2011-12-05 14:51:06

ለዘመነ ምጽአት የውህደት አንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን የበላይ መንፈሳዊ መሪ መልእክት


የውህደት አንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን የበላይ መንፈሳዊ መሪ የካንተርበርይ ሊቀ ጳጳሳት ክቡር ሮዋን ዊሊያምስ ለመላ አንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን ምእመናን ባስተላለፉት RealAudioMP3 የዘመነ ምጽአት መልእክት፣ የአንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን ውህደት ችግር ሳይሆን የእግዚአብሔር ጸጋ ነው። በዓለም ደረጃ ወቅታዊው የውህደት አንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሁኔታ እርሱም ቲዮሎጊያዊ ነክ ጥያቄዎች እና የተለያዩ አንግሊካውያን አቢያተ ክርስትያን የሚያንጸባርቁት የተለያየ ቲዮሎጊያዊ ነክ ሃሳቦችን ዳስሰው፣ በቅርቡ በማአክላዊ አፍሪቃ ክልል በምትገኘው አንግሊካዊት ቤተ ክርስያን ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት እና ከጳጳሳቱ እና ምእመናን ጋር ያካሄዱት ግኑኝነት ጠቀሰው፣ በአፍሪቃ ባካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት ወዳጅነትን እና ወንድማማችነትን በማረጋገጥ የወንድማማችነት ክብር በሙላት እንዲረጋገጥ የሚጠይቅ ሐሳብ በዚያ ክልል ከሚገኙት ቀርበው ከምእመናኑ እና ከጳጳሳቱ ለመረዳት እንደቻሉም ባስተላለፉት መልእክት እንዳሰመሩበት ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰየመው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ በትላትናው ኅትመቱ ይጠቁማል።
በተለይ ደግሞ በዚምባብዌ ባካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት ከኬፕ ታውን አንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሊቀ ጳጳስ ክቡር ቶሞ ሰሲል ማክጎባ እና እንዲሁም በሃራሬ የእግር ኳስ ሜዳ ምእመናን በተሳተፉበት በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ እና ጸሎት የእንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን ውህደት የማያጠያይቅ ዓላማ መሆን እንዳለበት ለመገንዘብ እንደቻሉ ጠቅሰው፣ በአፍሪቃ የሚታየው ድኽነት እንዲሁም በበለጸገው ዓለም የሚታየው የኤኮኖሚ ቀውስ እያስከተለው ያለው ማኅበራዊ ውጥረት አስታውሰው፣ ይኸ ሁሉ ችግር ለመፍታት ልዩነት ሳይሆን አንድነት ነው የሚበጀው፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚከተሉት ሁሉ ልዩነት ፈጽሞ መኖር የለበትም፣ የአንግሊካዊት ቤተ ርክስትያን ውህደት በሙላት መረጋገጥ በሁሉም አገሮች እና አካባቢዎች የምትገኘው አንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሊቀ ጳጳሳት እና አቡኖች የማያወላውል ፍላጎት መሆን አለበት እንዳሉ ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.