2011-11-15 10:16:52

የር.ሊ.ጳ ጉባኤ መልአከ እግዚአብሔር አስተምህሮ (13.11.11)


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ትናንትና በቅዱስ ጴጥሮስ ባቀረቡት የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ “ከእግዚአብሔር የምንቀበላቸው ስጦታዎች እንደመብታችን ማሰብ ቂልነት ነው፣ ከዚሁ የባሰ ደግሞ በሚገባ መጠቀማቸውን እምቢ ያልን እንደሆነ ደግሞ የህልውናችን ዓላማ አለምዋምዋላት ነው” ሲሉ እንደ ላቲኑ ሥርዓተ አምልኮ ትናንትና ከወንጌለ ማቴዎስ 25፤14 የተነበበውን ስለ ለሶስት አገልጋዮች የተሰጡ መክሊቶችና ሁለቱ ሲያተርፉ ሶስተኛው የተቀበለውን ገንዘብ ቀብሮ ባለንብረቱ በጠየቀበት ግዜ ምንም ሳላፈራ ገንዘቡን የመለሰለት ምሳሌ ጠቅሰው ካስተማሩ በኋላ ከምእመናኑ ጋር ጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር አሳርገዋል፣ ከጸሎቱ በኋላ ዕለቱ ዓለም አቀፍ የዲያበቲክስ የስኳር በሽታ ዕለት በመሆኑ ይህንን አመልክተውም ጥሪ አቅርበዋል፣
ቅዱስነታቸው ያቀረቡት ትምህርት እንደሚከተለው ነበር፣ ውድ ወንድሞችና እኅቶች፤ የዛሬ እሁድ ቃለ እግዚአብሔር በሥርዓተ አምልኮእችን ዘመን ሁለተኛ የመጨርሻ እሁድ መሆኑ ነው፤ በዚች ዓለም ኑሮአችን ግዝያዊ መሆኑን በማመልከት እንደ ነጋድያን መኖር እንዳለብን ሲያስታውሰን እግዚአብሔር የእርሱ እንድንሆን ስለፈጠረን ትኵረታችን እንድንኖርበት በፈጠረው በወዲያኛው ዓለም ማድረግ እንዳለብን ያሳስበናል፣ የመኖራችን ትርጉምና የመጨረሻ ውሳኔአችን ይህ ነው፣ እዚህ ላይ ለመድረስ ግን አይቀሬ በሆነው ሞት መሻገር አለብን፣ ይህንንም የመጨረሻው ፍርድ ይከተለዋል፣ ቅዱስ ጳውሎስ “የጌታ ቀን እንደሌባ በሌሊት ይደርሳል” (1ኛተሰ 5፤2) ማለትም አለምንም ማስጠንቀቅያ ይደርሳል ይለናል፣ ጌታ ኢየሱስ በክብር መመለሱን መገንዘብ የመጀመርያ መምጣቱን ዝክር በማዘውተር ተጠንቅቀን እንድንጠባበቅ ያደርገናል፣
ቅዱስ ማቴዎስ 25፤14-30 በሚተርከው የመክሊት ምሳሌ “ወደ ሌላ አገር የሚሄድ ሰው ባሮቹን ጠርቶ ያለውን ገንዘብ እንደ ሰጣቸው እንዲሁ ይሆናልና፤ለእያንዳንዱ እንደ ዓቅሙ፥ ለአንዱ አምስት መክሊት ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ሄደ። አምስት መክሊትም የተቀበለው ሄዶ ነገደበት ሌላም አምስት አተረፈ፤ እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ። አንድ የተቀበለው ግን ሄዶ ምድርን ቈፈረና የጌታውን ገንዘብ ቀበረ። ከብዙ ዘመንም በኋላ የእነዚያ ባሮች ጌታ መጣና ተቆጣጠራቸው። አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ሌላ አምስት መክሊት አስረክቦ። ጌታ ሆይ፥ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁበት አለ። ጌታውም። መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው። ሁለት መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፍሁበት አለ። ጌታውም። መልካም፥ አንተ በጎ፥ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፥ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው። አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥ ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንህባትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ ፈራሁም ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ፥ መክሊትህ አለህ አለ። ጌታውም መልሶ እንዲህ አለው። አንተ ክፉና ሃኬተኛ ባሪያ፥ ካልዘራሁባት እንዳጭድ ካልበተንሁባትም እንድሰበስብ ታውቃለህን? ስለዚህ ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ልትሰጠው በተገባህ ነበር፥ እኔም መጥቼ ያለኝን ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር። ስለዚህ መክሊቱን ውሰዱበት አሥር መክሊትም ላለው ስጡት፤ ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።” ብሎ ይተርካል፣ ጌታው በሁለቱ ደስ ሲለው ያ ሶስተኛው አገልጋይ ግን ጌታው እንደማይመለስና ሂሳብ እንደማይጠይቀው ሆኖ ስለኖረ እጅግ ያሳዝነዋል፣
ጌታ ኢየሱስ በዚህ ምሳሌ ለሐዋርያቱ ሊያስተምራቸው የፈለገው ጉዳይ ስጦታዎችን በደንብ መጠቀም እንዳለባቸው ነው፣ እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን ለሕይወት ይጠራናል በዘመናችን ኑሮ እውን ማድረግ ያለብን መደብ በመስጠት ደግሞ እንደየችሎታችን ስጦታ ያድለናል፣ እነዚህ ከእግዚአብሔር የምንቀበላቸው ስጦታዎች እንደመብታችን ማሰብ ቂልነት ነው፣ ከዚሁ የባሰ ደግሞ በሚገባ መጠቀማቸውን እምቢ ያልን እንደሆነ ደግሞ የህልውናችን ዓላማ አለምዋምዋላት ነው፣ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዐቢይ ለዚሁ የወንጌል ጥቅስ አንድምታ ሲሰጥ “በምታደርጉት ነገር ሁሉ ግብረ ሠናይን ማስቀድም እንዳለባችሁ አትዘንጉ” በማለት ጌታ በግብረሠናይኑ በፍቅሩ ይህ ነገር እንዳጐድል አደራ እንደሚል ያሳስባል፣ ቅዱሱ ይህንን ነገር ማለትም ለጓደኞችም ይሁን ለጠላቶች የፍቅር ሥራ ማጓደል እንዳለብን ካሳሳበ በኋላ “አንድም ሰው ከዚህ ምግባረ ሠናይ የ… ቢሮር ያለውን በጎ ነገር ሁሉ ያጠፋል፤ የተሰጠውን መክሊት ይነጠቃል፤ ወደ ጨለማም ይጣላል” ይላል፣
የተከበራችሁ ሆይ፤ ቅዱሳት ጽሑፎች የሚያቀርቡልንን የመጠባበቅ ጥሪ እንቀበል፣ ይህ ትሪ ጌታ እንደሚመለስና በእኛ ላይ በምግባረ ሠናይ ያፈረናችውን ፍሬዎች ለመቆጣጠር ይመጣል፣ የፍቅር ተግባር ማንኛውም ሊጎድልበት የማይሆን ተግባርና ወደር የለሽ መሆኑን በ1ኛ ቆሮንጦስ እንዳለው “ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም።” በማለት ጌታ ኢየሱስ ዮሐንስ በወንጌሉ “16 በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።” (ዮሐ 3፤15) እንዳለውና በመልእክቱ “ወዳጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል።” (1ኛዮሐ 4፤11) እንዳለው እኛም የጌታን የፍቅር ተግባር በተግባር እያሳይን በጌታ ደሥታ ለመሳተፍ እንደምንችል ያስተምረናል፣ እመቤታችን ድንግል ማርያም እግዚአብሔርን ለመጠባበቅ ተግባራዊና ደስታ በሞላበት ሁኔታ እንዲሆን አስተማርያችን ትሁን፣
ዛሬ ብዙ ሰዎችን ወጣቶችን ሳይቀር በማጥቃት ላይ የሚገኘው የዲያበቲክስ የስኳር ሕመም ዓለም አቀፍ ቀን ይዘከራል፣ በዚሁ በሽታ ስለተጠቁና በየዕለቱ ችግሩን ስለሚጋፈጡና በዚሁ ሕመም ለተቸገሩ ለመርዳት ስለሚጥሩ የጤና ባልደረባዎችና ባለ በጎ ፈቃድ ረዳቶች ስለሁሉም እጸልያለሁ፣
በዛሬው ዕለት ደግሞ የጣልያን ቤተ ክርስትያን የምስጋና ዕለት ታከብራለች፣ የመሬት ፍሬን የተመለከትን እንደሆነ ጌታ ዘንድሮም የወዛችን ፍሬ ሰጥቶናል። በዚህም ጌታ ፍርያም ባያደርገው ኖሮ የሰው ልጅ ሥራ ባዶ በሆነ ነበር። ምክንያቱም “እርሻችን ፍሬ የሚያፈራው ከእግዚአብሔር ጋር ብቻ ስንሠራው ነውና”፣ ለእግዚአብሔር ምስጋና ስናቀርብ ጌታ ልንጠብቃት የሰጠንን መሬት ለመጠበቅ ኃላፊነታችን እንልበስ”፣








All the contents on this site are copyrighted ©.