2011-12-02 15:25:05

የዓለም አቀፍ የተማሪዎች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ምክር ቤት ሶስተኛ ጉባኤ


የስደተኞች እና የተጓዦች ሓዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት የጠራው ከትላትና በስትያ ጀምሮ እ.ኤ.አ. እስከ ነገ ታህሳስ 3 ቀን 2011 ዓ.ም. የሚቀጥለው ዓለም አቀፍ የተማሪዎች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ምክር ቤት ሦስተኛው ጉባኤ፣ አስራ አራት ከኤውሮጳ ስምንት ከአሜሪካ አራት ከእስያ ሰባት ከአፍሪቃ ሶስት ከመካከለኛው ምሥራቅ በጠቅላላ ከ 36 አገሮች የተወጣጡ የተለያዩ አገሮች RealAudioMP3 የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የሰብአዊ እና የተማሪዎች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ድርገት ተጠሪዎች የመናብርተ ጥበብ ጸሎት ቤት እና አበ ነፍሳት ካህናት የተለያዩ ገዳማት እና መንፈሳዊ ማኅበራት እንዲሁም 30 ከተለያዩ አገሮች ከሚገኙት መናብርተ ጥበብ የተወጣጡ ተማሪዎች በጠቅላላ 135 ልኡካን በተጨማሪም ከኦርቶዶክስ ከአንግሊካዊት እና ከወንጌላዊት የሉተራን ኣቢያተ ክርስትያን የተወጣጡ ልኡካን እያሳተፈ መሆኑ የስደተኞች እና የተጓዦች ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮ ማሪያ ቨሊዮ ጉባኤ ከመጀመሩ ቀደም በማድረግ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አመልክተው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ ጉባኤውን በንግግር ሲከፍቱ፣ ጉባኤው እና ተጋባእያኑ ቤተ ክርስትያን ለተማሪዎች ለስደተኛ ተመሪዎች የተሟላ ሰብአዊ እና መንፈሳዊ እድገት መረጋገጥ የምትሰጠው አገልግሎት የሚመሰክር መሆኑ ጠቅሰው፣ የዚህ ሦስተኛው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ዓላማም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታየው ለትምህርት ያለመ እጅግ እየተሳፋፋ ያለው የተማሪዎች ከአገር ወደ አገር የመዘዋወሩ ጉዳይ የሚያስከትለው የባህሎች ግኑኝነት ማኅበራዊ ክስተት፣ መለያዊ ባህርያቱን ለመለየተ እና በጥልቀት ለመረዳት መሆኑ ብፁዕነታቸው ባሰሙት የመክፈቻ ንግግር አብራርተው፣ በአሁኑ ወቅት ካለችው ቤተ ክርስትያን የተማሪዎች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እንክብካቤ የባህሎች የልምዶች እና የሥልጣኔዎች የላቀው ኅብረ ዓይነቱን በመለየት የሚቀርብ አገልግሎት በመሆኑ ከዚህ አንጻር ኃላፊነቱ ከባድ መሆኑ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ያሉት ሐሳብ ዘክረው፣ ስለዚህ ጉባኤ በአዲሱ ሰብአዊነት ዙርያ የሚያደርገው ጥልቅ አስተንትኖ እና ጥናት ወቅታዊው ዘመን የሚያኖረው ዘርፈ ብዙ አቢይ ተጋርጦ ግምት በመስጠት እምነትን እና ባህልን በማጣመር የሚከናወን መሆን እንደሚገባው አሳስበው፣ ይኽ ደግሞ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እንዳሉት በአሁኑ ታሪካዊው ወቅት ባህላዊ እና መንፈሳዊነት ያጣመረ አዲስ ምርምር ተነቃቅተዋል ያሉትን ሐሳብ መሠረት ያደረገ ነው ብለዋል።
በዓለማዊንት ትሥሥር በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታየው ያልተረጋገጠው ፖለቲካዊ እና ሥነ ሕንጸት ሂደት ግምት የሰጠ ለተማሪዎች የሚቀርበው ሐዋርያዊ ግብረ ኖሎው አንገብጋቢ ነው፣ ወጣት ተማሪዎች ዘንድ የሚታየው ከአገር ወደ አገር የመዘዋወሩ ማኅበራዊ እና ሰብአዊ ክስተት በፖለቲካው በማኅበራዊው እና በኤኮኖሚው ዘርፍ በሚነሳበት አገር እና በሚስተናገድበተ አገር በተለይ ደግሞ ለቤተ ክርስትያን ተጨባጭ አቢይ ጥቅም ያለው ጉዳይ ከመሆኑ ባሻገር ጥያቄ እና ተጋርጦም ጭምር ነው። የሚያቀርበው ማኅበራዊ ሰብአዊ እና ኤኮኖሚያዊ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ጥያቄው በመለየት፣ በተለያየ መልኩ የቤተ ክርስትያን መሠረታዊው ትምህርት ሥር መልስ ለመስጠት የሚችል ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እጅግ አስፈላጊ ነው ካሉ በኋላ በአሁኑ ወቅት ከቦታ ቦታ የሚዘዋወሩ የተማሪዎች ብዛት ወደ ሦስት ሚሊዮን የሚጠጋ መሆኑም ገልጠው እ.ኤ.አ በ 2025 ዓ.ም. ወደ ሰባት ሚሊዮን ከፍ ሊል እንደሚችል መግለጣቸውም የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቅ።







All the contents on this site are copyrighted ©.