2011-11-21 15:26:53

ብፁዕ አቡነ ኤተሮቪች፦ “ኢየሱስ አፍሪቃን ከተለያዩ ባርነት ነጻ ያወጣል”


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የዛሬ ሁለት ዓመት በፊት እዚህ በአገረ ቫቲካን እርቅ ፍትሕ እና ሰላም በሚል ርእስ ተመርቶ የተካሄደው ሁለተኛው የመላ አፍሪቃ እና ማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ያጸደቀው ሰነድ መሠረት የደረሱት ሐዋርያዊ ምዕዳን በዚህ በቤኒን ባካሄዱት RealAudioMP3 22ኛው ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝት ወቅት ለአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት በይፋ ማስረከባቸው የሚታወቅ ሲሆን፣ የዚህ ሐዋርያዊ ምዕዳን ይዞታ በማስመልከት የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ኒኮላ ኤተሮቪች ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በአፍሪቃ የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እንድትኖር እና አገልግሎት እንድትፍጽም እግዚአብሔር በጠራት ኅብረተሰብ ዘንድ የሰላም መሣሪያ የፍትህ ገንቢ ሆና እንድትገኝ ከእግዚአብሔር እና ከባለንጀራ ጋር የሚል ተጨባጭ እርቅ እንድትኖር የተጠራች መሆንዋ የሚያስገነዝብ ነው። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በአፍሪቃ ያለችው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ለሚቀጥሉት 10 ዓመታት ለምትከተለው ሐውርያዊ ግብረ ኖልዎ እግብር ላይ ለማዋል የሚያግዛት ተጨባጭ ምዕዳን የሰጡበት፣ ወደ አሕዛብ ከሚለው መርህ የተንደረደረ ኢየሱስ ክርስቶስ ገና ወዳላወቁት የማድረስ የተልእኮ ኃላፊነት የሚያሳስብ ነው። የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት እርቅ ፍትህ እና ሰላም ለማረጋገጥ ያለመ አስፍሆተ ወንጌል ያነቃቁ ዘንድ የሚጠቅም ነው ብለዋል።
በወንጌል ብርሃን የተመሩ እና በቤተ ክርስትያን ዓንቀጸ ሃይማኖት የማኅበራዊ ጉዳይ ትምህርት ሥር በሚገባ የታነጹ ዓለማውያን ምእመናን በቤተሰብ በማኅብረተ-ሰብ በጠቅላላ በአፍሪቃ የወንጌል ብርሃን እንዲያደርሱ ብርሃን እና ጨው ሆነው እንዲገኙ የሚጠራ፣ ሁሉም ይፋዊ ምስክርነት መስጠት በሚኖርበት በሚተዳደርበት የሙያ ዘርፍ እውነኛ ምስርክ እንዲሆን የሚያሳስብ፣ የአፍሪቃ ሁለተኛው ይፋዊ ሲኖዶስ እንዳሰመረበትም፣ አፍሪቃ ከተለያዩ ኋላ ቀር ባህላዊ ልምዶች ሥር የሚጠቃለሉት ወደ ፊት እንዳትል ከሚያደርጉዋት ጎጂ ልምዶች “ባርነት” ክርስቶስ ነጻ እንደሚያወጣት ያለው እርግጠኝነት መኖር የሚጠይቀውን ሃሳብ ዳግም የተሰመረበተ ሐዋርያዊ ምዕዳን ነው ብለዋል።
በዓለም በተለይ ደግሞ በአፍሪቃ የሚታየው ውጥረት ዓመጽ ጨርሶ በሙላት እንዲወገድ የሚያደረገው ብሥራተ ወንጌል መሆኑ የማያጠራጥር ነው። ስለዚህ ቤተ ክርስትያን በአፍሪቃ የእርቅ የፍትህ እና የሰላም ወንጌል አብሳሪነት ትበረታ ዘንድ የሚያስገንዘብ፣ የዚህ ተልእኮ ተቀዳሚው ዓላማ፣ በቃል እና በሕይወት ምስክር ሆና እንዲትገኝ በተለያየ መልኩ የሚያስገነዝብ ምዕዳን ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.