2011-11-08 10:02:54

የሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቨልዮ መግለጫ ፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ፊታችን ዓመት 2012 ጥር 15 ቀን እኤአ ተከብሮ ለሚውለው 98ኛ ዓለም አቀፍ የስደተኞች ቀን ስደተኞች እና አዲስ ስብከተ ቅዱስ ወንጌል መሰየማቸው የሚታወስ ነው።

በቅድስት መንበር የስደተኞች ሐዋርያዊ ኖልዎ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ብፁዕ አቡነ አንቶንዮ ማሪያ ቨልዮ እንዳመለከቱት ፡ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት በተለያዩ ምክንያቶች ሀገራቸው ትተው ወደ ምዕራቡ ዓለም ሲፈልሱ ይታያሉ።

ፍልሰተ ህዝቡ ለስብከተ ቅዱስ ወንጌል መልካም አጋጣሚ መሆኑ እና ከኢየሱስ ክርስቶስን ትውውቅ የሌላቸው ስደተኞቹን ለማስተዋወቅ እና ስደተኞቹን መርዳት ቀዳምነት የሚሰጠው ተግባር መሆኑ ሊቀ ጳጳሱ አመልክተዋል።

እምነተ ክርስትና የሚከተሉ ስደተኞች በእምነታቸው ለመጽናት ማበረታት ባህላቸው አቅበው በሰላም ለመኖር ይችሉ ዘንዳ ማገዝ አስፈላጊ መሆኑ የስደተኞች ሐዋርያዊ ኖልዎ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብጹዕ አቡነ አንቶንዮ ማሪያ ቨልዮ ገልጠዋል።

ስደተኞቹ ከሚመጡባቸው ሀገራት እና በስደት በሚኖሩበት ሀገር መካከል ትብብር እንዲኖር እተጣረ መሁኑ እና ጥረት አዎንታዊ ፍንጭ ማሳየቱ ሊቀ ጳጳሱ በተጨማሪ አመልክተዋል።

በቅድስት መንበር የስደተኞች ሐዋርያዊ ኖልዎ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ስደተኞች በሚመለከት ዋነኛ ዓላማ የስደተኞቹ መሠረታዊ መብት እንዲጠበቅ ከነሱ ጋር መተባበር መሆኑ ብጹዕ አቡነ አንቶንዮ ማሪያ ቨልዮ ማስገንዘባቸው ተዘግበዋል።

ስደተኞቱ የሚኖሩበት ሀገር ባህል እና ሕግ እንድያስከብሩ ማስረዳት እና ማሳወቅም የምክር ቤቱ እና የባለ በጎ ፈቃድ ሰዎች ግዴታ መሆኑም አስገንዝበዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ መገናኛ ብዙኀን የስደት ጠንቅ እና የስደተኞች ሁኔታ ለአንባቢ እንድያስረዱ ባሳለፉት መልእክት ማሳሰባቸው የሚታወስ ነው ።

ይህ የመሰደድ ጠንቅ ያልተገነዘቡ ሰዎች በስደተኞች ላይ ያላቸውን አሉታዊ አስተያየት ለማስወገድ እንዲኖራቸው መሆኑ ቅድስነታቸው ቀደም ሲል ለዕለቱ ስተላለፉት መልእክት ላይ ማሳታቸው የማይዘነጋ ነው።

በተለያዩ ምክንያቶች ሀገራቸው ለቀው እንዲሰደዱ የሚገደዱ ሰደተኞች ጉዳይ ትኩረት የሚያስፈልገው መሆኑ እና የስደተኞቹ መብት እና ሰብአዊ ክብር እንዲጠበቅ ሁነኛ ርምጃ መወሰድ እንደሚያስፈልግ ብፁዕ አቡነ አንቶንዮ ማሪያ ቨልዮ አመልክተዋል።

ስደተኞቹ በሚገኙባቸው ሀገራት ከሕብረተ ሰቦች የመዋሀድ ከፍተኛ ችግር እንደሚገጥማቸው እና ስደተኞቹ በስደት የሚገኙባቸው ሀገራት ባህል ቋንቋ እና ታሪክ እንዲረዱ መርዳት እዥግ አስፈላጊ መሆኑም በተጨማሪ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.