2011-11-21 16:30:56

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ከበኒን ሐዋርያዊ ጉብኝት ወደ መንብራቸው ተመልሰዋል፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ በምዕራባዊ አፍሪቃ በኒን ላይ የሶስት ቀናት ሐዋርያዊ ዑደት ፈጽመው ትናትና አምሻቸው ወደ ሐዋርያዊ መንበራቸው በሰላም ተመልሰዋል ።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የበኒን ሐዋርያዊ ዑደታቸው ከማጠቃለላቸው በፊት ርፋድ ላይ ኮቶኑ ላይ በሚገኘው ላሚቲ ስታድዮም በሁለት መቶ የአፍሪቃ ጳጳሳት እና በሺ በሚቆጠሩ ካህናት ተሸኝተው ሥርዓተ ቅዳሴ መርተዋል።

የሀገሪቱ መንግስት መሪ ፕረሲዳንት ቶማስ ያዪ ቦኚ ጨምሮ የመንግስት ባለስልጣናት የተሳተፉ ሲሆን ሰማንያ ሺ ህዝብ የሥርዓተ ቅዳሴ ተሳታፊ መሆኑ ታውቆዋል።

ከተጓራች ሀገራት ከኒጀር ቶጎ ጋና እና ቡሪኪና ፋሶ በርካታ ምእመናን በዚሁ ሥርዓተ ቅዳሴ ተሳታፊ መሆናቸው ተመልክተዋል።

ከሥርዓተ ቅዳሴ ፍጻሜ በኃላም ሐዋርያዊ ሰነደ ምእዳን ለአፍሪቃ ጳጳሳት አስረክበዋል።

ዛሬ ያሳረግነው ሥርዓተ ቅዳሴ ሁለተኛ የአፍሪቃ ጳጳሳት ሲኖዶስ ለማቃናት የረዳን እግዚአብሔርን ለማመስገን ነው ያሉት ርእሰ ሊቃነ ጳጳጳሳት በነዲክቶ የሐዋርያዊ ሰነደ ምእዳኑ ይዘታ ለአፍሪቃ ይረዳ ዘንዳ ያላቸውን ምኞት ገልጠዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ለአፍሪቃ ያስረከቡት ሐዋርያዊ ሰነደ -ምእዳን በ2009 እዚህ ቫቲካን ውስጥ የአፍሪቃ ቤተ ክርስትያን ለዕርቅ ሰላም እና ፍትሕ በተሰኘው መሪ ቃል የተካሄደውን ሁለተኛ የአፍሪቃ ጳጳሳት ሲኖዶስ እልባት መሆኑ የሚታወስ ነው ።

ይሁን እና ቅድስነታቸው በኮቶኑ ላሚቲ በተሰኘው ስታድዮም ሥርዓተ ቅዳሴ ሲመሩ ባሰሙት ስብከት እንዳመለከቱት ፡ ከኔ በፊት የነበሩ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ዱካ በመከተል ለሁለተኛ ግዜ በአፍሪቃ ሐዋርያዊ ዑደት ሳከናውን እና የሰላም እና ተስፋ መልእክት ሳስተላልፍላችሁ ጥልቅ ደስታ ይሰማኛል ።

በማያያዝ በአጠቃላይ በዚሁ ሥርዓተ ቅዳሴ ለተሳተፋችሁ ብጹዓን ካርዲናላት ጳጳሳት ካህናት ድንግሎች እና ምእመናን አመሰግናለሁኝ ከበኒን ውጭ ። ከቡርኪና ፋሶ ከኒጀር እና ከቶጎ በመምጣት በዚሁ በኒን ውስጥ ቅዱስ ወንጌል የተበሰረበት 150ኛ ዓመት እና ሐዋርያዊ ሰነደ ምዕዳን ርክክብ የተገኛችሁ ሁሉ ምስጋናየ ይድረሳችሁ ብለዋል።

በዚሁ ሥርዓተ ቅዳሴ የተሰማው ቅዱስ ወንጌል እንደሚነግረን ይሰው ልጅ ክርስቶስ የመጨረሻ የሕወታንች ዳኛ ነው። እሱ የተራቡ የተጠሙ እና የታመሙ በአጠቃላይ የተቸገሩ ተምሳሌት መሆኑ አስረድቶናል ።

ስለሆነም እና እሱ ለነሱ ያደረገውን እንክብካቤ እና ሐሳቢነት መከተል ይጠበቅብናል ያሉት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር እያለ ሰው ሆነ ብለዋል በስብከታቸው አያይዘው ። ክርስቶስ ለሰው ድህነት ብሎ ተሰቃየ ተሰቀለ ሞተ አክለውበታል።

ከሁለት ሺ ዓመታት በኃላ የሰው ልጅ መድኀኔ ኩሉ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ጐን ትቶ ወይም ረስቶ ለስልጣን እና ለገንዘብ ትኩረት ሰጥቶ ሲራመድ ይታያል ያላይ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ምሥጢረ ጥምቀት የተቀበለ ክርስቶስን ለመከተል ሲውስን ወደ ኀይለኛ ችግር ሊመራው እንድያውም መስውዕት ሊሆን ይችላል ።

ቅዱስ ጳውሎስ እንደሚያስታውሰን ክርስቶስ ለሞት አሸንፎ ተነስተዋል እና እኛም አብረነው መነሳት አለብን ብለዋል።

አፍሪቃ አሉ በነዲክቶስ 16ኛ አፍሪቃ መካነ ሰብአዊ ሳንባ መሆንዋ አውስተው፡ ክርስትያናዊ እሴቶችዋ ትጠብቅ ዘንዳ አሳሰበዋል ።

በክርስቶስ በመተማመን ሕይወታችን ከመራን እሱ ለሰላም ለዕርቅ እና ፍትሕ እንቅፋት የሆኑ ሁሉ ያስወግዳል ብለዋል በነዲክቶስ 16ኛ ።

በመጨረሻም ሥርዓተ ቅዳሴ ከተከታተለ ህዝብ ጋር የሑድ መልአከ እግዚአብሔ ጸሎት ደግመዋል።

በበኒን ኮቶኑ ላይ በሚገኘው አሚቲ ስታድዮም የተካሄደው ሥርዓተ ቅዳሴ እንደተጠናቀቀ ወደ ቤተ ጵጵስና ሐዋርያዊ ወኪል ተመልሰው ከየአፍሪቃ ጳጳሳት ለምሳ ተቀምጠዋል።

ከሰዓት በኃላም ከጳጳሳቱ ተሰናብተው ወደ ካርዲናል ጋንተን አውሮፕላን ማረፍያ

ተጉዘው እዚያው ከቤተ ክርስትያን እና የሀገሪቱ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ተሰናብተው ወደ ሐዋርያዊ መንበራቸው ተመልሰዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ከትናትና ወድያ በርእሰ ከተማ ኮቶኑ የሚገኘው የቅድስት ሪታ ካተድራል የፍቅር ልዑካን ድንግሎች ማሕበር ከሚንከባከብዋቸው ከሕጻናት ጋር ተገናኝተው ጸልየዋል ተወያይተዋልም።

በዚሁ ካተድራል የሚገኙ ሕጻናት በመዝሙር እና በደስታ ቅድነታቸውን የተቀበልዋቸው ሲሆን ፡ ድንግሎቹ የሚንከባከብዋቸው ሕጻናት ድሆች እና ሕሙማን መሆናቸው ይታወቃል።

ሁለት ሕጻናት ለቅድስነታቸው የእንኳን ደህና መጡ ንግግር ያሰሙ ሲሆን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በርካታ ሕጻናት አቅፈው በመሳም ለእነሱ ያላቸውን ፍቅር ገልጸዋል።

የመጀመርያ ቅዱስ ቁርባን ከተቀበልን በኃላ ክርስቶስ ከኛ ጋር ይኖራል ክርስቶስ ይወደናል በመላ ዓለም በሚገኙ መንበረ ታቦቶች ይገኛል እዚህ መንበረ ታቦትርም ከኛ ይገኛል በየግዜው ጠይቁት እና እንደምትወዱት ንገሩት ።

እሱም እንደሚወዳችሁ በተለያዩ መንገዶች ይገልጥላችሃል ብለዋል ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ። አያይዘውም ጸሎት ማድረግ የእግዚአብሔር ፍቅር ጭሆት መሆኑ ጠቅስው ሕጻናቱ እንዲጸልዩ መክረዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በኒን ቆይታቸው የብጹዕ ካርዲናል በርናርደን ጋንተን መቃብር ጐብኝተዋል ጸልየዋልም።








All the contents on this site are copyrighted ©.