2011-12-05 14:49:14

ብፁዕ ካርዲናል ፐንጎ፥ “አፍሪካ ሙኑስ-የአፍሪቃ ቃለ መሐላ”።


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ከህዳር 16 ቀን እስከ ህዳር 20 ቀን 2011 ዓ.ም. በበኒን ባካሄዱት 22ኛው ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝት RealAudioMP3 ለአፍሪቃ ቤተ ክርስትያን አፍሪካ ሙኑስ-የአፍሪቃ ቃለ መሐላ የተሰየመው በአፍሪቃ ለምትገኘት ካቶሊካዊት ቤተ የለገሱት ሐዋርያዊ ምዕዳን በአፍሪቃ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የአስፍሆተ ወንጌል ተልእኮ በማደስ የሚያነቃቃ ሥልጣናዊ መርህ መሆኑ የመላ አፍሪቃ እና ማዳጋስካር የብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ ሊቀ መንበር በታንዛኒያ የዳረ ኤል ሰላም ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ፐንጎ፣ ሐዋርያዊ ምዕዳኑ በማስደገፍ በኮቱኑ እ.ኤ.አ. ከህዳር 21 ቀን እስከ ህዳር 23 ቀን 2011 ዓ.ም. የተካሄደው ጉባኤ ለማስጀመር ባሰሙት ንግግር እንዳመለከቱ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
ብፁዕነታቸው በተካሄደው ጉባኤ ባሰሙት ንግግር ዓለም አቀፍ የስደተኞች እና ተጓዦች ተንከባካቢ የካቶሊክ ድርገት፣ የሚሰቃዩት አቢያተ ክርስትያን ደጋፊ የግብረ ሠናይ ማኅበር በአፍሪቃ እና እንዲሁም ከመላ አፍሪቃ እና ማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ጉባኤ ጋር በመተባበር እና የዚህ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ጉባኤ የሚወጥናቸው የትብብር እና የሕንጸት እቅዶች እግር ላይ ለማዋል የሚፈጽመው የሚሰጡት ያልታከተ ድጋፍ በማስታወስ ማኅበራቱን ማመስገናቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት ካሰራጨው ዜና ለማወቅ ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.