2011-11-29 10:30:01

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እግዚአብሔርን እና ዓለምን ከማፍቀር ለተኖረው ስቃይ አርአያ


“የር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሥልጣናዊ ትምርህት መሠረት የጤና ጥበቃ ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ለሕይወት አገልግሎት” በሚል ርእስ ሥር የተመራ የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያዘጋጀው 26ኛው ዓለም አቀፍ ዓመታዊ ምልኡ ጉባኤ እ.ኤ.አ. ከህዳር 24 ቀን እስከ ህዳር 26 ቀን 2011 ዓ.ም. RealAudioMP3 በአገረ ቫቲካን በሚገኘው በአዲሱ የሲኖዶስ አዳራሽ መካሄዱ ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ከተለያዩ 70 አገሮች የተወጣጡ 40 ብፁዓን ጳጳሳት ያካተተ በጠቅላላ 685 ተጋባእያን ቅዳሜ በቫቲካን ተቀብለው በሰጡት መሪ ቃል መጠናቀቁም የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ቅዱስነታቸው በሰጡት መሪ ቃል፣ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በድካምነት ያለውን ኃይል የመሰከሩት፣ የጤና ጥበቃ አገልግሎት፣ መድኅን ከሆነው ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይ የሚመነጭ ወንጌላዊ ራእይ ያለው ነው ካሉ በኋላ፣ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ በጣረ ሞት የነበረው የመድህን ገጽ፣ ከአብ ጋር ኅልው የሆነው ወልድ እንደ ሰው ስለ እኛ የተሰቃየው፣ በእግዚአብሔር አምሳያ እና አርአያ የተፈጠረው ለዘለዓለማዊ ሕይወት ለጠራው የእያንዳንዱ ሰው ልጅ ክብር እና እሴት በሁሉም ደረጃና በማንኛው የሕይወት ሁናቴ፣ ሕይወትን እንድንከባከብና እንድናነቃቃ ያስተምረናል ብለዋል።
ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የአካል መድከም፣ በነበራቸው ጽኑ እና የተረጋገጠ እምነት አማካኝነት ታውዶ፣ ኅመም በክርስቶስ በቀራንዮ የሥቃይ ጉዞ ሱታፌ በማድረግ፣ እግዚአብሔርን ቤተ ክርስትያንና ዓለምን በማፍቅር በተጨባጭ እንደኖሩት ቅዱስ አባታችን አብራርተው፣ እለት በእለት መስቀሉን ተሸክሞ እስከ ፍጻሜ ይከተለኝ የሚለው የጌታችን ተከታይ የመሆን ጥሪ የሚጠይቀው ሱታፌ፣ ብፁዕ ዮሐንስ ጵውሎስ ዳግማዊ የኖሩት፣ ይኽ ደግሞ እንደ መምህር እና ጌታ ከመስቀል ላይ ውሎ ለሁሉም ሰው ዘር መስህብ ማራኪ እና የድኅነት እንዲሁም የክብሩ ምልክት ሆኖ መገኘት የሚል ፍጻሜ ያለው ነው።
የሥቃይ ምሥጢር፣ እንግዳ የተለየ እንዳውም የሰው ዘር ስቃይ ምክንያት ተብሎ ጣት ተቀስሮበት የእግዚአብሔር ገጽ የጋረደ ቢመስልም፣ የጥልቅ እምነት ዓይኖች ግን ይኸንን ምሥጢር በጥልቀት ለመገንዘብ መሠረት ነው። እግዚአብሔር በትስብእቱ ለሰው ልጅ ቅርብ በመሆን በማንኛውም የመከራ ወቅት ስቃይን ሳያስወግድ ከሞት በተነሳው ስቁል፣ በእግዚአብሔር ልጅነት እስከ ሞት በመስቀል እስከ መሞት መከራን በመቀበል፣ ፍቅሩን ልሰው ልጅ ተስፋን ለመስጠት እጅግ ጥልቅ ወደ ሆነው የሰው ልጅ አዘቅት ድረስ ዝቅ የሚል መሆኑ ገልጦልናል በማለት፣ እ.ኤ.አ. በ 1984 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጵውሎስ ዳግማዊ “ሳልቪፊቺ ዶሎሪስ-የሚያድን ስቃይ እርሱም ስቃይ ያለው የማዳን ክብር የሚያብራራ የደረሱት ሐዋርያዊ ምዕዳን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በማስታወስ ስቃይ እና ኅመም ኢምክንያታዊ የማድረጉ አዝማሚያ ፊት የሥቃይ ክርስትያናዊው ትርጉም በቃል እና በሕይወት ያስተማሩ መሆናቸውንም ዘክረው፣ ይህ በብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እ.ኤ.አ. በ 1985 ዓ.ም. የተቋቋመው የጤና ጥበቃ እና የጤን ባለ ሙያዎች ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት፣ በተለያዩ የቤተ ክርስትያን የጤና ጥበቃ አገልግሎት አማካኝነት የሚያስተምረው እና በድኾች አገሮች የሚሰጠው የተሟላ አገልግሎት የሚደነቅ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.