2011-10-26 14:40:19

ብፁዕ ካርዲናል ኮች፦ “የክርስትያኖች ውህደት ማረጋገጥ የቅዱስ አባታችን ር..ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ቀዳሚው ሐዋርያዊ ዓላማ ነው”።


የክርስትያኖች አንድነት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ኩርት ኮች በአሲዚ የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራ ግኑኝነት መርሃ ግብር ከሚከናወንበት ቀነ ቀጠሮ RealAudioMP3 አንድ ቀን ቀደም በማድረግ ላ ኮሮይክስ ለተሰኘው የፈረንሳይ ዕለታዊ ጋዜጣ ላቀረባቸው ቃለ መጠይቅ ሲመልሱ፣ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ቀዳሚው ሐዋርያዊ ዓላማ የክርስትያኖች አንድነት ማረጋገጥ የሚል መሆኑ ገና የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታዮ ሆነው በእነተ ላእለ ኩሉ ቤተ ክርስትያን ከተሾሙበት ዕለት ጀምረው ያነጣጠሩበት ዓላማ መሆኑ ማብራራታቸው ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
ስለዚህ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶ ውህደት ቀዳሚነት የሚሰጥ መሆኑ የአንግሊካን የኦርቶዶክስ የሉተራን አቢያተ ክርስትያን መንፈሳውያን መሪዎች ቀርበው ሊገናኝዋቸው የሚሹ ከሳቸው ጋር መወያየት እና መነጋገርን የሚወዱ መሆናቸው የሚገልጡት ሃሳብ እና የሚያካሂዱት ግኑንነቶች ያረጋግጥልናል ሲሉ ብፁዕ ካርዲናል ኮች ለፈረንሳዩ ዕለታዊ ጋዜጣ የሰጡት ማብራሪያ ሲር የዜና አግልግሎት ጠቅሶ፣ በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ እና የመላ ሩሲያ እና የሞስካ ፓትሪያርክ ያለው ግኑኘነት ከዚህ ቀደም ያልታየ የተዋጣለት መሆኑ ብፁዕነታቸው እንዳስታወሱም የዜናው አገልግሎት አክሎ አስምሮበታል። ስለዚህ የአሲዚው ግኑኝነት ሃይማኖት ሰላም እንጂ አመጽ ማለት እንዳልሆነ ሁሉም የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች መንፈሳውያን መሪዎች እና ኢአማንያን ምሁራን ጭምር በጋራ በመገናኘት የሚያበክሩት ሃሳብ እንደሚሆን በመግለጥ የሰጡት ቃለ ምልልስ እንዳጠቃለሉ ሲር የዜና አገልግሎት አመለከተ።








All the contents on this site are copyrighted ©.