2011-10-31 13:48:46

በአረብ አገሮች ፀደይ የማኅበረ ክርስትያን አስተዋጽዖ


በአሁኑ ወቅት በቱኒዝያን አንድ በማለት የተቀጣጠለው የለውጥ እና ኅዳሴ ጠሪ ሕዝባዊ አብዮት በብዙ አረብ አገሮች በመታየት ላይ ሲሆን፣ ብዙውን ጊዜ ስለ ሕዝባዊው ዓብዮት እንጂ RealAudioMP3 የዚህ ሕዝባዊ አብዮት ተወናያን ክፍለ ኅብረተሰብ ብዙ እንደማይባል በቅድስት መንበር የኢራቅ ልኡከ መንግሥት ሃቢብ ሞሃመድ ሃዲ አሊ አል ሳድር ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በማብራራት፣ በዚህ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ የአረብ አገሮች ክርስትያን ማኅበረሰብ ዜጋ ሚና የሚደነቅ ነው። የአረብ አገሮች ማኅበረ ክርስትያን የአገራቸው ክፍለ ኅበረተሰብ ናቸው እንጂ የውጭ አገር ዜጎች አይደሉም ካሉ በኋላ፣ ሁሉም አለ ምንም የሃይማኖት ልዩነት ኅዳሴ እና ለውጥ ፈላጊ ሆኖ የታየበት ሕዝባዊ አብዮት ነው። የሚረጋገጠው ለውጥ ሕዝብ እምቢ ያለው አምባገነናዊው ሥርዓት፣ በተለያየ መልኩ በአክራሪነት እና በፅንፈኞች የፖለቲካ ሰልፎች አማካኝነት ሕይወት እንዳይዘራ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። እንቅስቃሴው የመሩት የተለያዩ የአረብ አገሮች ክፍለ ኅብረተሰብ መሪዎች የሕዝባዊ እንቅስቃሴ መሪዎች የተሳታፊው ሕዝብ መለያ እና ራእይ የተለያየ የተከፋፈለ ይመስላል፣ እንዲህ ባለ ሁኔታም ክርስትያን ማኅበረሰብ የሚቃወሙ እና ለማጥፋትም የሚሹ አክራርያን ሃይሎች የሕዝቡ ሃይማኖታዊ ስሜት መሣሪያ በማድረግ የራሳቸውን ዓለማ እውን ለማድረግ እንዲነቃቁ አጋጣሚ ሊፈጥር ይችላል።
በአረብ አገሮች የተሰቃየው እና ለስደት የተዳረገው ማኅበረ ክርስትያን ብቻ አይደለም፣ የተለያዩ ውሁዳን ሃይማኖቶች እና ጎሳዎች ጭምር የነካ ጉዳይ ነው። የተቀጣጠለው ሕዝባዊ አብዮት ለአገር ውስጥ ውጥረት አጋጣሚ ሆኖ ለአናሳው የኅብረተሰብ ክፍል አደጋ ሊሆን ይችላል። ስደት ከማለት ግን አብሮ በአገር ውስጥ ለውጥ ከሚሹ ጋር በመሆን በእምነት ጸንቶ የሚረጋገጠው ለውጥ ለሁሉም ብርህ ተስፋ አዘል ሆኖ እንዲገኝ በሚደረገው ጥረት ማኅበረ ክርስትያን ማእከላዊ ሚና አለው ብለዋል።
የክርስትናው እምነት የመቀበል እና የአሳቢነት ቸር ባህል ያለው በመሆኑም የአረብ አገሮች ማኅበረ ክርስትያን በዚህ መልኩ ለኅዳሴ በሚደረገው ጥረት የሰላም መሣሪያ ብቻ ሳይሆን ሰላም ለማረጋገጥ በሚደረገው ጉዞ ሁሉም መንግሥታትንም ጭምር ያነቃቃሉ። ሕዝባዊው ለውጥ በጦር መሣሪያ ሳይሆን በሰላማዊ መንገድ እንዲረጋገጥ አብነት ሆነው ለውጡ ለአክራርያን እና ፅንፈኞች አመች እንዳይሆን የሰላም ባህል ለማስፋፋት በሚደረገው ጥረት ተቀዳሚ ሥፍራ የያዙ ናቸው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.