2011-10-19 14:48:16

ብፁዕ አቡነ ፎርተ፥ እራሱን ከታሪክ የሚያገል እውነተኛ ክርስትያን ሊሆን አይችልም


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባላቸው የቅዱስ ጴጥሮሳዊ ሥልጣን አነሳሽነት መሠረት ግብረ ሐዋርያት ምዕራፍ 14 ቁጥር 27 “ፖርታ ፊደይ-የእምነት በር” በሚል ርእስ ሥር እ.ኤ.አ. ጥቅምት 11 ቀን 2011 ዓ.ም. ይፋ ያደረጉት እ.ኤ.አ. ጥቅምት 11 ቀን 2012 ዓ.ም. የእምነት ዓመት አመልካች ሰነድ ዘንድ RealAudioMP3 እንደተመለከተው፣ የእምነት በር ለሁሉም ለእነዚያ እምነት ጸጋ መሆኑም ጭምር ለማያምኑ ለማያውቁም ነገር ግን ከነገራዊ ተጨባጭ ወዲያ ምን አለ ለሚለው ጥያቄ መልስ ለሚሹ የፍጻሜ ትርጉም ፍለጋ ለሚጠመዱትም ሳይቀር ዘወትር ክፍት ነው።
የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ልዩ በራስ አነሳሽነት የመወሰን ሥልጣን መሠረት “ፖርታ ፊደይ-የእምነት በር” በተሰኘ ርእስ ሥር የደረሱት ሐዋርያዊ መልእክት በማስደገፍ በኢጣሊያ የኪየቲ ቫስቶ ሊቀ ጳጳስ የቲዮሎጊያ ሊቅ ብፁዕ አቡነ ብሩኖ ፎርተ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የእምነት ዓመት እ.ኤ.አ. ጥቅምት 11 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ እ.ኤ.አ. ህዳር 24 ቀን 2013 ዓ.ም. የሚጠናቀቅ ሲሆን እጅግ ሰፊ እና አቢይ ትርጉም ካለው ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ፍጻሜ 50ኛው ዝክረ ዓመት እንዲሁም የኩላዊት ቤተ ክርስትያን የትምህርተ ክርስቶስ ሰነድ 20ኛው ዝክረ ዓመት ጋር የተያያዘ በተለይ ደግሞ የእምነት ዓመት የመክፍፈቻ ቀን እ.ኤ.አ. ጥቅምት 11 ቀን 2012 ዓ.ም. አዲስ አስፍሆተ ወንጌል እምነትን ለማስፋፋት በሚል ርእሰ ጉዳይ የሚወያየው የመላ እንተ ላእለ ኩሉ ቤተ ክርስያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ጅማሬ ጋር የተቆራኘ በመሆኑ፣ ከዚህ አኳያ ያለው አቢይ ትርጉም ለመረዳቱ አያዳግትም፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ መልካም ፍሬ ከእምነት ጋር የተሳሰረ መሆኑ እና ጠቅላል ባለ አነጋገርም ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ የተደረሰ የእምነት ፀደይ ነው። ይኽ ደግሞ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል እና የእምነት ዓመት ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ያነቃቃው ህዳሴ መሠረት ያደረገ ቅዱስ አባታችን ይኸንን ቋሚ እና ጽኑ ኅዳሴ ለማመልከት እርሱም እምነት አቢይ ጸጋ መሆኑ ለማሳሰብ አልመው የሰጡት ውሳኔ መሆኑ የሚያረጋገጥ ሁኔታ ነው።
ቅዱስ አባታችን አማኞች እና እንዲሁም እውነትን ለማወቅ በፍለጋ የሚገኙት የእምነት ጥልቅነቱን እንዲገነዘቡ እና በዚሁ ጥልቅ ጉዞ የቤተ ክርስትያን የትምህርተ ክርስቶስ ሰነድ ዋቢ እንዲያደርጉ እና በጥልቀት ቀርበው እንዲረዱት አልመው የሰጡት ውሳኔ ነው። የእምነት ይዞታ እና ፍሬ ነገር በነጻነት በሚደረግ ጉዞ መፈለግ እንዳለበት የሚያመለክት፣ ስለዚህ የሰው ልጅ ነጻነት የሚያከብር ገዛ እራሱ በእምነት ጉዞ ተወናያን በማድረግ እምነትን እንዲፈልግ የሚያነቃቃ መንፈስ ያካተተ ውሳኔ ነው ብለዋል።
ስለዚህ እምነት የግል ጉዳይ እንደሆነ አድርጎ በግለኝነት ከታሪክ ተነጠሎ እና ነጥሎ መኖር እንደሌለበት የሚያሳስብ ውሳኔ ሲሆን፣ ይህ ደግሞ የክርስትናው እምነት ከታሪክ የሚያድን ሳይሆን ታሪክን የሚያድን፥ እምነት ቃል ሥጋ ሆነ በመካከላችን ላደረው የጌታችን ኢየሱስ ክስቶስ ትስብእት እማኔ ማለት ነው። ባለንበት የአሁኑ ወቅት በተጨባጭ መኖር በእግዚአብሔር ቃል የተገባው በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሙላት ግልጸት የተደመደመው ለእኛ መጻኢ በሆነው ዓለም ታምኖ መኖርን ይጠይቃል። ስለዚህ እነዚህ ሁለት ዓይነት እማኔዎች ክርስትያናዊ ምስክርነትን የሚገልጡ ናቸው። ከታሪክ የተነጠለ ምስክርነት የለም፣ ምስክርነት፥ እምነትን በታሪክ እምብርት በማቅረብ ሕይወትን እና ልብን የነካው እና የለወጠው በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተገለጸው የእግዚብሔር ምጽአት ገጠመኝ መኖር ማለት ነው ካሉ በኋላ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ውሳኔ ይኸንን ግምት የሰጠ ጥልቅ እና ሰፊ ዓላማ ያለው ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.