2011-12-10 10:02:38

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ “ንጽህት ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር ጸጋ በምድር እንዲያንጸባርቅ ለማድረግ እንድንችል ወደ ሰማያተ ሰማይ ታቀርበናለች”።


ማርያም ለእግዚአብሔር “እነሆኝ…እንዳልከው ይሁንልኝ” በሚሉት የፍጹም ተአዝዞ ቃላቶችዋ አማካኝነት ሰማይ ለምድር ቅርብ እንዲሆን አደረገች። እኛም በእርሷ ድጋፍ አማካኝነትም ፍጹምነት ጸጋ በሕይወታችን ቦግ ብሎ እንዲያንጸባርቅ ማድረግ ይገባናል። በነዚህ ቃላት ሥር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 8 ቀን 2011 ዓ.ም. በላቲን ሥርዓት በተከበረው ዓመታዊ በዓለ ጽንሰታ ለማርያም RealAudioMP3 ምክንያት እኵለ ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በብዙ ሺህ የሚገመቱ ከውጭ እና ከውስጥ የመጡት ምእመናን በተገኙበት ከሐዋርያዊ መንበራቸው ካለው መስኮት ሆነው ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ከማሳረጋቸው ቀደም በማረግ አስተምህሮ እንዳቀረቡ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።
በዚህ ዓቢይ አመታዊ በዓለ ጽንሰታ ለማርያም የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ እ.ኤ.አ. ከ1958 ዓ.ም. በሮማ ከተማ በሚገኘው የስፓኛ አደባባይ ወዳለው የቅድስት ንጽሕት ድንግል ማርያም ሐወልት በቆመበት ሥፍራ በመሄድ ለክብርዋ አበባ የማኖር እና እዛው ለሚገኙት ምእመናን አስተምህሮ ማቅረብ እና ማርያማዊ ጸሎት በመድገም ሓዋርያዊ ቡራኬ የመስጠቱ ቅዱስ ባህል መሠረት ቅዱስ አባታችን ትላትና ወደ አደባባይ ስፓኛ በመሄድ በሮማ ከንቲባ እና የሮማ ክፍለ ሃገር መሥተዳድር አባላት እና ምእመናን አቀባበል ተደርጎላቸው አበባ በማኖር ከጥንት ጀምሮ ክርስትያናዊው አመለካከት እና አስተሳሰብ እግዚአሔር የልጁ እናት ለሆነቸው ማርያም የተገባው ጸጋ ፍጹምነት ለመግለጥ የሚጠቀምበት ቃላት ያለው ውስነት ባሻገር የተስተንፍሶ ቃላት በመሻት የማይገለጠውን ለመግለጥ ያደረገው ጥረት ቅዱስ አባታችን ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ ላቀረቡት አስተምህሮ መግቢያ በማድረግ፣ ከ1854 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ ዘጠነኛ ምኅረት እና ሓቅ ብቻ መንገዱ የሆነው፣ “ኢነፋቢሊስ ደውስ - ሊገለጥ የማይቻል እግዚአብሔር” በተሰየመው ሓዋርያዊ መልእክት ሥር በሰጡት ሐዋርያዊ ውሳኔ አማካኝነት የደነገጉት የማይሻር የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ክፍለ ዓንቀጸ ሃይማኖት “ጽንሰታ ለማርያም” እነሆ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 8 ቀን 2011 ዓ.ም. የላቲን ሥርዓት በምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የተከበረው ዓመታዊ በዓለ ጽንሰታ ለማርያም፣ ከዚህ ውሳኔ በፊት ከጥንት ጀምሮ ማኅበረ ክርስትያን በተለያየ መልኩ ይገልጠው የነበረው እግዚአብሔር እንከን የሌላት ከአዳም ኃጢአት ነጻ የመሆን ልዩ ምርጫ ለማርያም የተገባ ማድረጉ የሚገልጥ የእምነት ሐቅ ይፋዊ እውቅና እንደተሰጠው ሲያብራሩ፣ “ጸጋ የሞላሽ የሚለው መግለጫ በኃጢአታችን ያጣነውን ሕይወት እና ነጻነት ዳግም በአንዲያ ልጁ ትስብእት ሞት እና ትንሣኤ አማካኝነት ያጎናጸፈን የእዚአብሔር የሚያስደንቅ የፍቅር ተግባርን ነው የሚያመለክተው። ይኽ ከሁለተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በምሥራቅም በምዕራብም ቤተ ክርስትያን “እነሆኝ…እንዳልከው ይሁንልኝ” በተሰኙት የፍጹም ታዛዥነት ሕይወተ-ቃላቶችዋ አማካኝነት ሰማይን እና ምድርን ያቀራረበች መሆንዋ ታከብራለች ወደ እርስዋም ትማጠናለች” ብለዋል።
ይኸንን ለማረጋገጥም ጥንታውያን የክርስትያን ጸሓፍት ከሆኑት ውስጥ ቅዱስ ሶፍሮኒዮስ ዘእየሩሳሌም፣ ቅዱስ ቤዳ ዘክብሩ (እ.ኤ.አ. ከ 672 እስከ 735 ዓ.ም. የኖረ) እንዲሁም ቅድስት ሂልደጋርድ ዘቢንገን (እ.ኤ.አ ከ 1098 እስከ 1179 ዓ.ም. የኖረች) ዘክረው፣ የፍጹም ጸጋ ሥጦታ ለማርያም ብቻ ሳይሆን ለእኛም ተሰጥቶናል፣ ስለዚህ ይህ ፍጹም ጸጋ በእግዚአብሔር ቀድመን የታሰብን እንደ መሆናችን መጠን በሕይወታችንና በምድር ደምቆ እንዲበራ ማድረግ ይገባናል። ቅድስት ሂልደጋርድ ዘ ቢንገን “ቤተ ክርስትያን በምሥጢራዊው የመንፍስ ቅዱስ ኃይል አማካኝነት የምትጸንሳቸው እና የምትወልዳችው የእግዚአብሔር ልጆች ተብለው እንዲጠሩም ወደ እግዚአብሔር የምታቀርባቸው የሁሉም ክርስትያኖች ንጽሕት ድንግል እናት ነች” ያለቸውን ቃል አስታውሰዋል።
ቅዱስ አባታችን እ.ኤ.አ. ታህሳስ 8 ቀን 2011 ዓ.ም. በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ ልክ 16.30 ሰዓት ገደማ በዚህ ዓቢይ አመታዊ በዓለ ጽንሰታ ለማርያም የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ እ.ኤ.አ. ከ1958 ዓ.ም. በሮማ ከተማ በሚገኘው የስፓኛ አደባባይ ወዳለው የቅድስት ንጽሕት ድንግል ማርያም ሐወልት በቆመበት ሥፍራ በመሄድ ለክብርዋ አበባ በማኖር እና እዛው ለሚገኙት ምእመናን አስተምህሮ በማቅረብ፣ ማርያማዊ ጸሎት አሣርገው ሓዋርያዊ ቡራኬ የመስጠቱ ሥነ ሥርዓት መሠረት ወደ ክልሉ በመሄድ በሮማ ከተማ ከንቲባ በመንግሥት እና የፖለቲካ አበይት አካላት በብዙ ሺሕ የሚገመቱ ምእመና አቀባበል ተደርጎላቸው፣ ለማርያም ክብር አበባ በማኖር ባቀረቡት አስተምህሮ የማርያም መንፈሳዊነት ውበት ካዘየሙ ማኅሌታውያን ውስጥ ብዙውን ጊዜ የሚጠቀሰው ቅዱስ መርናርዶስ ዘ ኪያራቫለ (እ.ኤ.አ. ከ 1090 እስከ 1153 ዓ.ም. የኖረ) የቅዱስ ገብርኤል መልአክ ሰላምታ ለማርያም “ሰላም ላንቺ ኦ ማርያም ጸጋ የሞላሽ በእግዚአብሔር በቅዱሳት መላእክት በሰው ዘር ተወዳጅ እና ተቀባይነት ያለሽ ለእግዚአብሔር በትህትናዋ፣ ለቅዱሳት መላእክት በድንግልናዋ ለሰው ዘር በእናትነትዋ ተወዳጅ እና ተቀባይነት ያለሽ በማለት እንደገለጣት በማስታወስ ዮሓንስ ራእይ ምዕ. 12 ቍ. 1 “ከዚህ በኋላ አስደናቂው ምልክት በሰማይ አየ፤ ፀሐይን የለበሰች፥ ጨረቃን ከእግሯ በታች ያደረገች፥ ዓሥራ ሁለት ኮከቦችን እንደ አክሊል በራስዋ የደፋች አንዲት ሴታ ታየች።” የሚለው ራእያዊው ቃል ሥር ሥልጣናዊ ትምህርት እንዳቀረቡ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.