2011-11-21 15:30:09

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በበኒን ለመላ አፍሪቃ ያስተላለፉት “የተስፋ” ቃል


የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ 22ኛው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ዓለም ዓቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝት ርእስ ሥር ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በበኒን ቅዱስ አባታችን ለመላ አፍሪቃ ያስተላለፉት RealAudioMP3 መልእክት እና በአፍሪቃ ለምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የሰጡት ሐዋርያዊ ምዕዳን ድህረ ሲኖዶስ ጭምር ተስፋ ማእከል ያደረገ ነው።
በሌሎች ክፍለ ዓለም በተለይ ደግሞ በአፍሪቃ አሁንም አሉታዊ ክስተቶች የሚታዩ ቢሆንም ቅሉ በዚያች ክፍለ ዓለም አወንታዊ ፍጻሜዎች እንዳሉ መዘንጋት የለብንም፣ ስለዚህ አፍሪቃ ባላት ማኅበራዊ እና የተፈጥሮ ሃብት አማካኝነት ፍትህ ሰላም እና እርቅ መሠረት በማድረግ ገዛ እራስዋ በበለጠ ለማነጽ እንደምትችል ነው፣ ይኸንን ያላታ ዘርፈ ብዙ ሃብት በፍትህ ለመጠቀም እንድትችል በአፍሪቃ የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ወንጌላዊው የክርስትናው ተስፋ በቃል እና በሕይወት እንዲመሰከር ያስገነዘበ ሐውርያዊ ጉብኝት መሆኑ አብራርተዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሐዋርያዊ ምዕዳን ድህረ ሲኖዶስ በአፍሪቃ ለምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ሲያስረክቡ፣ የተካሄደው ሲኖዶስ ውሳኔዎች እግብር ላይ እንዲውል የሚያበቃ ነው። በዚህ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሐዋርያዊ ምዕዳን መሠረት የአፍሪቃው ሁለተኛው የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ቅድመ ዝግጅት የሲኖዱ ሂደት እና ያጸደቀው ሰነድ እግብር ላይ እንዲውል መከተል የሚያስፈልገው መሠረታዊ መንገድ የሚያመለክት ብቻ ሳይሆን፣ አንዳንድ ሥልጣናዊ ሀሳብ እና አስተያየት ጭምር ያካተተ፣ የአፍሪቃ የእርቅ ዓመት፣ የእርቅ ሳምንት መርሃ ግብር እንዲኖር የሚጠይቅ፣ በአፍሪቃ ፍትሕ ሰላም እና እርቅ ለማረጋገጥ የሚያግዙ ተጨባጭ መርሃ ግብር የሚያመለክትም መሆኑ አባ ሎምባርዲ አብራርተዋል።
በዚህ ሐዋርያዊ ጉብኝት ቅዱስ አባታችን ከመንግሥት አካላት እንዲሁም በአፍሪቃ በሚታየው የተስተካከለ መንግሥታዊ መስተዳድር እጥረት ሰለባ ከሆኑት ሕፃናት ጋር በመገናኘት የአፍሪቃ መንግሥታት የሕዝባችሁ ተስፋ እና መጪ ሕይወት አትንፈጉ፣ ተስፋ እና ብሩህ ተስፋ የጨለመው አታድርጉ፣ ይህ ጥሪ የነገ ታሪክ ተረካቢ ትውልድ ጉዳይ የሚመለከት እና ለዚህ ትውልድ የተሟላ ድጋፍ ይቀርብ ዘንድ የሚያሳስብ መልእክትም ነው። በአንድ መልኩ ግብረ ገባዊ እና ሥነ ምግባራዊ ጽናት የተሞላው ቃል ለፖለቲካ አካላት ሲያስተላልፉ በዚህ መልእክት ሥር አባታዊ መንፈስ የጎላበት በአይን አማካኝነት ወደ ልብ የሚሻገሩትን ሕፃናት በማሰብ መሆናቸውም አብራርተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.