2011-11-07 14:08:47

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ካህናት የግል ሳይሆን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ይፈልጉ


ጳጳሳዊ መናብርተ ጥበብ የትምህርት ዓመት መባቻ ምክንያት እ.ኢ.አ. ህዳር 4 ቀን 2011 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የተሳተፉበት እና ሥልጣናዊ አስተምህሮ RealAudioMP3 የሰጡበት ጸሎተ ሰርክ መፈጸሙ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።
ቅዱስ አባታችን በዚህ ጸሎት ሠርክ ለተሳተፉት የጳጳሳዊ መናብርተ ጥበብ ተማሪ ካህናት እና ዓለማውያን ምእመናን የእግዚአብሔር ጥሪ ርእሰ ግላዊ እቅድ ሳይሆን ምንም’ኳ እራስን ፈጽሞ ለማረጋገጥ ከሚመራን የግል ፍላጎት ጋር የማይዛመድ ቢሆንም የእግዚአብሔር ፈቃድ እሺ ተብሎ በሕይወት የሚስተነገድ ጸጋ ነው በማለት እ.ኤ.አ. ህዳር 4 ቀን 2011 ዓ.ም. የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ጠባቂ የቅዱስ ካሮሎ ቦሮመዮ ዓመታዊ በዓል የምትዘክርበት ቀን በማስታወስም፣ በጸሎት የሚጸና ክርስቶስ ጋር ካለው ጥብቅ ትሥሥር እና ግኑኝነት ከወንጌል የተቀበልነው መልእክት ለማካፍል ካለው አቢይ ቅናት እና ፍቅር ሐዋርያዊ ጥሪ ኅያው ነው በማለት፣ ከክርስቶስ ጋር የሚስማማ ሕይወት በካህን ሕይወት እንዲጎላ ከተፈለገ በቅድሚያ የእግዚአብሔር መንግሥት በማስፋፋት እቅድ ከክርስቶስ ጋር መተባበር፣ በሚሰዋ ፍቅር የታጀበ ሐዋርያዊ አገልግሎት፣ የተገልጋይነት ሳይሆን የአገልጋይነት ጠባይ የሚሻ መሆኑ ማብራራታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ሲያመለክት፣ የምሥጢረ ክህነት ጥሪ፣ ከእየሱስ ጋር መገናኘትን የእርሱ ቃላት በእርሱ አንደበት እና ሰብአዊነት በአድናቆት መማረክን ይጠይቃል። ከሁሉም ከተለያዩ ድምጾች ለይቶ የእርሱን ድምጽ በማወቅ ልክ እንደ የኤማውስ ደቀ መዛሙርት ከእርሱ ጋር በመቅረት ከዚህ ከእርሱ ጋር መቅረት በሚሰጠው ኃይል አማካኝነትም ለዓለም ሁሉ ወንጌል ለማበሠር የሚጠራ እና የሚልክ በእርሱ መልካምነት ደምቆ እና በርቶ ከእርሱ ፍቅር የሚመነጭ ጥሪ ነው።
ለክርስቶስ ፍቅር እሺ ብሎ የሚገዛ በእርሱ እንዲፈቀር ገዛ እራሱን የሚተው፣ ከእርሱ ጋር መሆንን መቅረትንም ጭምር የሚያውቅ፣ ከእርሱ ጋር ውሁድ ስምምነት ያለው ጥብቅ ጓደኝነት እግዚአብሔርን ደስ እንደሚያሰኝ ሁሉ ይፍጸም ዘንድ በአቢይ ውስጣዊ ነጻነት እና ጥልቅ ልባዊ ደስታ ተክኖ መኖር ማለት መሆኑ ቅዱስ አባታችን በማብራራት፣ ጥሪ ለሚያሳፍር ፍላጎት ወይንም በርእሰ ብቃት አማካኝነት የራስ ግላዊ እቅድ ማስፍፈጸሚያ ሳይሆን፣ ምንም’ኳ እራስን ፈጽሞ ለማረጋገጥ ከሚመራን የግል ፍላጎት ጋር የማይዛመድ ቢሆንም፣ የእግዚአብሔር ፈቃድ እሺ ተብሎ በሕይወት የሚስተነገድ እና የሚኖር ጸጋ ነው። ስለዚህ ማንኛውም ካህን ሊዘነጋው የማይገባውም ብቸኛው የተገባ ርእሰ እቅድ ማሳካት ሳይሆን ከመስቀል ወደ ሚገኘው ድል ወደ የሚያደሚያደርሰው የእረኛነት ምሥጢር የሚመራ መሆኑ በጥልቀት ማስገንዘባቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።
ካህናት የድህነት መሣሪያ የሆኑት ቅዱሳት ምሥጢራትን በገዛ ፈቃድ ሳይሆን ለሕዝበ እግዚአብሔር ጥቅም በትሁት የአገልጋይነት መንፈስ የሚሠሩ፣ የእግዚአብሔርን በጎች በጥንቃቄ የሚንከባከቡ በታማኝነት እና በእማኔ ተገቢው እና ትክክለኝው ሊጡርጊያ የሚያከብሩ ስለ ወንድሞች የሚሉ ናቸው በማለት ቅዱስ አባታችን እ.ኤ.አ. ሕዳር 4 ቀን 1941 ዓ.ም. የክህነት ጥሪ ለማነቃቃት የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ለማበረታታት የተገባ ሰብአዊ እና መንፈሳዊ ሕንጸት ለማነቃቅት አልመው ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 12ኛ እንዲቋቋም ያደረጉት የክህነት ጥሪ ተግባር ተንከባካቢ ማኅበር የተመሠረተበት 70ኛው ዓመት በሚዝከርበት በአሁኑ ወቅት ይህ የዘርአ ክህነት ተማሪዎች እና የመንፈሳዊ ማኅበሮች ተንከባካቢ በሚል መጠሪያ ተተክቶ ከዛም እ.ኤ.አ. በ 1988 ዓ.ም. በመልካም እረኛ ውሳኔ መሠረት የካቶሊክ ትምህርት ተንከባካቢ በሚል ስያሜ የጸናው ቅዱስ ማኅበር እኔ መረጥኩዋችሁ በሚል ርእስ ሥር ተመርቶ በተካሄደው ዓወደ ጥናት የተሳተፉት ካህናት እና የዘርአ ክህነት ተማሪዎች የጳጳሳዊ መናብርተ ጥበብ በሮማ የሚገኙት የተለያዩ ጳጳሳዊ ተቋሞች ተማሪዎችን ሰላምታ በማቅረብ፣ የክህነት ጥሪ እያንዳንዱ የእራስ ፍላጎት ለጌታ ፍላጎት በማስገዛት በለጋስነት የሚኖር የግል እቅድ ሳይሆን የእግዚአብሔር እቅድ የሚኖር ሕይወት መሆኑ፣ ስለዚህ ሕዝበ እግዚአብሔርን ለመምራት በሚሰጠን የተልእኮ ኃላፊነት ተገቢ እና ብቃት ያለው አገልግሎት ለመሰጠትም የሥነ እውቀት ሕንጸት እጅግ አስፈላጊ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.