2011-12-12 13:29:04

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ


ሁሌ እንደተመለመደው የቅድስት መንበር የዜና እና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በሳምት ማገባደጃ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ በመቀጠል፣ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ቅድስት መንበር የስደተኞች ጉዳይ ተንከባካቢ ዓለም ዓቀፍ ማኅበር RealAudioMP3 ሙሉ አባል አገር የሆነችበት ቀን ማአክል በማድረግ እሁድ ባቀረቡት ርእሰ ዓንቀጽ እንዳመለከቱት፣ በአለማችን ተከስቶ ያለው የኤኮኖሚ እና የቁጠባው ቀውስ የስደተኛው ጸአት እንዲቀንስ ሳይሆን በተለያየ መልኩ እጅግ ከፍ እንዲል የሚያደርገው መሆኑ ገልጠው፣ ለስደት ከሚዳርጉት ምክንያቶች አንዱ ድኽነት እንዲሁም የተፈጥሮ መዛባት እና ፖለቲካዊ ችግር የተሰኙትን ጠቅሰው፣ ከዚህ ሁሉ ችግር ለማምለጥ እና ሕይወትን ካደጋ ለማላቀቅ አስቦ ሕይወቱን ለአደጋ በማጋለጥ የሜዲትራኒያ የቀይ ባህር እና የሲናይ እንዲሁም የአሪዞና ምድረ በዳ ጉዞ የሚጋፈጠው ስደተኛ በማስታወስ፣ እነዚህን ስደተኞች እንዴት ተቀብሎ እና አስተናግዶ ሰብአዊ ክብር ተጠብቆለት ለመኖር እንዲቻል፣ ስደተኛው በጅምላዊ ቅድመ ፍርድ መመልከቱ የተለመደው ምርጫ አስወግዶ ተቀብሎ ማስተናገድ ወሳኝ ነው። ስለዚህ ዓለም አቀፍ ሰብአዊነት ማሳየል ተገቢ ነው ብለዋል።
ቅድስት መንበር ከጥንት ጀምራ ለስደተኛው የምትሰጠው እንክብካቤ እና ስለ ስደተኛው መብት እና ፈቃድ በመቆም የምታቀርበው አገልግሎት ግልጽ ነው። ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 12ኛ የስደተኛ ጉዳይ የሚከታተል የነዚህ የኅብረተሰብ ክፍል ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት እንዲቋቋም በማድረግ ብሎም ይህ ጳጳሳዊ ምክር ቤት በር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ ውሳኔ መሠረት በበለጠ ተጠናክሮ በዚሁ ዘርፍ የምትሰጠው አገልግሎት በሕዝባዊ ማኅበርነት ያላት ተሳትፎ ለማሳየል የዚህ ዓለም አቀፍ የስደተኞች እና ተፈናቃዮች ጉዳይ ድርጅት በታዛቢነት ደረጃ ሳይሆን ሙሉ አባል አገር ለመሆን በተደጋጋሚ ጥያቄ ስታቀርብ መቆየቷንም አባ ሎምባርዲ በርእሰ አንቀጹ ዘክረው፣ ቅድስት መንበር የሰው ልጅ ሰብአዊ መብት ክብር እና ፈቃድ ጠበቃ እንዲሁም በተለያዩ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የተራድኦ ማኅበሮችዋ አማካኝነት በሁሉም መስከ ቀዳሚ በመሆን የበለጠ ማኅበራዊ ሕይወት እንዲረጋገጥ ለሁሉም የመኖር እና የእድገት መብት እንዲረጋገጥ አገልግሎት እንደምትሰጥ አስታውሰው ርእሰ ዓንቀጹን አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.