2011-12-21 14:44:56

ፊሊፒንስ፣ ዝናብ አዘል ኃይለኛው አውሎ ነፋስ ያስከተለው ጉዳት


በፊሊፒንስ ዋሺ የሚል ስያሜ የተሰጠው ኃይለኛው አውሎ ነፋስ በሰው እና በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት አስከትለዋል። በተከስተው የተፈጥሮ አደጋ ሳቢያ የሞት አደጋ ያጋጠማቸው RealAudioMP3 ብዛት ወደ አንድ ሺሕ መድረሱ ሲነገር፣ የአገሪቱ ርእሰ ብሔር በኒኞ አኵይኖ ዝናብ አዘል አውሎ ነፋሱ በተከሰተበት በፊሊፒንስ ሰሜናዊ የሚንዳናው ደሴት በስፋት በታየበት ክልል ብሔራዊ የተፈጥሮ መቅሰፍት አዋጅ መደንገጋቸው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት ሲያመለክት፣ በአውሎ ነፋሱ እጅግ የተጠቃው የካጋያን ደ ኦሮ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮ ለደስማ ለተጎዳው ሕዝብ መርጃ ድጋፍ እና ትብብር ጠይቀው መልካም ፈቃድ ያላቸው ሁሉ ዜጎች በዚሁ የሰብአዊ ድጋፍ እና ትብብር የመዋጮ እቅድ እንዲሳተፉ ጥሪ ማቅረባቸው የዜና አገልግሎት ይጠቁማል።
ስለ ተከተሰተው የተፈጥሮ አደጋ በማስመልከት ጳጳሳዊ የልኡካነ ወንጌል ማኅበር አባል በፊሊፒንስ በማገልገል ላይ የሚገኙት በኅብረ ሃይማኖት የጋራው ውይይት “ሲልሲላህ” በሚል የሚጠራው የሰላም እንቅስቃሴ ያቋቋሙት አባ ሰባስቲያኖ ዳምብራ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር በስልክ ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ እንዲህ ያለ የተፈጥሮ አደጋ ካሁን ቀደም በፊሊፒንስ አልታየም፣ አደጋው የተከስተው በሌሊት በመሆኑም ብዙ ሕዝብ ከአደጋው ገዛ እራሱን ለማዳን እድል አላገኘም፣ የሞት አደጋ ያጋጠማቸው ለይቶ አፈር አዳም ለማልበስ እጅግ አስቸጋሪ ሆነዋል፣ ስለዚህ ከዚህ አኳያ የደረሰው ዘርፈ ብዙ አደጋ ምንኛ አሳሳቢ መሆኑ ለመገመቱ አያዳግትም።
ለተጎዳው ሕዝብ በክልሉ የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በብፁዕ አቡነ ለደስማ በኩል የቤተ ክርስትያን የግብረ ሠናይ አገልግሎት ተቀናጅቶ ሰብአዊ አገልግሎት እያቀረበች መሆኗንም ጠቅሰው፣ ችግር እና ስቃይ ያስተባብራል፣ አለ ምንም የሃይማኖት እና የጎሳ ልዩነትም ሁሉ በመተባበር ላይ መሆኑ ገልጠው፣ የዳግመ ግንባታው እቅድ በጣም ሰፊ እና አድካሚ እንደሚሆን ከወዲሁ ሲገመት፣ ወላጅ አልባ የቀሩትን ሕፃናት ለመደገፍ እና ተገቢ መጠለያ በመስጠት አገልግሎት ቤተ ክርስትያን መሠማራትዋንም ገልጠው፣ ሁሉም ለተጎዳው ሕዝብ በጸሎት እና ድጋፍ በማቅረብ ይተባበር ዘንድ ጥሪ አቅርበው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.