2011-10-19 14:49:41

የአሕዛብ ቅጥር ግቢ ፥ የአማኒያን እና ኢአማንያን የጋራ ውይይት


የባህል ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት በአማኒያን እና ኢአማንያን መካከል በፈረንሳይ ርእሰ ከተማ ፓሪስ ያስጀመረው የጋራው ውይይት መርሃ ግብር በመቀጠል በተለያዩ የኤውሮጳ ክልል አገሮች የተለያዩ የውይይት አውደ ጥናቶች ካከናወነ በኋላ ከትላንትና በስትያ በኢጣሊያ በታሪካዊት የፊረንዘ የሥነ ውበት ከተማ RealAudioMP3 “ሰብአዊነት እና ውበት፥ ትላትና እና ዛሬ” በሚል ርእስ ሥር እምነት እና ሥነ ጥበብ ማእከል ያደረገ አማኒያን እና ኢአማንያን ሊቃውንት የተሳተፉበት የባህል ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፅዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ ሠፊ እና ጥልቅ አስተምህሮ በማቅረብ ያስጀመሩት ዓወደ ጥናት መካሄዱ ዓወደ ጥናት የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ፋቢዮ ኮላግራንደ ካስተላለፉት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
ብፁዕ ካርዲናል ራቫዚ ባቀረቡት አስተምህሮ አለ ሥነ ጥበብ እግዚአብሔር ረቂቅ፣ ተጨባጭ ያልሆነ፣ እምነትም ጭምር ለሰው ልጅ ልብ የመናገር ብቃት የሌለው ሆኖ በቀረ ነበር። ሆኖም ውበት እንደ የሥነ ህልውና እውነታና እውቀት ምርምር፣ ማለትም የመልካም ነገራዊ መሆን ባሻገር መግለጫ ሁኔታ ነው። እንዲህ ሲባልም ከምናየው ተጨባጭ ነገር ሁሉ ማዶ ያለው ውበት የሚገልጽ ሁኔታ ነው። ስለዚህ ይህ ያለው የውበት የላቀው ትርጉም ኢአማንያን እና አማንያን የሚያገናኝ አዲስ ሰብአዊነት ለመገንባት ለሚበጅ ሥነ ምግባር ምንጣቄ የሚያሰጥ ኩላዊ መድረክ እና ኩላዊ ቋንቋ ሊሆን ይችላል መሆንም አለበት እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ፋቢዮ ኮላግራንደ ያስተላለፉት ዘገባ ያመለክታል።
በአውደ ጥናቱ ተገኝተው ንግግር ያሰሙት የፊረዘን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ በቶሪ ይላሉ፣ ይህ የአሕዛብ ቅጥር ግቢ መርሃ ግብር እርሱም አማኒያን እና ኢአማኒያንን የሚያወያየው መርሃ ግብር ቤተ ክርስትያን ላይ ብዙውን ጊዜ የሚዘነዘረው እርሱም የነገር መለኮት ቀኖናዊ ግትርነት አመለካከት የምትከትል ነች የሚለው ወቀሳ ከእውነት የራቀ መሆኑ የሚመሰክር ተጨባጭ አብነት ነው እንዳሉም የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ፋቢዮ ኮላግራንደ ዘገባ ይጠቁማል።
በዚያ የፊረንዘ አውደ ጥናት የተሳተፉት የሥነ ትያትር ሊቅ ሞኒ ኦቫዲኣ እና ከሕይወት በኋላ ሌላ ሕይወትና የአምላክ መኖር ለማወቅ አይቻልም የሚለው ፍልስፍና ሊቅ ሰርጆ ጂቮነ እንዲሁም ደራሲ ኤሪ ደ ሉካ የሥነ ጥበብ ታሪክ ሊቅ አንቶኒዮ ፓውሉቺ በየፊናቸው ጥናታዊ ንግግር ማሰማታቸው ሲገለጥ፣ በመጽሓፈ ሲራክ የሚተረከው ውበት፣ ውበት በውስጡ ያለው እምቅ ኃይል የሚያረጋግጥ መሆኑ ብፁዕ ካርዲናል ራቫዚ በማብራራት፣ የሮማኒያ ዜጋ የሥነ ግጥም ሊቅ ገጣሚ ኤሚል ቺዮራን የባኽ የሙዚቃ ሥራዎችን ብቻ በማዳመጥ በእውነት ህልወተ እግዚአብሔር ለማረጋገጥ እየተቻል የእግዚአብሔር ህላዌ ለመንገር የሚደረገው የሥነ ምርምር ሂደት ጊዜ ማባከን መስሎ ይታየኛል ሲሉ፣ የአይሁድ መሠረተ እምነት ያላቸው የሥነ ትያትር ሊቅ ኦቫዲያ በበኩላቸውም ሥነ ጥበብ ህልወተ እግዚአብሔር የሚያረጋግጥ የተሟላ እውቀት ነው ብለዋል።
ቤተ ክርስትያን ሥነ ጥበብ እና በሥነ ጥበብ የሚገለጠው ውበት የእግዚአብሔር ጥላ መሆኑ ከጥንት ጀምራ የምታስተምረው እውነት መሆኑ በተካሄደው ዓውደ ጥናት እንደተሰመረበት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ፋቢዮ ኮላግራንደ ካስተላለፉት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.