2011-08-12 12:06:35

ቅድስት ክያራ ዘአሲዚ


ትናንትና በላቲኑ ሥርዓተ አምልኮ ግጻዌ የአሲዚዋ ቅድስት ኪያራ በዓለ ተከብረዋል፣ ቅድስትዋ በ1194 ዓም ከመለድዋ በፊት ገና በእናትዋ ማኅፀን እያለች እናትዋ በቅዱስ ሩፊኖ ካተድራል ጸሎት ሲያሳርጉ “ሴትየ ሆይ አትፍሪ! ዓለም የምታበራ ንፅሕት ብርሃን ትወልጅያለሽ” የሚል ድምጽ ሰሙ።። ልጅትዋ በተወለደች ግዜ በሰማችው ድምጽ መሠረት ክያራ (ንፅሕት) ብላ ሰየመቻት፣ ለጥምቀትም በዛኛው ካተድራል ወሰደቻት፣ ሕፃን ክያራ በጥሩ አስተዳደግ ካደገችና ከተማረች በኋላ በቅዱስ ፍራንቸስኮ ዘአሲዚ ስብከት የነበራትን ሁሉ እርግፍ አርጋ በመተው እንደ ጌታ ቃል ለመኖርና ቃሉን በፍጹም ለማስተንተን ከቤተ ሰቦችዋ በቅዱስ ዳምየን ቤተ ክርስትያን ተደብቃ ብዙ ግዜ ካሳለፈች በኋላ ሁሉ አልፎ ገዳም መሠረተች፣ በዚሁ መጠግያዋ በነበረው የቅዱስ ዳምያን ቤተ ክርስትያን “ድሆች ደናግል” በሚል የደናግል መሠረተች፣ ገዳሙ ከዛ በኋላ ለተቆረቆሩ ገዳሞችዋ መሪ ሆነ፣ ቅድስት ክያራ ከሞተች በኋላ የገዳሙና የደንግሎቹ ማኅበር ስም ክላሪሰ የሚል ሆነ፣ ቅድስት ክያራ በዚሁ ገዳም ለ42 ዓመታት ኖረች፣ ብዙ ጤናም አልነበራትም፣ በ1215 ዓም ላይ ቅዱስ ፍራንቸስኮስ የግዳሙ እመምኔት እንድትሆን ቅድስት ክያራን በመሾም የመጀመርያ የገዳም ደምብም ሰጣቸው፣ በ1253 ዓም ማኅበሩ በቤተ ክርስትያን ተቀባይነት አግኝቶ ር.ሊ.ጳ ኢንቸንሶ 4ኛ በአዋጅ አጸደቁት፣ ቅድስት ክያራም ከ2 ቀናት በኋላ ነሐሴ 11 ቀን 1253 ዓም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች፣ ከሁለት ዓመታት ብኋላ በ1255 ዓም ቅድስት ተባለች።።







All the contents on this site are copyrighted ©.