እዥግ እንዳሳናቸው ገልጸዋል።

በአቡጃ አከባቢ የሚገኘው ማዳላ ላይ የቅድስት ተሬዛ ቤት ክርትያን በምእከላዊ ናይጀርያ ጆስ ላይ የሚገኘው ቤተ ክርትያን እና በሰሜናው ናያጀርያ ዮበ ክፍለ ሀገር ጋዳካ በተባለ ቦታ ሶስት ካቶሊካውያን አብያተ ክርስርትያናት የጥቃት ሰለባ መሆናቸው ተነግረዋል።

በዚሁ ጸረ አብያተ ክርስታያን የተካሄደ አስከፊ እና አሳፋሪ ትቃት እስካሁን ድረስ 27 ሰዎች ለሕልፈት መዳረጋቸው በርካታ መቁሰላቸው ክርእሰ ከተማ አቡጃ የመጣ ዚና አስታውቀዋል።

ቦኮ ሐራም የተባለ የእስላም ሽብርተኛ ቡድን የጥቃቱ ባለቤት እንደሆነ መግለጹ ይህ ከአቡጃ የመጣ ዜና አመልክተዋል።

ባለፈው ዓመት በገና ግዜ በመካከለኛው ናይጀርያ ጆስ ላይ 32 ሰዎች ገሎ 74 ማቁሰሉ የሚታወስ ነው ።

የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በልደተ ክርስቶስ የደስታ እና የሰላም ግዜ እንዲህ ዓይነት የጥላቻ ተግባር ሲፈጸም አሳዛኝ መሆኑ ጠቅሰው ቤተ ክርስትያን በዚሁ ትርጉም የለሽ ግድያ ሕይወታቸው ላጡ እንደምትጸልይ ገልጠዋል።

የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ለአብሮ በሰላም መኖር ተጻራሪ ተግባር እንዲገታም አጽንኦት ሰጥተው ጠይቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.