2011-10-14 14:01:50

ፍቅር በሐቅ ዓዋዲ መልእክት፥ ሥነ ምግባር እና በቃኝን የሚያውቅ ቍጡብ ሕይወት


ከትላትና በስትያ “የዓለም አቀፍ ኤኮኖሚ፥ ቅድመ እና ድኅር ካሪታስ ኢን ቨሪታተ-ፍቅር በሓቅ፣ መጻኢ እቅድ እና ተስፋ በሚል ርእስ ሥር RealAudioMP3 የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ዓዋዲት መልእክት መሠረት ዓወደ ጥናት መካሄዱ ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በዚያች አዋዲት መልእክት ያስቀመጡት መሠረታዊ ሐሳብ እና ያተኩርባቸው ነጥቦች በጥልቅ ያስቀመጡት እሴቶች ለሥነ ኤኮኖሚ ሂደት መሠረት መሆኑ የሰጡት ትንታኔ ባሰመረው ዓውደ ጥናት የተሳተፉት የቅድስት መንበር ለሃማኖታዊ ተግባር ተቋም ሊቀ መንበር የሥነ ኤኮኖሚ ሊቅ ፕሮፈሶር ኤቶረ ጎቲ ተደስኪ ከቫቲካን ረዲዮ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ሲያብራሩ፣ በቅድሚያ የሰው ልጅ የግል ኃላፊነት ትርጉም እና ለዚህ ግንዛቤ ደጋፊ በመሆን የሚያገለግሉ መሣሪያዎች በተገባ በመለየት የአጠቃቃም የኃላፊነት ስሜት ጭምር መጎናጸፍ ይኖርበታል የሚለው ሐሳብ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍቅር በሐቅ በተሰኘችው ዓዋዲት መልእክታችው የሰጡት ጥልቅ ማብራሪያ፣ በነዚህ ባለፉት ዘመናት በተደናገረው እና ሃይማኖታዊ ግብረ ገባዊ እምነቶች ብሎም መንግሥታዊ ሥርዓት ጨርሶ መኖር የለበትም በሚለው የኢምንትነት ፍልስፍና እጅግ የተጠቃው ዓለም፣ ሁሉ ነገር ከመሠረታዊው ትርጉም ሰጭ እና ከግብረ ገብ እና ሥነ ምግባር መመሪያ፣ ነጻ ከመሆናቸውም ባሻገር መገልገያ መሣሪያ መሆናቸው ቀርቶ ዋና ግብ ሆነው ዕደ ጥበብ ያመጣው የተራቀቀው መሣሪያ ጭምር ለመቆጣጠር እና በሚገባ ሊጠቀምባቸው የሚያበቃው በኤኮኖሚ ብቻ ሳይሆን፣ የተለያዩ የሥነ ምርምር ዘርፍ በሳል የኅሊና የማመዛነ ብቃቱን በማጣት ምክንያት ለአደጋ ተጋልጦ ይገኛል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የሁሉም ቀውሶች አናሥር የሰው ልጅ የገዛ እራሱ ቅዉም ነገር ሰብአዊ ክብሩንም ጭምር ማጣቱ ያስከተለው ሃይማኖታዊ ግብረ ገባዊ እምነቶች ብሎም መንግሥታዊ ሥርዓት ጨርሶ መኖር የለበትም በሚለው የኢምንትነት ፍልስፍና መሥፋፋት እርሱም ሰውን የማስተዋል ሳይሆን የማሰብ ብቃት ብቻ ያለው እንስሳ ነው በሚለው መግለጫ በመለየት፣ ስለዚህ የሚያስብ እንስሳ ከሆነ ከዚህ ይፋዊ መነሻ በቁስዊ ነገር ብቻ መርካት አለበት ወደ ሚለው መደምደሚያ ጠቅላይ ሐሳብ ተደርሶ፣ ክብሩን በመቀናቀን እና ጸረ ሰብአዊነቱ በመኖር በዚህ መሠረት ሁሉንም ነገር በመግለጥ ይኸው ባለፉት 20 እና 30 ዓመታት ፍጆታው ላይ ብቻ ለማርካት ተራውጧል። በዚህ ትርጉም የለሽ የፍጆታ ባህል ተንደባሎ ሰው በሥጋ እና በነፍስ የቆመ መሆኑ ዘንግቶ ለመኖር የተከተለው የአኗኗር ሥልት ያስከተለው ችግር መሆኑ ያብራራሉ።
ስለዚህ በሁሉም ዘርፍ ሥነ ምግባር የተነጠቀው ዜግነት ዳግም ማጎናጸፍ ያስፈልጋል፣ በኤኮኖሚው እና በገበያው ሂደት ሥነ ምግባር ማካተት ሥነ ምግባር በፖለቲካው ዓለም ዳግም መሥረጽ ይኖርበታል። ይህ ደግሞ ግብረ ገባዊ መመሪያዎች መሠረት በማድረግ መኖር እንደሚያስፈግል የሚያመለክት ሲሆን፣ ሥነ ምግባር የግብረ ገብ መመዘኛዎች መሠረት መኖር ማለት ሲሆን፣ ግብረ ገብ ደግሞ የሰው ልጅ የተሰጠው ክፉን እና መልካሙን የመለየት ብቃት መሠረት የሚገለጥ ሚዛን ነው ካሉ በኋላ በዓለም ተከስቶ ካለው የኤኮኖሚ እና የቁጠባ ቀውስ ለመላቀቅ እድገት የሚያነቃቃ ብቃት ያለው መርሃ ግብር ማቅረብ ብቻ ሳይሆን፣ በቃኝ ማለቱ እና ካአባካኝነትም መላቀቅ፣ ሃይማኖታዊ ግብረ ገባዊ እምነቶች ብሎም መንግሥታዊ ሥርዓት ጨርሶ መኖር የለበትም በሚለው የኢምንትነት ፍልስፍና እና ካስከተለው የሥነ ፍጆታ አመለካከት ነጻ መሆን አስፈላጊ እንደሆነ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ፍቅር በሐቅ የተሰኘቸው ዓዋዲ መልእክት የሰጡትን ሥልጣናዊ ትንተና ተንተርሶ ያስገነዘበ ዓወደ ጥናት ነበር በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.