2011-09-14 14:59:10

ሰነጋል፣ ክርስትያኖች እና ሙስሊሞች


የሰላም እና እሴቶች መልሶ ማነጽ እንቅስቃሴ በሚል መጠሪያ በሴነጋል እ.ኤ.አ. ባለፈው መስከረም 8 ቀን 2011 ዓ.ም. በርእሰ ከተማ ዳካር በከተማይቱ ሊቀ ጳጳሳ ብፁዕ ካርዲናል ተዮዶረ አድሪየን ሳር እና ሼክ ኤል ሃድጂ ሙስታፋ ሲሴ RealAudioMP3 አነሳሽነት በአገሪቱ ሰላም ለማነቃቃት እና ለመገንባት በማቀድ መቋቋሙ ሲር የዜና አገልግሎት ያመለክታል።

አብርሃማዊ ኃይማኖቶች የሚያስተምሩት እና ከትልድ ወደ ትውልድ የሚያስተላልፉት ሰላም መተባበር መደጋገፍ የተሰኙት ምግባረ ጥሩነት ለማነቃቃት ብሎም በማኅበራዊ ሕይወት ጎልቶ ማኅበራዊ ሰላም ለማረጋገጥ የሚደግፍ የሚያንጽ እንቅስቃሴ ሲሆን፣ ሁለቱ ማለትም ብፁዕ ካዲንል ሳር እና ሼክ ሲሴ በሊቀ መንበርነት የሚመሩት ማኅበር መሆኑ ሲር የዜና አገልግሎት ያሰራጨው ዜና ይጠቁማል።

በዚህ አጋጣሚም በሴኔጋል እ.ኤ.አ. በ 2012 ዓ.ም. ሊካሄድ የታቀደው የርእሰ ብሔር እና የሕዝብ ተወካዮች እና የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት ምርጫ የተዋጣለት ብቻ ሳይሆን ትክክለኛ እና ሕጋዊ ሆኖ የሕዝብ ውሳኔ እና ምርጫ የሚያከብር በማድረጉ ረገድ አቢይ ድጋፍ የሚሰጥ እንደሚሆን ከወዲሁ ግምት ያለ ሲሆን፣ እንዲሁም በቅርቡ በአገሪቱ የተካሄዱት የመንግሥት ተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ያስከተለው ግጭት እና ጉዳት በመጥቀስ የሃይማኖት መሪዎች ሕዝቡ እንዲረጋጋ እና ለሰላም እንዲጸልይ ጥሪ በማቅረብ የፖለቲካ ሰልፎች በውይይት መድረክ ብቻ እማኔአቸው እንዲያኖሩ አሳስበው እንደነበርም ሲር የዜና አገልግሎት ያመለክታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.