2011-11-21 15:23:28

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ብሥራተ ወንጌል በጋለ ስሜት ማነቃቃት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. ከ ከህዳር 18 ቀን እስነ ህዳር 20 ቀን 2011 ዓ.ም. በአፍርቃዊት አገረ በኒን ባካሄዱት 22ኛው ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝት በርእሰ ከተማ ኮቶኑ በሚገኘው በቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ሕንፃ እ.ኤ.አ. ህዳር 19 ቀን 2011 ዓ.ም. ከአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት RealAudioMP3 ጋር በመገናኘት በሰጡት ሥልጣናዊ ምዕዳን፣ አስቀድመው የተደረገላቸው የሞቀው ልባዊ አቀባበል አፍሪቃዊ አቀባበል ብለው በመሰየም፣ በዚህ ሐዋርያዊ ጉብኝት በተገኙበት ሥፍራ እና ባለፉበት መንገድ ሁሉ ሕዝብ ከጎናቸው ሳይለይ እንደሸኛቸው ጠቅሰው፣ ከልብ አመስግነው ለዚህ ሁሉ መረጋገጥ ምክንያት የሆነው የዛሬ 150 ዓመት በፊት በአገሪቱ የተከናወነው ለክርስቶስ ፍቅር የሕይወት መሥዋዕትነት የጠየቀው ወንጌላዊ ተልእኮ እና ብሥራተ ወንጌል መሆኑ ዘክረው፣ የቤኒን ካቶሊክ ምእመን፣ ማንም በኢየሱስ ክርስቶስ ያለው እምነት በቤተ ክርስትያን እና ከቤተ ክርስትያን ቅጥር ግቢ ውጭም ከመመስከር ኃላፊነት ሳያፈገፍግ ለወንጌላዊ ተልእኮ ግንዝቤ እና ኃይል በመስጠት በግብረ ወንጌላዊ ተልእኮ ይሳተፍ ዘንድ አሳስበዋል። ስለዚህ ቤተ ክርስትያን የክርስቶስን ወንጌል የተቀበሉትን በሚንከባከብ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እንደማትታጠር ቅዱስነታቸው በመግለጥ በጋለ ስሜት የሚነቃቃው ወንጌላዊ ልኡክነት የአንድ ማኅበረ ክርስትያን ብስለት የሚመሰክር ነው ብለዋል።
ቤተ ክርስትያን የእግዚአብሔር ቃል ለገዛ እራስዋ እና በገዛ እራስዋ ውስጥ ለማቀብ ሳይሆን፣ ወንጌል ለዓለም ማሳወቅ የሚል የተልእኮ ጥሪ የተቀበለች ነች። በቤተ ክርስትያን ተልእኮ ማለትም በአስፍሆተ ወንጌል ተልእኮ ልዩ ሚና ያላቸው ዓለማውያን ምእመናን ዘክረው፣ ብሥራተ ወንጌል ያለው ነቢይነት አድማስ አዲስ ኃይል የሚያሰጠው ቀጣይ መለወጥ የሚለው ተግባር በተካነው መንፈስ ይኖሩትም ዘንድ አደራ በማለት፣ ብፁዓን ጳጳሳት እንደ የእግዚአብሔር ልብ እረኞች በመሆን እውነተኞች የወንጌል አገልጋዮች ይሆኑም ዘንድ በማሳሰብ፣ ሕዝብ ከእነርሱ የሚጠብቀውም ይኸንን ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.